ግንቦት 20 ለሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን የውርደት ቀን!
ታየ ቦጋለ አረጋ – ኢልመ ደሱ ኦዳ
*
በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ (1939-45) የፋሺስቶች ጎራ “በፍትህ ፈላጊው ዓለም” ኃይል ድባቅ ተመታ። የናዚዎቹ ሳጥናዔላዊ ኢብሊስ ቡድን የ50ሚሊየኖችን ክቡር ህይወት ከነጠቀና አያሌ የንብረት ውድመት ካስከተለ በኋላ የግፈኞቹ ጎራ በአውሮፓ ተንኮታኮተ። ይህ ቀን፦ May 8,1945 = VE የአውሮጳውያንና የመላው ዓለም ነፃነት ናፋቂ ህዝብ የድል ቀን ሆኖ መከበር ጀመረ።
*
ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ ውስጥ መከበር ባለበት የድል ቀን ዙሪያ ወደፊት የምንወያይ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ (የማያወዛግቡ፦ የካቲት 23 – አድዋ፤
ሚያዝያ 27 – የአርበኞች ቀን አሉልን) …
በሚያሳፍር ሁኔታ ልቦለዳውያኑ፤ የድል ቀን ቀርቶ የውርደት ቀን ይከበር ቢሉን ነው እኛ የሚገባን…
‘ጀርመን መራሹ Axis Powers በርካታ ሀገሮችን የወረሩበትና ጊዜያዊ ድል ያገኙበት ዓመታት መነሻ የግፍ ቀን (ግንቦት 20) ይከበር’ ማለታቸው መሆኑን ነው። ደግሞም ጥርጥር የለውም።
የአጫጭር ፍቅር መድብል ደራሲዎችን ስንታዘብ፤
የየሠፈሩ የጎበዝ አለቆች የጦርነት ሴራ ተንታኝ ሆነው እኮ ነው የተቸገርነው¡¡¡
*
የጀርመን ናዚዎች በ፦ Allied Powers (የቃል ኪዳኑ ሀገሮች) እንደተሸነፉት ሁሉ፤ የወያኔ ትህነግ ናዚዎች፦ በኢትዮጵያውያን ትግል ባጠቃላይና በቄሮ ፋኖ ዘርማ ኮንሶ ወጣቶች (ኦሮማራ) ትግል በተለይ መጋቢት 24/2010 ድባቅ ተመተው ወደ ተነሱበት ደደቢት ተመለሱ። ታዲያ የናዚዎቹ ቀን ይከበር ወይስ (አንፃራዊው) የድል ቀን?! ይህም ቀን መከበር እንደሌለበት አምናለሁ። ገና አልለየለትምና!
የውርደት ቀን ግን በምን ስሌት ይከበራል?!
ሀገራዊ ኃፍረት = ሀገራዊ ውርደት።
እነ Short Memory ሜጀር ጀነራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ እኮ በቅርቡ፦
“የታገልነው ለትግራይ ነው፤ ለኢትዮጵያ የሆነ ርዝራዥ ተርፏት ይሆናል” ማለቱ አይዘነጋም።
የህወሓት ማኒፌስቶ እና የደረሰው ግፍስ?
*
የአጫጭር ፍቅር ልቦለድ ደራሲዎቹ ታዲያ የኢትዮጵያውያን ድል ቀርቶ፤ ሀገር የተዋረደቺበት የተከፋፈለቺበትና ከዚህ በታች የተዘረዘሩት 30 የግንቦት 20 መርዝ ፍሬዎች ይከበሩ እያሉን ነው።
ሰው ሲመረቅን ወይም ተጋዳሊት ሴት ሲያቅፍ አይፃፍ የምንለው ለዚህ ነው።
*
የወያኔ የ27 ዓመታት ሌጋሲዎች፦
1. ግብረሰዶማዊነት
2. የተናጠልና የተደራጀ ዝርፊያ
3. ከፋፋይነት ጎሰኝነት = አንድነትን መናድ
4. በአደባባይ የሰው ልጅ መግደል
5. ጅምላ ጭፍጨፋ
6. ሽብርተኝነት
7. ታሪክ አርካሽነት
8. ማምከን
9. ማቀንጨር
10. የትምህርት ጥራት ድቀት
12. የሞራል ውድቀት
13. ሀገር ጠልነት
14. የሀይማኖት ክብርን ማራከስ
15. አምባገነንነትና ጠቅላይ አግላይነት
16. ህገወጥ የሰውና የመሣሪያ ዝውውር
17. በሰው ልጅ መነገድ
18. ማፈናቀል
19. የሪፖርት (ዘገባ) ውሸት
የቅጥፈት ዶኩመንተሪ
20. የታላላቆችን ክብር ማዋረድ
21. የከፋ የአፓርታይድ ሥርአት
22. በተለያዩ መንገዶች ማሰቃየት፦
ቶርቸር (ገልብጦ ከመግረፍ ጀምሮ)
ጥፍር መንቀል
ብልት ላይ ኮዳ ማንጠልጠል
በመርዝ አሰቃይቶ መግደል
ማህፀን ውስጥ ብረት መክተት
ብልት ውስጥ ብረት መክተት
እግር መቁረጥ
ዐይን ማፍረጥ
ጨለማ ክፍል ማሰር
ከአውሬ ጋር ማሰር
ሴቶችንና ወንዶችን አስሮ መድፈር
በሀሰት ስም ማጥፋት መወንጀል…
23. ከሠፈርና ከቀዬ በመንቀል
በምትኩ የትህነግ አባላትን ማስፈር
24. አእምሮን በመንካት ማሳበድ
ታላላቅ ሰዎችን ራቁታቸውን ደፍሮ
ቪዲዮ በመቅረፅ ሰለባ ማድረግ
25. ከሥራ በማፈናቀል ማሰቃየት
(መገለጫ ፕሮፌሰር ምንዳርአለው)
26. እስከመጨረሻው መሰወር
(ማስረጃ መሪጌታ እንደሥራው አግማሴ)
27. በጠራራ ፀሐይ ህዝብን መፍጀት
(ለምሳሌ፦ ባህርዳር ጎንደር አምቦ ሞያሌ…)
28. ይፋዊ አሰቃቂ አገዳደል
(ማሳያ፦ አሰፋ ማሩ፣ ኤቢሳ አዱኛ…)
29. ህዝብን ወይም ቡድንን
በጅምላ ፈርጆ መስደብና ማዋረድ
(ለማስረገጥ፦ ትምክህተኛ ጠባብ
የስብእና መሸርሸር ያለበት
የጎዳና ላይ ነውጠኞች
አደገኛ ቦዘኔዎች ዋልጌዎች
የቀለም አብዮተኞች
የሻዕቢያ ተላላኪዎች
ፀረሰላም ፀረ ልማት ፀረ ዴሞክራሲ ፀር…
አሸባሪዎች (ኡስታዞችንና ገዳማውያንን
ጭምር…)
30. ሀገርን መጥላት፣ ሰንደቅን ማዋረድ፣
ኢትዮጵያን የመሰለ ስምን ለመጥራት መፀየፍ
በአጠቃላይ ከ1983 – 2010 ኢትዮጵያ በከፋ ጨለማ የተዋጠችበት የውርደት ዘመን ሆኖ አልፏል።
ዛሬ ከምናያቸው 90እጅ ምስቅልቅሎች ጀርባ ወያኔ ትህነግ አለች። ተላላኪዎች ቢጠፉ፤ ሌላ ከሀዲ ተላላኪ ይፈጠራል። ወያኔ አልሞተችም አፈር በልታ ለመነሳት ሁሉንም መንገድ እየተጠቀመች ነው።
ሞኝ አይደለሁም ሥሩና ግንዱ እያለ ቅርንጫፍ ላይ አልንጠለጠልም።
ጊዜያዊ ተላላኪዎችን እመኑኝ አረፋ እናስደፍቃቸዋለን። ከላይ የሚንሳፈፈውን ስልባቦት መጥረግ አያስቸግርም።
መርዙን ከነሰንኮፉ ለመንቀል አንድ ሆነን እንቁም!!!
ሰፋ አድርገን ስናቀርበው ደግሞ ይህንን ይመስላል፦
ግንቦት 20ን በማስመልከት የተፃፈ ቁልፍ ንፅፅር
ደርግ Dergue Vs. Woyane ትህነግ
*
የግንቦት 20 አድናቂዎች ትህነግ ወያኔንና ደርግን አነፃፅረው ትህነግን ሲያሞካሹ?!
(በነፃ ህሊና ነፃ ፍርድ ስጡ!)
*
አቋማቸው በየወቅቱ የሚዋዥቀውና በምንዳና በአንሶላ የሚፅፉ የምናውቃቸው ብዕረ መልካሞች መንጋውን እንዳሻቸው ይሰግሩታል። የታሪክንም ፍርድ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ እያሉ ያዛባሉና እውነተኛ ህሊና ያለው ፍርድ እንዲሰጥ የሚከተለውን ማነፃፀሪያ አስቀመጥን። መቼም የ27 ዓመቱ ፍሬ ሀሳብን በተሻለ ሀሳብ እንዳይሞግት ሆኖ ስለተቀረፀ በመሳደብ እንጂ በዕውቀት አያምንምና መከራከሪያ ያለው ወዲህ ይበልና እንሟገት?
*
የወንጀሎች አፈፃፀም፦
1. ግብረሰዶማዊነት
ሰዶሞና ገሞራን ያጠፋቸውና በእስልምናም ሆነ ክርስትና (በመላው የሰው ልጅ ሀይማኖትና ልቅ ባልሆነ ሞራል አጥብቆ የሚወገዘው) የጌዮችና ሌዝቢያኖች ዘር የማያስቀጥል ነውር በማን ተፈፀመ?!
በደርግ ዘመን ወሬውን እንኳ የማናውቀው ግብረሰዶማዊነት፤ በመዋቅርና በዕቅድ በተደራጀ አኳኋን፤ በማረሚያ ቤት ጭምር የተስፋፋው በወያኔ ነው = ያውም አስገድዶ በመድፈር
(ፖሊስ ጣቢያ ከሚቀርቡ የአስገድዶ መድፈር ሪፖርቶች የማይናቅ ቁጥር ያለው ግብረሰዶማዊነት መመዝገቡን ለማረጋገጥ የፖሊስ ምርመራ ሪከርዶችን ማየቱ ይበቃል።)
*
2. የተናጠልና የተደራጀ ዝርፊያ
ደርግ እንኳን በቡድን የተደራጀ ዝርፊያ ይቅርና በተናጠልም ፀረ-ሌባ እንደነበር የምንክድ አይመስለኝም። መንግሥቱ ኃይለማርያም ፀረሌባ አቋሙ የማያወላዳ ስለመሆኑ፤ ወጣቶች ወላጆቻችሁን ብቻ ብትጠይቁ ይገልፁላችኋል። በወቅቱ ለአቅመ ፖለቲካ የደረስን የማንሰውረው እውነት ነው። ኮንትራባንድ ሀገሬን እንዴት ጋጣት?
የገንዘብ የከፋ ዝውውር
ግልፅ የየመሥሪያ ቤት ሺህ አይነት ሌብነት
3. ከፋፋይነት ጎሰኝነት = አንድነትን መናድ
ደርግ ምንም እንኳ በዋናነት ከብሔረሰብ አንፃር ቁልፍ በሆኑት የኦሮሞ ተወላጆች፦ ተፈሪ በንቲ፣ መንግሥቱ ኃይለማርያም ወልዴ አያና፣ ደበላ ዲንሳና መሰሎቻቸው የሚዘወር ቢሆንም፤ በከፋፋይነት ፈፅሞ አይታማም። ወያኔ ትህነግ፦
ኦሮሞና አማራን፣ አማራውን እርስበርሱ፣ ኦሮሞውን እርስበርስ፣ ሶማሊና ኦሮሞን… በደምሳሳው እስከ ጎሳ ድረስ ወርዶ ሲያናክስ እንደነበር Short Memory ያለው ካልሆነ በስተቀር፤ ዛሬም ለሚፈሰው ደምና፤ ቀጥሮ ባሰማራቸው የፖለቲካ በጥባጮች መሪ ተዋናዩ ወያኔ/ትህነግ ነው።
የሞያሌ፣ ጉጂ ዞን፣ ቦረና ዞን… አወቃቀር በራሱ ሆነ ተብሎ የኦሮሞውን አንድነት ለማላላት በእቅድ የተፈፀመ ነው። መርዙ እነሆ ዛሬም የጥላቻ ምንጭ ሆኖ ቀጥሏል።
ለመሆኑ በሚሊዮን ኦሮሞ ከሶማሊ የተፈናቀለው በማን ጊዜ ነው?! በወያኔ አይደለምን?!
አማራውን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት የተዘጋጀውን ማኒፌስቶ መካድ የሚችለው ማነው?!
በእቅድ አማራው በደኖ ሂንቁፍቱ ወተር ኦሮሚያ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ጋምቤላ ሶማሊ… የቱም ሥፍራ ሀገሩ እንዳይመስለው መሠራቱን፤ በአኀዝ አስደግፎ መተንተን ይቻላል።
4. በአደባባይ የሰው ልጅ መግደል
በማይካድ መልክ ደርግ ከሁለት ዓመት ላልበለጠ ጊዜ በጠራራ ፀሐይ፦ ለነጭ ሽብር ምላሽ፣ ሶሻሊስታዊ ተቀናቃኞችን የመግደል ባህርይ እና ፋሺስትነቱ ተደምሮ አንድ ትውልድ ገድሏል።
ይሁንና የወያኔ 27 ዓመታት ያላባራ ግድያ እጅግ የረቀቀና የሚያሳቅቅ ነበር።
4.1 የኢሬቻ ፍጅት The Iretcha Massacre እንዴት ይገለፃል? 800 ወገን
4.2 አምቦ 27 ዓመት የፈሰሰው ደም
4.3 የባህርዳር 86 ንፁሃን የስናይፐር ጭፍጨፋ
4.4 የሰኔ 1/ 1997 የአዲስ አበባ ፍጅት
4.5 የሞያሌ እልቂት፣ የሻሸመኔ፣ ነቀምት፣ ሻኪሶ፣ ጎንደር፣ ወልዲያ…
4.6 እስር ቤቶች ውስጥ ሰውን እንደጧፍ ማንደድ
4.7 የአሰፋ ማሩ፣ የኤቢሳ አዱኛ፣ የደምቢ ዶሎ፣ ጨለንቆ፣ የመስጊድ ውስጥ ጭፍጨፋዎች… ሺህ ምንተሺህ የስናይፐር ጭፍጨፋዎች…
5. ጅምላ ጭፍጨፋ
ደርግ ኢህአፓ መኢሶን ኢዲዩ… ብሎ በፓርቲ አባልነት ጨፍጭፏል።
በወያኔ አማራው በማንነቱ ብቻ በሚሊዮኖች ጅምላ ጭፍጨፋ ተፈፅሞበታል። ኦሮሞው በተመሳሳይ
ኮንሶ ወላይታ ሶማሊ አፋር… ግልፅ የጅምላ ጭፍጨፋን የሚያሟሉ ወንጀሎች ተፈፅመውባቸዋል።
6. ሽብርተኝነት
ለደርግ እየደጋገምን የምንገልፀው፦ ያንንው አንድ ድርጊት በተለያዩ አውዶች አስገብተን ሲሆን፤ ወያኔ ትህነግ/ ህወሓት ግን ሁሉንም በተናጠል፤ ሊያውም ከደርግ በሚያስከነዳ አረመኔያዊ ተግባር ፈፅሟቸዋል።
ከውሸት ዶኩመንተሪ (ፌኩመንተሪ) እንኳ ብንነሳ
6.1 “አዲስ አበባን እንደ ባግዳድ”
የሚል ድራማ ቀርፆ – ከሚኒባስ ታክሲ ጀምሮ ራሱ አፈንድቶ ሽብርተኝነት እንደፈጠረ የዐይን እማኞች አሉ።
6.2 “ጂሀዳዊ ሐረካት”
የሚለው ድራማ፤ የሰላም ሀይማኖት ተከታይ በሆነው በሙስሊሙ ወገኔ የተፈፀመ ሳይሆን፤ የወያኔ ድርሰት ስለመሆኑ ሰለባዎቹ የሉምን?!
6.3 “የሳራ በረሀ ምሥጢር” …
6.4 እንደ ደርግ ዘመን የአንድ ፓርቲ “ምርጫ” ቢሆን ምን ነበረበት?!
ምርጫ ላይኖር በምርጫ ሰበብ ስንት ሽብር ተፈፀመ?!
7. ታሪክ አርካሽነት
ደርግ ታሪክን በመደብ ከፋፍሎ ገዢ መደቡ ላይ ቢያተኩርም ቢያንስ የዘመናት ታሪክን አላዋረደም።
የወያኔ ፍሬዎች ታሪክ ላይ የሠሩትን ደባ…
8. ማምከን
የአማራው ብቻ ቢጠቀስ ይበቃል።
9. ማቀንጨር
በዓለም አንደኛ የሆንነው በወያኔ ጊዜ ነው።
10. የትምህርት ጥራት ድቀት
ትምህርትን ገደለው አይገልፀውም። ከወታደራዊ ባህላዊ ጀነራል እስከ መፃፍና ማንበብ የማይችል ምሩቅ
12. የሞራል ውድቀት
13. ሀገር ጠልነት
14. የሀይማኖት ክብርን ማራከስ
ማነው ሙስሊሙን ሱፊና ሰለፊ እያለ የከፋፈለው?
ማነው መጅሊሱን የሰነጠቀው?
ማነው ስደተኛ ሲኖዶስ የፈጠረው?!
ደርግ ነው እንዴ?! አይደለም ወያኔ ነው።
15. የአፓርታይድ ሥርዓት
በግልፅ ኢትዮጵያ የአድዋ ስብሓት ነጋ እና አሽአ አክሱም ሽረ አድዋ አልነበረቺምን?
ስንት ገበሬ ከአፋር ከጋምቤላ ከኦሮሚያ ከአማራ ተፈናቀለ?
22 ስሙ ለምን ጎላጉል ሆነ?.
ቦሌ መድኃኔዓለም አደባባይ ለምን ኤድናሞል ተባለ?
80 እጅ የአዲስ አበባ ህንፃዎች የማን ናቸው?!
እንዴት?!
የአበባ እርሻዎች ማንን አፈናቅለው ተሠሩ?
የአፋር ማዕድንና ጨው 85እጅ የማን ነበር?!
16. ህገወጥ የሰውና የመሣሪያ ዝውውር
በደርግ ጊዜ ነበረ ወይ?! የለም።
17. በሰው ልጅ መነገድ
በደርግ ጊዜ ነበረ ወይ?! የለም።
18. በተለያዩ መንገዶች ማሰቃየት፦
ቶርቸር (ገልብጦ ከመግረፍ ጀምሮ)
ደርግ 2 ዓመት – ወያኔ 27 ዓመት
ጥፍር መንቀል
በደርግ የለም፤ በወያኔ ኡኡኢኡኡኡኡ
ብልት ላይ ኮዳ ማንጠልጠል
በደርግ የለም፤ በወያኔ እህእ!
በመርዝ አሰቃይቶ መግደል
ደርግ መች መሰሪ ሆነና!
ማህፀን ውስጥ ብረት መክተት
ብልት ውስጥ ብረት መክተት
እግር መቁረጥ
ዐይን ማፍረጥ
ጨለማ ክፍል ማሰር
ከአውሬ ጋር ማሰር
በወያኔ በተጨባጭ ሶማሊ ክልል የታየ
ሴቶችንና ወንዶችን አስሮ መድፈር
ደርግ ሴቶችን፤ ወያኔ ፍናፍንትም ካገኘ አይምርም
በሀሰት ስም ማጥፋት መወንጀል…
19. ከሠፈርና ከቀዬ በመንቀል
የደርግ ለህዝብ የወገነ፤ ልማትን ማዕከል ያደረገ ሠፈራ
የወያኔ፦ ነቅሎ በምትኩ የትህነግ አባላትን ማስፈር
20. አእምሮን በመንካት ማሳበድ
ታላላቅ ሰዎችን ራቁታቸውን ደፍሮ
ቪዲዮ በመቅረፅ ሰለባ ማድረግ
(የወያኔ ብቻ ተግባር ነበር።)
21. ከሥራ በማፈናቀል ማሰቃየት
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 22 መምህራን ጀምሮ ማንነትን መሠረት ያደረገ እስከ አንደኛ ደረጃ መምህራን
21. እስከመጨረሻው መሰወር
(ማስረጃ መሪጌታ እንደሥራው አግማሴ)
የወልቃይት ማንነት ጠያቂዎች
22. ክልል መዝረፍ
ከአፋር ከአማራ እነ ወልቃይት ራያ…
23. ህዝብን ወይም ቡድንን
በጅምላ ፈርጆ መስደብና ማዋረድ
(ለማስረገጥ፦ ትምክህተኛ ጠባብ
የስብእና መሸርሸር ያለበት
የጎዳና ላይ ነውጠኞች
አደገኛ ቦዘኔዎች ዋልጌዎች
የቀለም አብዮተኞች
የሻዕቢያ ተላላኪዎች
ፀረሰላም ፀረ ልማት ፀረ ዴሞክራሲ ፀር…
አሸባሪዎች (ኡስታዞችንና ገዳማውያንን
ጭምር…)
24. ሀገርን መጥላት፣ ሰንደቅን ማዋረድ፣
ኢትዮጵያን የመሰለ ስምን ለመጥራት መፀየፍ
በአጠቃላይ ከ1983 – 2010 ኢትዮጵያ በከፋ ጨለማ የተዋጠችበት የውርደት ዘመን ሆኖ አልፏል።
25. ለምን ተዋጉ?!
ወያነ፦ የትግራይ ሪፐብሊክ ለመገንባት
ደርግ፦ ሀገርን ለማዳን
ማረጋገጫ፦ ተክለብርሃን ወልደአረጋይ
26. ዛሬ የምንበጠበጠው በማነው?!
የመንግሥት መልፈስፈስ እንዳለ ሆኖ፤ ዛሬ ከምናያቸው 90እጅ ምስቅልቅሎች ጀርባ ወያኔ ትህነግ አለች። ተላላኪዎች ቢጠፉ፤ ሌላ ከሀዲ ተላላኪ ይፈጠራል። ማነው ለትምህርት ቤት በተላከ በጀት ሀገር አፍራሽ ኮንፌደራሊስቶች በሀገር በጀት የሚሰበስበው? ወያኔ አልሞተችም አፈር በልታ ለመነሳት ሁሉንም መንገድ እየተጠቀመች ነው።
27. ደርግ 17 ዓመት የተዋጋው ሀገር ሊታደግ ነው። ባድመ ብቻ ያለቀው ወገን በ17 የደርግ ዓመታት አልሞተም። የኢትዮጵያን ሠራዊት የኮንጎ የኮርያ የካራማራ የኦጎባ የቀብሪደሀር… ማነው አዋርዶ የደርግ ሠራዊት ያለው?!
ሞኝ አይደለሁም ሥሩና ግንዱ እያለ ቅርንጫፍ ላይ አልንጠለጠልም።
ጊዜያዊ ተላላኪዎችን እመኑኝ ብንተባበር አረፋ እናስደፍቃቸዋለን። ከላይ የሚንሳፈፈውን ዓላማ የለሽ ሆድአደር ስልባቦት መጥረግ አያስቸግርም።
መርዙን ከነሰንኮፉ ለመንቀል አንድ ሆነን እንቁም!!!
(((((((ዝርዝሩን ከፈለጋችሁ
መራራ እውነት በኢትዮጵያ ታሪክ
በሚለው መፅሐፌ ላይ በጥልቀት ተሰንዷል።))))))
ታየ ቦጋለ አረጋ – ኢልመ ደሱ ኦዳ
ዘነጌሌ ቦረና
ግንቦት 20 ቀን 2012