>

50 አመታት  አንባገነናዊ ፓርቲ?!....  ፈንቅል ይለውጠዋል! (አምዶም ገ/ሥላሴ)

50 አመታት  አንባገነናዊ ፓርቲ?! ፈንቅል ይለውጠዋል!

አምዶም ገ/ሥላሴ

በአለማችን ውስጥ የዛሬ ሃምሳ አመት በነበረው ጭንቅላቱ፣ አስተሳሰቡ እና አንድ አይነት ሰዎች ህዝብን ልምራ የሚል ፓለቲካ ከህወሃት በቀር ሌላ ፈልጎ ማግኘት የ10 ሚሊዮን ዶላር ጥያቄ ነው ብንባል ፈፅሞ አናገኝም።
ከህወሃት ሽማግሌዎች በቀር አለማችን ባለፉት 50 አመት በርካታ ለውጦችን አስተናግዳለች። እነሱም:-
         – የማያቋርጥ የቴክኖሎጂና የኦኮኖሚ ለውጥ
         – ከእርሻ ወደ ኢንዱስትሪያላይዜሽን ሽግግር
         – ከቦታ ቦታ በቀላሉ እና በፍጥነት መዟዟር መቻል
         – ከፍተኛ የሆነ የተማራ የሰው ሃይል ምጣኔ እድገት
         – በስራ ክፍፍል ማመን የተጀመረበት
         – ዘመናዊነትና የከተሞች መስፋፋት
         – ከአንባገነናዊነት ወደ ዲሚክራሲያዊ መንግስት
         – መዋቅር ከሌለው ወደ ቢሮክራቲክ አሰራር መለወጥ
         – ቡድን ግለሰባዊ ተጠያቂነት አለማስቀረት
         – ከቤተሰባዊነትና ቡድነኝነት ይልቅ ተወዳዳሪ መሆን
         – አሳታፊ የሆነ ፓለቲካና የህግ ማእቀፍ እድገት
         – የህዝቦች አኗኗር እና የባህል መቀራረብ
በአጠቃላይ አለማችን በማህበራዊ፣ ፓለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በከፍተኛ ፍጥነት በተለወጠችበት በዚህ ወቅት የህወሃት መሪዎች ግን ከአለም ለውጥ ጋር አብሮ መሄድ የሚችሉ የተሻለ ለተማሩ ልጆቻቸው ስልጣንን አላስረክብ ብለው በድርቀት ላለፉት ሃምሳ አመታት በአንድ አስተሳሰብ፣  በአንድ ቤተሰብ አባላትና የባልና ሚስቶች ስብስብ በህዝቡ ሃብት ላይ ሲቀልዱ ከርመዋል።
በመሆኑም ማናችንም ብንሆን ባልተለወጠ አስተሳሰብ መመራት ስለማይገባን ዘማቻ #ፈንቅል ን ልናበረታታ ይገባል።
ፓለቲካ ሃይማኖት ስላልሆነ የማይናወጥ መስመር አቅፈን ለመስመር መዘመር ሳይሆን የሚገባው ከግዜ ጋር አብሮ የሚለወጥ አስተሳሰብን ነው መከተል ያለብን።
በግል ለፈፀመው ወንጀል ተጠይቅ ሲባል በቡድን ውስጥ ተደብቀው “እኔ መንካት ይህንን ብሔር መንካት ነው” በሚል በህዝቡ ውስጥ የወንበዴ ዋሻ የሚገነቡትን በቃ ማለት አለብን።
በህዝቡ ስም በኤፈርት ነግደው ያፈሩት   ህዝብ ሃብት ነው። በመሆኑም ጥቂት ሰዎች ብቻ በሚያውቁት አግባብ በግለሰብ ስም በውጭ አገር ያስቀመጡን ገንዘብ የት ባንክ? በማን ስም? እንዳስቀመጡ ህዝቡ መጠየቅ አለብን።
በዚህ በሰለጠነ ዘመን ከግዜው ጋር የሚሄዱ ወጣቶች ህዝቡን ሊመሩት ነው የሚገባው።
ስልሳ ሺህ ህዝብ መስዋእት የሆነበት የትግል ውጤት የአንድ ቤተሰብ አባላት እና የባልና ሚስቶች ስብስብ ኋ/የተ/የግ/ማህበር መሆኑ በቃ ሊባል ይገባል!!!!
Filed in: Amharic