>

የጣና ሀይቅን በተመለከተ  የእኔ  የግል ምልከታ ...!!!  (ዘመድኩን በቀለ)

የጣና ሀይቅን በተመለከተ  የእኔ  የግል ምልከታ …!!!

 ዘመድኩን በቀለ 
•••
ጣና እኮ ደረቀ። ጣና ጣና እኮ ተነነ። ጣናን እኮ አረም፣ እንቦጭ ወረረው አትበሉኝ። እና በዚህ አያያዛችን ጣና ላይደርቅልህ ኑሯል? ጣና እኮ ሀይቁ ራሱ በወያኔ ህወሓት እንደ አንድ ህይወት እንዳለው ሰው የተከሰሰ፣ የተጠመደ፣ እንደ ዐማራ፣ እንደ ኦርቶዶክስ የተቆጠረ ጥርስ የተነከሰበት ሀይቅ ነው። እና ላይደርቅ ነው? መለስ ዜናዊ፣ ስብሐት ነጋ፣ ስዩም መስፍን፣ ዓባይ ፀሐዬ እንደ አባት ገዳያቸው በሚቆጥሩት፣ በመርፌ፣ በበሽታ፣ በጦርነት ፈጅተው አላልቅ ያላቸው የዐማራው ነገድ ሀብት ስለሚመስላቸው ጣና ባይደርቅ ነበር የሚገርመው።
•••
ህወሓት ማለት እኮ የኢትዮጵያ አሲድ ናት፣ መርዝ፣ ዓለምማያን ያደረቀች ኮቴ መናና፣ እነ ሻላን፣ አብያታን ያተነነች በረሃ የበረሃ ውላጅ የደደቢት ዛር፣ ኢትዮጵያን በአጥንቷ ያስቀረች ሰላቢ እኮ ናት። እና ጣና ባይደርቅ ነበር የሚገርመው።
•••
ጣና እኮ ኦርቶዶክስ ነው ተብሎ ተፈርጇል። ጣና የተዋሕዶ ሐብት ነው ተብሎ ተፈርጇል። ጣና ዐማራ ነው ተብሎ በእነ አቦይ ስብሀት ነጋ ተፈርጇል። ዐማራና ኦርቶዶክስ ደግሞ አከርካሪው መሰበር አለበት ተብሎ በግልጽ ፖሊሲ ሲሠራበት ተከርሟል። ዐማራንና የዐማራ ሀብት ነው ብላ ወያኔ የፈረጀችውን ሁሉ [ ኢንኬዝ የፈረንጅ አፍ እዚህ ጋ ይገባል] እሷ ባትኖር እንኳ ዳይፐር ቀይራ፣ ጡጦ እያጠባች፣ በአንቀልባ አዝላ በሳደገቻቸው የጉዲፈቻ ልጆቿ አማካኝነት ሰበራውን እንዲቀጥሉላት አድርጋ ነው እሷ መቐለ የመሸገችው።
•••
በረከት ስምኦን ኤርትራዊ ሆኖ ለኢትዮጵያም፣ ለዐማራም ይሠራል ብሎ ያስብ የነበረ የዋሕ ህዝብ ጣና ዐይኑ እያየ ባይደርቅ ነበር መገረም የነበረበት። ዐቢይ አህመድ ሃይማኖቱ እስላም ነው። በልቡ የሚያምነው እስልምናን ነው። በአፉ ደግሞ ጴንጤ ነው። ጴንጤነቱ ለሥልጣኑ ጠቅሞታል። ከምዕራባውያኑ ድጋፍ ያስገኝለታል። ፕሮቴስታንቱ ዓለም ኖቤል የሸለመው እኮ አቢቹ ተአምር ሠርቶ እኮ አይደለም። በአፉ ኢየሱስ በልቡ አልቁዱስ እንደሆነ ስለሚያውቁ እኮ ነው። እውነታውም ይሄው ነው።
•••
ብዙ ሰው የዐቢይ መንግሥት ጣናን የሚታደግ መስሎት ይለምነዋል። በተስፋም ይጠብቀዋል። ይማጸነዋልም። ዐቢይ የጋለ የእሳት አሎሎ ነው። በሜካፕ የባደ፣ ሲያዩት ሲሰሙት የሚያምር፣ ለወዳጆቹ ማር ለጠላቶቹ ሬት፣ አፈ ቅቤ ሆደ ጩቤ ነው። ለዚህ ነው አይንህ እያየ አናትህ ላይ መስጊድ የሚሠራው። ዐቢይ ግን ምኑ ሞኝ ነው። መስጊድ መሥራቱን ትቶ ጣናን የሚያድንልህ። ዐቢይ እኮ የእስልምና ምክር ቤቱ ኧረ ይሄ ነገር እንዴት ይሆናል እያለ፣ ቤተ ክርስቲያን በር ላይ መስጊድ እንዴት ይሠራል እያለ፣ ሕጉ እኮ አያዝም ተዉ እንጂ እያለ፥ ምንአባታቸው ያመጣሉ ብሎ 30 ሺ ካሬ ሜትር መሬት በነጻ ያደለ የሼክ ልጅ ነው። እና ጣና ለምን በአፍጢሙ አይደፋም። ጉዳዩ አይደለም።
•••
ደመቀ መኮንን እስላም ነው። ወያኔ ፀረ ዐማራ አድርጎ ኮትኩቶ ያሳደገው እስላም ነው። እና ደመቀ አክራሪ እስላም ሆኖ ጣናን ምን ይፍጠርልህ? ምን ያድርግልህ? ጉዳዩ ነው እንዴ? ለምን መድረቅ አይደለም ትንን አይልልህም። ትቀልዳለህ እንዴ? ዐማራ ነኝ ብሎ የዐማራን ስም ይዞ በዐማራ ኮታ የዐማራን የሥልጣን ድርሻ ይዞ ፀረ ዐማራ ሆኖ በህወሓት ተኮትኩቶ ያደገ እኮ ነው። ዘሬ ኦሮሞ ነው የሚል የዐማራ ባለሥልጣን፣ ዘሬ ትግሬ ነው የሚል ዐማራ ላይ የተሾመ ባለ ሥልጣን እንዴት ብሎ ነው ዐማራ ነው፣ የዐማራ ነው ተብሎ የተፈረጀን የጣና ሐይቅ ስለ ዐማራው ግድ በማይሰጣቸው በደመአ መኮነን ይታከምልናል ብለህ ማሰብህ ይገርማል። እናም አዳሜ ከመንግሥት ምንም አትጠብቅ። በዐማራ ሰበብ፣ በዐማራ ጥላቻ ጣናም ዐማራ ተደርጎ እንዲተን፣ እንዲደርቅ ተፈርዶበታል። ኦርቶዶክስ ነው ተብሎ ጣናም በኦርቶዶክስነት ስለተፈረጀ ለምን አይተንም ጉዳያቸው አይደለም። እውነቱ ይሄው ነው።
•••
በአዴን የተባለው ፓርቲ ስብስቡ በሙሉ ሆደ ሰፊ፣ ጭንቅላተ ጠባብ ነው። እንደ ጉማሬ እንደ ዝሆን ሆዳቸው ለጠጥ ያለ ፍጥረታት ናቸው። ብአዴኖች እንደ ሰጎን ያለ ሚጢጢዬ ጭንቅላት ባለቤቶች ናቸው። ከየቦታው በወረንጦ ተመርጠው ነው የተሾሙት። ተፈልገው። በእጅ በእግር፣ በፈረስ ተፈልገው፣ በባትሪ ተፈልገው ነው የተሾሙት። ላቀ አያሌውን ተመልከቱት ይጾማል አሉ። አሉ ነው እኔ አላየሁም። ገዱ አንዳርጋቸውን ተመልከቱት የጽጌን ጾም ሳይቀር ይጾማል አሉ። ነገር ግን ቅንጭላት የለም። ቅንጭላት ከየት ይምጣ? አይደለም ጣና ዐማራም፣ ኦርቶዶክሱ ክፍል ትግሬውን ጭምር፣ ኦሮሞውንም የሚያደርቅ ኃይል ነው አሁን ስልጣን ላይ ያለው።
•••
አንተ ብቻ ጣና ዳር ተቀምጠህ እዬዬ በል። ጎርጎራ ወደቡ ዳር ቁጭ ብለህ አልቅስ። ጎንደሬ፣ ጎጃሜ ማዶና ማዶ ሆነህ ኢኚኚኚ በል። በውጭ ያለው ኦርቶዶክሳዊ ዐማራ ለዐቢይ በቀን 1 ዶላር እያዋጣ መሃል ሸገር ላይ ከእንጦጦ ጋራ ስር የሚፈስ፣ ከሽሮ ሜዳ ነዋሪ ሽንትቤት በሚፈስ ውኃ ያማረ፣ ከፒያሳ ሆቴሎች በሚለቀቅ ትኩስ ካካ የደመአ ግሩም ክርፋታም ሀይቅ ይሠራለት ዘንድ ያዋጣል። ሆዳም ዐማራው ለነገ አያስብም። ሆዳም ትግሬው፣ ሆዳም ኦሮሞው ለነገ ለትውልድ አያስብም። አይጨነቅም። የጣና መድረቅ ለህወሓትና ለኦህዴድኦነግ ካድሬዎች ትልቅ ድል ነው። ዐማራ አምሮበት እንዴት ይኖራል ባይ እኮ ነው የህወሓት የቦለጢቃ ፊሎሶፊ። ከዐማራ የሚፈለገው ቆንጆ ቆንጆ ሴቶቹና ማኛ ጤፍ፣ ኮረንቲው፣ ግብሩ ብቻ ነው። ይኸው ነው።
•••
መፍትሄው አንድና አንድ ብቻ ነው። ከኢ ቦ ። አትዘፍዘፍ፣ አትጎለት፣ ተነሥ ተጠራራ፣ ተሰባሰብ። ተመካከር፣ ራስህ ሥራውን ሥራ። የሚሠራልህ ስለሌለ አትዘነጋ። ጅል ጅላንፎ አትሁን። ከብት ነህ እንዴ ደመአ መኮንን ጣናን ያድንልኛል ብለህ የምትጠብቀው? የአኖሌን ሃውልት የሚንከባከበው የአሩሲው ንጉሡ ጥላሁን ጣናን ምን ያድርግልኝ ነው የምትለው? አታስጨንቋቸው እንጂ። ለጣና የመጡት ማሽኖች የት ደረሱ? ለጣና እምቦጭ ማስወገጃ ተብለው ከውጭ ሃገር የገቡት እና በሀገር ውስጥ ጭምር እንተሠሩ የተነገረላቸው  ማሽኖች ምን በላቸው? ዐማራ ሀብቱን መቆጣጠር ለምን አቃተው? ዘራፍ እኔ ጎንደሬ፣ የቴዎድሮስ ልጅ፣ እኔ።ወሎዬው፣ እኔ ጎጃሜው፣ እኔ የሸዋ የሚኒልክ ዘር እያልክ ቀረርቶ፣ ፉከራ፣ ሽለላ ጣናን አያድነውም። እስከ አሁን ለጣና እምቦጭ ማስወገጃ ታስበው የተገዙት እና የተገነቡ ማሽኖች ወደ ስድስት እንደደረሱ ተነግሯል። እነሱም፦
• በጎንደር ዩንቨርስቲ የተሠራው
• በባህር ዳር የንቨርስቲ የተገዙ
• በአማጋ ሓላፊነቱ የተወሰነ ማኅበር ከቻይና የመጣው።
• በካናዳና በሲያትል በሚኖሩ ኢትዮጵያዊን ባለ 120 ፈረስ ጉልበት ተብሎ የተገዛው።
• በአትላንታ እና በእስራኤል የሚኖሩ ኢትዮጵያን በተሰበሰበ ገንዘብ ከካናዳ የትገዛው ባለ 25 ጉልበት ማሽን
• አቶ ከተማ ከበደ ( ኬኬ) እስር ቤት እያሉ የሰጡት እስካቫተር እና በሚሊዮኖች ብር የወጣባቸው የጣና ብሮች ማን በላቸው?
• ዶክተር በላይነህ ክንዴ ብሩን በልቶ የውሸት ሪፖርት ሲያቀርብ ቁጭ ብለህ ስታጨበጭብ ከርመህ፣ ሰውየው ጣናን አድርቆ ሲሄድ አይተህ እንዳላየህ ዝም ብለህ ከርመህ፣ ለጣና ተብለው የተገዙት ማሽኖች የት ደረሱ? ለጣና ተብሎ የተሰበሰበው በቢልዮን የሚቆጠር ገንዘብ የት ገባ? ብለህ ሳትጠይቅ ከርመህ የሆነ ቀን ድንገት ብድግ ብትት ብለህ ስካሩ እንደለቀቀው ሰካራም፣ ከእንቅልፉም እንደሚነቃ ህጻን እሪሪሪ ትልልኛለህ። አቢቹ ጡጦ የሆነች ዲስኩር፣ ታከለ ቀሽት የሆነች ፎቶ፣ ደመአ ወኔ ቀስቃሽ ንግግር አድርጎ መልሶ ሊያስተኛህ ደርሰህ እዬዬ ስትል በሳቅ ነው የማላገኘውን ፍርፍር በሃሳቤ የምታበላኝ። [ ፍርፍር ግን ስንት ገባ ? ]
•••
እናም በዐማራ ላይ ግፍ የሠራ የጠየቀም የተጠየቀም የለም። በኦሮሚያ ያን ሁሉ ወጣት ያስገደሉት እኮ አሁን የለውጥ ሃዋርያ ናቸው። ትግራይ ወጣቱን ህወሓት እየገደለች ( ፖሊሱ በቁጥጥር ስር ዋለ)  ትልልሃለች። እናም ወዳጄ ነጠላህን አዘቅዝቀህ ለብሰህ፣ ደረትህን እየደቃህ፣ ፀጉርህን ፂምህንም እየነጨህ ዋይ ዋይ ተለያየን እያልክ አታለቃቅስብኝ። ተው ማልቀስህን አቁመህ ለጣና ሃኪም ሁነው። ጣና ክፉኛ ታመመ እንጂ አልሞተም። ማከም የምትችለው ደግሞ ራስህ ነህ። አህመዲን ጀበል የሞጣ ጉዳይ እንጂ የጣና ጉዳይ ጉዳዩ እንዳልሆነ እወቅ። ዐቢይ አህመድን እርሳው። ደመአ መኮንንም እርሳው። ራስህ መፍትሄውን አምጣው።
•••
በየፌስቡኩ እየዞርክ አስለቃሽ አትፈልግ። ዘመዴ ስለጣና የሆነ ነገር በል እንጂ አትበለኝ። አትጨቅጭቀኝ። አንተ የምትለውን ነው እኔም የምለው። አንተ የምትለውን ነው እኔም የምደግመው። የገደል ማሚቶ ሆኜ ከማገልገል፣ የአንተኑ ጩኸት ከማስተጋባት በቀር ሌላ ምንም ልረዳህ አልችልም። ምንም አልኩህ። ጣና አይንህ እያየ ከደረቀ ተጠያቂው ዐቢይ አህመድ ብቻ አይደለም። ብአዴንም አይደለም። ተጠያቂዎቹ ራሳችን፣ ራሳችሁ ጭምር ናችሁ። ራሳችን ነን ተጠያቂው። የጣና መድረቅ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት የመፍረስ ምልክት ነው። ሀገርም እምነትም አይፈርስም። መንገራገጩ ግን አይቀርም። ታዲያ ለዚህ ተጠያቂው አንተ ራስህ ነህ። ይሄን ጦማር የምታነቡ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ። አከተመ።
•••
ሀይቅ ይደርቃል? አዎ ይደርቃል። አልጀዚራ አምሐሪክ ከተባለ ገጽ ላይ ያገኘሁትን ላካፍላችሁ። [ ጣና እንደ የአረል ሐይቅ ነው የሚለው ርዕሱ]
•••
ምንም እንኳን የጣና ሐይቅ ሕመም እንደ COVID 19 ሁሉ፣ ድንገተኛ ቢሆንም በልዩ ልዩ ምክንያቶች ባለፉት 60 እና 50 ዓመታት ብቻ በሰው ልጅ ለተፈጥኖ በማይስማማ ተግባርና በአካባቢያዊ የአየርን ብረት ለውጥ ምክንያት በርካታ ውኃማ አካላት ጠፍተዋል። እየጠፉም ናቸው። ከእነዚህ ፩ኛው በቀድሞዋ ሶቬየት ኅብረት ይገኝ የነበረው #አረል_ባሕር (Aral Sea) ነው።
•••
አረል ባሕር፣ በዓለማችን ከሚገኙ ሐይቆች በግዝፈቱ 4ኛ ነበር። የባሕር ተፋሰሱ፦ ካዛኪስታን፣ ኪርጊስታን፣ ታጃኪስታን፣ ተርኪስታን እና ኡዝቤኪስታን የተባሉትን ከሶቬት ኅብረት የተገነጠሉ 5 ሀገራትንም የሚያካትት ነበር።
•••
ይሁን እንጅ እ.ኤ.አ. ከ1960 ዓ.ም ወዲህ በገጠመው፣ በተለይ በሐይቁ በቅርብ እርቀት ከሚገኙ፣ የኪዚልኩ፣ የካራኩም እና የኡስተርት በረሃዎች በሚነሳ ነፋስ የሚፈጠረው፣ የነፋስ ብክለት (wind erosion) ሐይቁን በጨዋማ አፈር እየሞላ በ2 ትውልድ (በ60 ዓመታት) እንዳልነበረ አድርጎታል።
•••
ቀድሞውኑ በሐይቁ ላይ ይርመሰመሱ የነበሩ የመጓጓዣ እና የንግድ መርከቦች አሸዋ ላይ ተተክለው፣ ለትዝብት ቀርተዋል። ወደ ሀይቁ ይመጡ የነበሩ ወቅታዊ አእዋፍት (migratory birds) ባልተገመተ ጊዜ እስካንድያው ተሰናብተውት ቀርተዋል። ዓሣ ማስገር እና በደማቅ ሰማያዊው የአራል ባሕር በዋና መዝናናት፣ በሐይቁ ዙሪያ መስኖ ማልማት ተረት ሆኗል። ጣና ሐይቅስ? ባሕር ዳር ሆይ ምን አልሽ? በማለት ይጠይቃል። እንቦጩን ማድረቅ የሚችል ከኬሚካል ነፃ የሆነ እንቦጭ ማጥፊያ የሠሩ አባት ሁሉንም ነገር ልከውልኝ ብአዴን አፍኖት እንደያዘው አጫውተውኛል። ጣናን ብአደፀን እንዲጠፋ ለምን እንደፈለገ ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው።
•••
እናም ወዳጄ አትጨቅጭቀኝ። ብቻህን አልቅስ። አትረብሸኝ። የጣና ሀይቅ በግራኝ አህመድ ጊዜ ያልተዘረፈው፣ ያልተመዘበረው፣ ያልተቃጠለው እኮ ውኃ ላይ ስለነበረ ነው። አሁን ግን ጣና በግራኝ አህመድ የልጅ ልጆች ዘመን ውኃው የብስ ሆኖ ደርቆ ለዘራፊ ክፍት ይሆናል።
•ግራኝ መሐመድ [ አያት ]
• ዐቢይ አህመድ
• ጃዋር መሐመድ
• ደመአ መኮነን ሐሰን፣ አሊ አባቦራ
• ሙፈርያት ካሚል
• ካሚል ሸምሱ
• አቡበከር አህመድ
• አሕመዲን ጀበል
•• ለማ መገርሳ
•• ሽመልስ አብዲሳ
•• ኩማ ደመቅሳ
•• አዲሱ አረጋ ፈይሳ
•• ህዝቅኤል ጋቢሳ
•• ፀጋዬ አራርሳ
•• ዶክተር ገመቺሳ
•• ታከለ ዑማ
•• ግርማ ጉተማ ስለጣና፣ ስለ ኦርቶዶክስ ምን ይፍጠሩልኝ ነው የምትላቸው። አንተ በእነሱ ፍቅር ተጠልፈህ፣ በቀን አንድ ዶላር ለማኪያቶ ያልካትን ቀንሰህ ትገብርለታለህ እሱ ሆዬ ዓለም አቀፍ መስጊድ ቤተ ክርስቲያን ጊቢ ውስጥ ይሠራልሃል። በዶላርህ ጣናን አታክመውና ሩቅም ቅርብም ሆነህ እዬዬ በል። አልቃሻ  !!
•••
እናም ተወኝ ተፋታኝ። ስለጣና አትጨቅጭቀኝ። እኔ አሁን በአቅሜ መሥራት የምችለውን ልሥራበት። ለአብነት ተማሪዎቹ ልጩህላቸው። ለአብነት ተማሪዎቹ እዬዬ ልበልላቸው። በየመቃብር ቤቱ ወድቀው በረሃብ ለሚያጣጥሩት በበሽታ ለሚሰቃዩት ልድረስላቸው። ተወኝ አትጨቅጭቀኝ። የተጻፈ ጦማር እንኳ ፈርተህ ሼር የማታደርግ ቦቅቧቃ፣ ራስወዳድ አንተ አታድክመኝ። አታዝለኝ። ሌላው ሞቶልህ አንተ ነፃ መውጣት የምትፈልግ፣ አንተ በሞቀ ቤትህ ተቀምጠህ እኔ ከእነ ልጆቼ በአውሮጳ ጎዳና እየኖርኩ እንድጮህልህ አትጠብቅ። ፈሪ በመጀመሪያ ከፍርሃት ራስህን ነፃ አውጣ። ሆዳም በመጀመሪያ በአበልና በድግስ ለከርስህ ብለህ ሃገር አትሽጥ። ተወኝ ብዬሃለሁ። ተወኝ።
•••
ኢንተርኔት ለመጠቀም ዋይፋይ ፍለጋ ብርድ ለሚቆጋኝ ለእኔም እዘንልኝ እንጂ። በጀርመን በታላቋ የአውሮጳ ከተማ የአፍሪካ ገጠረማ ስፍራ እንደሚኖር ሰው ለተፈረደብኝ ለእኔም እዘንልኝ እንጂ። ሆድ አታስብሰኝ። የያዝኩትን ልጨርስ፣ በሞቀበት ሁሉ አትጣደኝ። በእናትህ ተወኝ። እኔ ያለሁበትን ስቃይ እኔው ነኝና የማውቀው እኔን ተወኝ። አንተ የደላህ ሶዬ ተወኝ ተፋታኝ። በተመቻቸ ህይወት ውስጥ ሆነህ መሥራት ያቃተህ ሶዬ ስለፈጠረህ እባክህ ተወኝ። እኔ በቤቴ ዋይፋይ ስለሌለኝ ደጅ ወጥቼ ነው በብርድ፣ በንፋስ፣ በፀሐይ ስልኬ ላይ ተደፍቼ አይኔ ብዥ እስኪልብኝ የምለፋው የምደክመው። አንተ የደላህ ነህ። ተፋታኝ አልኩህ ተፋታኝ።
•••
የምወዳችሁ እናንንት “ የትናንቱን ለነገ ” ዓላማ ደጋፊዎች ግን ተዘጋጅታችሁ ጠብቁኝ። ስንደራጅ፣ ስንሰባሰብ ለሁሉም ነገር መፍትሄ ይኖረዋል። ጥቂቶች ሆነን ተአምር እንሠራለን። እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ምስክሬ ናት ተአምር ነው ነው የምንሠራው።
•••
አሁን እስከ አሁን በሚልየን የሚቆጠሩ ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች ድምጼን ሰምተው ያለማቅማማት ተቀብለውኛል። ህወሓትን ስለጮህኩባት ያኮረፉኝ የትግራይ ልጆችም ታርቀውኛል። ኦነግናና ኦህዴድን ስለወቀስኩ ያኮረፉኝ ኢጆሌ ቢየ አባኮቲ ወጂኒስ ወሊአራረምኔ ጂራ። የበድኑ ብአዴን ደጋፊዎችም በመጠኑ እየሰሙኝ ነው። በአጠቃላይ እመነቱ አንድ ላይ እንድንቆም አድረጎናል።
• 200 ሺ የቴሌግራም አባላት ጨቅ ብለው እየተወያዩ ነው።
• በሀገሪቱ አሉ የተባሉ የሕግ ባለሙያዎች የመተዳደሪያ ደንብ፣ የማኅበሩን መመሥረቻ ሠርተው ጨርሰዋል።
• ደማቸውንም፣ ገንዘባቸውንም፣ እውቀታቸውንና ጊዜአቸውን የሚሰጡን በሃይማኖታቸው የተከበሩ፣ በመንግሥትም በቤተ ክህነቱም አንቱ የተባሉ ባለሙያዎች የተሰባሰቡበት የቦርድ አባላት ተሟልተው ሥራ ሊጀምሩ በዝግጅት ላይ ናቸው።
• ትናንት ብቻ ባቀረብኩት ጥሪ መሠረት አሁን ላይ 271 የሚሆኑ አርክቴክቶችና መሃንዲሶች የቴሌግራም ግሩፕ ከፍተንላቸው እየተዋወቁ፣ እየተወያዩም ነው።
• አሁን ጠዋት ባቀረብኩላቸው ጥሪ መሠረት በዚህች ደቂቃ ብቻ ከመላው ዐለም የተሰባሰቡ 172 የአይቲ ሳይንቲስቶች በከፈትኩላቸው የቴሌግራም ግሩፕ ውስጥ እየተወያዩ፣ ስማቸውን እየተዋወቁ ይገኛሉ። ወዳጄ መዳኛህ መሰባሰብ ብቻ ነው። ሌላ ምንም መፍትሄ የለም።
• በቀጣይ ወደ ማታ ደግሞ ወደማታ ጥሪ የማቀርብላችሁ የተዋሕዶ ልጆች አላችሁና ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ። አንድም ሰው አይቀርም። ተዘጋጅተህ ጠብቅ። ጨረረቄን ማቄን ሳትል ለራስህ ስትል፣ ለልጆችህ ስትል ተዘጋጅተህ ጠብቅ። ነግሬሃለሁ። መፍትሄው ራስህ እጅ ላይ ነው።
•••
• ግዙፍ የሆነ የኦርቶዶክሳውያን ሆስፒታል ዲዛይን።
• ግዙፍ የሆነ የኦርቶዶክሳውያን ትምህርት ቤት ዲዛይን።
• ግዙፍ የሆነ የኦርቶዶክሳውያን የግዕዝ ዩኒቨርሲቲ።
• ግዙፍ የሆነ የሊቃውንተ ቤተክርስቲያን መርጃ ማዕከል
• ግዙፍ የሆነ የኦርቶዶክሳውያን ባንክ
• ግዙፍ የሆነ የኦርቶዶክሳውያን ኢንሹራንስ
• ግዙፍ የሆነ የኦርቶዶክሳውያን የሥነ ዜማና የሥነ ጽሑፍ የጥናትና የምርምር ማዕከል
• ግዙፍ የሆነ የኦርቶዶክሳውያን የመድኃኒት ቅመማና የዕጸዋት ምርምር ማእከል።
• ግዙፍ የሆነ የኦርቶዶክሳውያን የሥነ ህንጻ ጥበብ ትምህርት ቤት
• ግዙፍ የሆነ የኦርቶዶክሳውያን የሥነ ሥዕል ትምህርት ቤት ዲዛይኖች ይዘጋጁ። በምን ገንዘብ፣ መቼ ሊሠሩ ወዘተረፈ ብቻ እንዳትሉኝ። ይዘጋጁ። ይዘጋጁ። ይዘጋጁ። ተናግሬአለሁ። በዚህ ዘመን ተሻጋሪ ፕሮጀክት ላይ እያንዳንድህ አሻራህን ለማስቀመጥ ተዘጋጅ።
•••
ማስታወሻ | ~ በነገው ዕለትም በከርቸሌ አካባቢ በ30 ሺ ሄክታር ላይ ስላረፈው መስጊድ ጉዳይ የራሴን ምልከታ ይዤ እቀርባለሁ። በመስጊዱ መሠራት ምንም ተቃውሞ የለኝም። ነገር ግን በሕጋዊ አሠራርና በእኛ በራሳችን ጉዳይ ላይ አስተያየት እሰጣለሁ። ዘለግ ያለች ጦማር ናት። ውኃ እየተጎነጫችሁ የምታነቧት ጦማር ናት። ነገ እሁድ ጠብቋት። ብሞትም አይቆጨኝ።
••• ሌላው የጴጥሮሳውያን ኅብረት ተብዬ ሆዳም ጉደኞች ምደረ የደሃ አእምሮ ባለቤት፣ ገና ምኑንም ሳትይዙት የታከለ ኡማ ካዳሚ ሆናችሁ አሉ። ኮንዲሚንየም አገኛችሁ እንዴ? ከተማ አስተዳደሩ ላይ ወሸቃችሁ እንዴ? ድራሽ አባታችሁ ይጥፋና ምነው ስለ ከርቸሌው ጉዳይ ዝም አላችሁ። እናንት ከሃዲዎች ተጠንቀቁ። የመስከረም 4 ቱን ሰልፍ አሳልፋችሁ ሽጣችሁ ለውርደት መዳረጋችሁ ሳያንስ አሁን ደግሞ በምስር ወጥ በኩር ኦርቶዶክስን ለመሸጥ ድርድር ላይ ናችሁ አሉ። ጠብቅ ምድረ አፈጣድቅ ነጠላ ሁላ። ጠብቀኝ አልኩህ። አንት ይሁዳ የይሁዳ ልጅ።
•••
ሻሎም !   ሰላም !
ግንቦት 15/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic