>
10:56 am - Sunday December 4, 2022

በአዲስ አበባ የመሬት ወረራው ህጋዊ ሽፋን ተሰጥቶት ፤ የፖሊስ አጀብ ተጨምሮለት እየተሳለጠ ነው!!! (ሀብታሙ ምናለ)

በአዲስ አበባ የመሬት ወረራው ህጋዊ ሽፋን ተሰጥቶት ፤ የፖሊስ አጀብ ተጨምሮለት እየተሳለጠ ነው!!!

ሀብታሙ ምናለ
 
* “ወለጋ ቢሆን ኖሮ እንከተክታቸው ነበር”
የወራሪዎቹ ዛቻ
*  ታከለ ኡማ ለወደደው እንዲህ በፖሊስ እያስጠበቀ መሬት ያድላል። ህገወጥ ወረራውም ቢሆን ለቤት ልጆች ሲሆን ህጋዊ ሽፋን ይሰጠዋል። 
*  ካልወደደህ ደግሞ  . . . ላይህ ላይ ቤትህን አፍርሶ በነዚሁ ፖሊሶች ከዱላ የተረፈውን በጥይት ቆልቶ። በአካባቢው ቀርተህ “ልማቱን” እንዳታደናቅፍ በ5 ባስ ጭኖ በፖሊስ አጀብ ባህርዳር ወስዶ ይጥልሃል።  ወይም ትላንት እንዳየናት እናት ከወለደች በ15 ቀኗ በአራስ አንጀቷ እናቷ ሞታ ሃዘን ላይ ከዚህ ሁሉ ጋር በኮረና ወረርሽኝ ቤቷን ንዶ ሜዳላይ ሲጥላት ታያለህ።
 
🛑  “ ቦታው መታጠር ተጀምሯል!
በአዲስ አበባ ከንቲባ ይሁንታ በወረዳ 12 የጥቅም ተጋሪዎች ፈቃድ፣ ቡልቡላ ላይ ያውም መንደር ውስጥ፣ መንገዱን በሚጋፋ መልኩ፣ በፖሊስ ልዩ ጥበቃ እየተደረገ ለቤተ እምነት በሚል ትላንት የጀመሩትን ቦታ በዚህ መልኩ እያጠሩት ይገኛሉ። “
በአዲስ አበባ የመሬት ወረራ የዕለት ክንውን ከሆነ ቆይቷል፡፡ በህገ – ወጥ መልኩ የሚያዙ ቦታዎች እዚህም እዛም ይታያል፡፡ ለዚህም ደግሞ የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ዑማ ዋና ተዋናይ እና ይሁንታ ሰጪ ነው፡፡
በመሬት ወረራ ከግለሰቦች እኩል የእምነት ተቋማትም ሲሳተፉ ይታያል፡፡ በቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ላይ የታየው ክስተትም ይህን ያረጋግጣል፡፡
የተወሰኑ የፕሮቴስታን እምነት ተከታዮች ነን ያሉ ቦታው ላይ በመገኘት ሰፊ መሬት ለማጠር ይሞክራሉ፡፡ ህዝቡም ወጥቶ ምን እንደፈለጉ ሲጠይቅ ለቤተ እምነት የሚሆን ቦታ እያጠሩ ፍቃድም እንዳላቸው ያሳውቃሉ፡፡ ህዝቡም “ቦታውን መንገድና መንደር ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡ ከተፈቀደላችሁ ማስረጃ አሳዩን ቢባሉም ፍቃደኛ ባለመሆናቸው፣ ከአንድ አመት በፊት ወደ ኃላፊነት ወደመጣው ወደ አቶ ቆሪቾ ጎሴ የሰላምና ፀጥታ ኃላፊ ይደወላል፡፡ እሱም “እናንተ ምን አገባችሁ?” የሚል ምላሽ ለነዋሪው ይመልሳል።
የአካባቢው ነዋሪ “መብታችንን አናስደፍርም የመሬት ወረራውንም በዝምታ አናይም” በማለት አጥር ለማቆም የተደረገውን ሙከራ አስቆመ። መሪቱን ለማጠር የሞከሩት ኃይሎች ለጊዜው ስፍራውን ለቅቀው ከሄዱ ከሰዓታት በኋላ የሰው ኃይል ጨምረው በአንድ የመከላከያ መኪና ጭምር በቅርብ ርቀት ክትትል እየተደረገላቸው ተመልሰው ለማጠር ሲመጡ የነዋሪው ቁጥር ሲበዛባቸው ችካል ብቻ ቸክለው፤ ነገ መጥተው እንደሚያጥሩ በእርግጠኝነት ተናግረው ሄደዋል፡፡
በክርክሩ ወቅት እነሱ “እናጥራለን!” ነዋሪው “አታጥሩም!” ሲሏቸው ለማጠር ከመጡት መካከል አንዱ …
በኦሮሞኛ “ወለጋ ቢሆን ኖሮ እንከተክታቸው ነበር”
በማለት ሲናገር ቦታው ላይ የነበሩ የኦሮሞኛ ቋንቋ በድንብ የሚሰሙና አቀላጥፈው የሚናገሩ ሰዎች ሰምተውታል፡፡
ቡልቡላ ላይ ከዚህ ቀደም…
* የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ወጣቶች በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው፣ ፍቃድ አግኝተው ስራ በሚሰሩበት ወቅት የሚሰሩበትን ቦታና (ሱቅ) አፍርሶ በሸገር ራዲዮ ጭምር ሲሸልል የነበረ መንግስት ፤
* አንድ ቆርቆሮ “ኳ” ስትል በር ላይ የሚደርስ ደንብ
አስከባሪና ፖሊስ ከየት እንደመጡ በማይታወቁ ሰዎች የመሬት ወረራ ሲደረግ እንዳላየ ማለፍ ብቻ ሳይሆን ከለላ መስጠትን መርጠዋል፡፡
ነዋሪውም በተደጋጋሚ እየተከናወነ ያለውን ህገ ወጥ ድርጊት በምሬት ለሚመለከተው አካል ቢገልጹም ሰሚ አካል አጥተዋል፡፡ ይሄ ደግሞ በመንግሥት አካል ከሚደረግ ሽፋንና ድጋፍ ውጭ ማንም ደፍሮ እንደማያደርገው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

https://www.facebook.com/100021360467208/posts/593321791389831/

Filed in: Amharic