>
5:13 pm - Wednesday April 19, 8484

ከለጋሾች የሚያገኘው እርዳታ እንጂ የዜጎች ደህንነት የማያሳስበው መንግስት!!!  (ታሪኩ አበራ)

ከለጋሾች የሚያገኘው እርዳታ እንጂ የዜጎች ደህንነት የማያሳስበው መንግስት!!! 

ታሪኩ አበራ

★ መንግሥት የባህል ሐኪሞችን ለምን አፈናቸው ? 
 
 
★ እናታችን ሀኪም አበበች በአገር በቀል እውቀቶች ወረርሽኙን ስለመከላከልም ሆነ ስለ በህላዊ መድኃኒቶች አስመልክቶ አንዳችም ዓይነት መረጃ ለህዝቡ ይፋ እንዳያደርጉ፣ ከመንግስት በተለይም ከሁለቱ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች እገዳ/እገታ? ተደርጎባቸዋል!!!
 
★ ወገኔ ሞት በደጅህ አድብቷል ዝም አትበል!!!
ክፍል አንድ
===========
➤ #መንግሥታችን አገር በቀል እውቀቶችን ከዘመናዊው እውቀት ጋር አቀናጅቶ በከፍተኛ ሥርጭት ላይ የሚገኘውን ወረርሽኝ ለመግታትና በወረርሽኙ የሚጎዱ ዜጎችን በፍጥነት ለመታደግ የጀመረውን መንገድ በማን አስገዳጅነትና በምን ቅድመ ሁኔታዎች እንዳስቆመው በግልፅ ለህዝቡ ማሳወቅ እንዳለበት አምናለሁ።
ለጊዜው እናታችን ሀኪም አበበችን ጨምሮ ሌሎች አንዳንድ የባህል ህክምና/መድኃኒት አዋቂዎች ከሁለቱ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ጋር ያላቸው የትብብር ሥራ ግንኙነት በቂ ባልሆነ ምክንያት እንዲቋረጥ ተደርጓል። በአንዳንድ የባህል ህክምና/መድኃኒት አዋቂዎች በተለይም በእናታችን ሀኪም አበበች እምነት መንግስት አገር በቀል እውቀቶችን ከዘመናዊው የህክምና ግኝቶች ጋር በማስተባበር ህብረተሰቡን በአስቸኳይ ከወረርሽኙ ለመታደግ የጀመረውን እንቅስቃሴ የገታው፣ ኢትዮጵያ ወረርሽኙን ለመከላከል ያስችላታል የተባሉ የገንዘብና የህክምና ቁሳቁስ እርዳታዎች ከውጭ ባለሀብቶች መጉረፍ በጀመሩበት ማግስት ነው።
 መንግሥት በአገር በቀል እውቀቶችና የባህል ህክምና/መድኃኒት ግኝቶች ላይ ተጥሎ የነበረውን ተስፋ ከውጭ ባለሀብቶች በጎረፉ እርዳታዎች ሙሉ በሙሉ እንዲዳፈን አድርጎታል። ወረርሽኙን በአገር በቀል እውቀቶችና የባህል መድኃኒት ግኝቶች ጎን ለጎን ለመከላከል የወጣውን የቅድመ ዝግጅት እቅድ መንግሥት በከፍተኛ መነሳሳት ላይ የነበሩትን ባለሙያዎች ሳያማክርና ሳያወያይ በድንገት ሰርዞታል። ይህም ወረርሽኙን እንደ አገር ለመከላከል የሚያስችሉ ከውጭ ባለሀብቶች የተግተለተሉ እርዳታዎችን ለመቀበል ሲል ብቻ መንግሥት እንደ ቅድመ ክራይቴሪያ እነዚህን የአገር በቀልና የባህላዊ መድኃኒት ግኝቶችን ማዳፈን እንደመረጠ ያለጥርጥር ያሳያል።
የውጭ ባለሀብቶቹም በተከታታይ ለኢትዮጵያ መንግሥት ያጎረፉትን እርዳታ እነዚህን መሰል በአገር በቀል እውቀቶችና የባህል መድኃኒት ግኝቶች መነሻነት በአገር ውስጥ ወረርሽኙን ለመከላከል የሚከናወኑ ፕሮጀክቶችን ማስቆም ዋናው ግባቸው የማይሆንበት ምንም መንገድ የለም። ለመንግሥትም አዋጭው መንገድ የትኛው ነው? የተባለ እንደሆን ያለምንም ማወላዳት ከውጭ የጎረፈውን እርዳታ ለመቀበል በአገር በቀል እውቀት ላይ የተመሠረቱ እንቅስቃሴዎችን ማስቆም ነው።
በአገር በቀል እውቀቶችና የባህል ህክምና/መድኃኒቶች ወረርሽኙን ለመከላከል ርብርብ ማድረግ ህዝብን እንጂ ለመንግሥት የሚያስገኘው አንዳችም ጥቅምም ሆነ ፖለቲካዊ ትርፍ የለም። እንደውም እንዲህ በመሰለው የአገር በቀል መፍትሔ ወረርሽኙን ለመከላከልና ህዝቡን ለመታደግ መሞከር የዓለም መንግሥታትንና ባለሀብቶችን ሊያስከፋ ይችላል። በመንግሥትም ላይ ጥርስ ነክሰው የማዕቀብና ክልከላ ናዳ ሊያወርዱበት እንደሚችሉ ጥርጥር የለውም።
 በተጨማሪም ከውጭ መንግሥታትና ባለሀብቶች የሚገኙት ብዙ ዓይነት እርዳታዎች በተለይ የሚሊዮን ዶለር እርዳታዎች ለዝርፊያ አመች ሁኔታን የሚፈጥሩ በመሆናቸው በመንግሥት በኩል ተመራጭ የማይደረጉበት ሁኔታ የለም። በመሆኑም በአገር በቀል እውቀቶችና የባህል ህክምና ግኝቶች ወረርሽኙን ለመከላከል የተጀመረው ርብርብ “መንግሥት ወረርሽኙን በሚገባ ለመቆጣጠር በሚያስችል በቂ አቅም ላይ ይገኛል” በሚል ምክንያት እንዲደናቀፍ ተደርጓል። ለህዝብ ጥቅምና ለቀጣይ የአገር መፃኢ ዕድል ሳይሆን ከፖለቲካዊ ትርፎችና ጥቅሞች አንፃር አገራችን ከውጭ መንግሥታትና ባለሀብቶች በሚጎረፉላት እርዳታዎች ብቻ ተወስና ወረርሽኙን ለመከላከል ትገደዳለች ማለት ነው። የትኛው የመከላከያ መፍትሔ ይሻላል? የተባለም እንደሆን መልሱ ፖለቲካዊ ሆኖ ይቆያል።
➤ [እጃችንን] አጣጥፈን እስከምናልቅ መቀመጥ እንደሌለብን ይሰማኛል። በቀጣዮቹ ጥቂት ጊዜአት በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥር እንደማጠናከሪያ ሆኖ ይህ የባህል ህክምና/መድኃኒት ጉዳይ ከነአካቴው ከሌሎች ክልከላዎች ሁሉ በሚልቅ መልኩ መታገዱ የማይቀር ይሆናል። ህዝቡ እነዚህን ጉዳዮች እያነሳ መወያየት ከጀመረና መፍትሔ መለዋወጥ ከቻለ ከውጭ የጎረፈው የገንዘብና የህክምና ቁሳቁስ እርዳታ አፈር ሊበላው ይችላል።
በሂደት መንግሥታችን በውጭ መንግሥታት ፊት ያለውን እምነትና ተቀባይነት ጥላሸት ሊቀባበት እንዲሁም በሥልጣን የመቆየቱን ዕድል ሊያጠብበት ይችላል። ያ ከመሆኑ በፊት ግን መንግሥት እጅግ ጥብቅ የሆኑ እገዳዎችንና የክልከላ አዋጆችን በማውጣት በባህላዊ መንገድ ወረርሽኙን የመከላከል ተስፋዎችን በጥቂት ጊዜ ውስጥ ያመክናቸዋል።
ስለባህላዊ የህክምናና የመድኃኒት ጉዳዮች አስመልክቶም በምንም ዓይነት መንገድ ውይይት ማድረግ(ትንፍሽ ማለትም) #ሊያስገድል በሚችል ቅጣት መታጠሩ እንደማይቀር እወቁ። ይህ ጉዳይ ለብዙ ሰዎች የፖለቲካ አሊያም ለሥልጣን ጥማት የሚሰነዘር ሃሳብ ሊመስላቸው ይችላል። ግን ጥያቄው በፍፁም የዶ/ር ዐቢይን ወንበር ከመፈለግ ብሎም የሌሎችን የፖለቲካ ኃይሎች ፍላጎት ለማንፀባረቅ የተሰነዘረ አለመሆኑን ሁሉም ሰው እንዲረዳልኝ እፈልጋለሁ፤ እለምናለሁም። መጭው የመንግሥት ትልቁ እርምጃም ሆነ ዓላማም ይኸው ነው። ደርሶም በዐይናችሁ ማየታችሁ ስለማይቀር መከራከራችን ጉንጭ ማልፋት ይሆናልና አልፈዋለሁ። ዞሮ ዞሮ እዚህ ጋር እንዲሰመርበት የተፈለገው ሃሳብ ጉዳዩን ለፖለቲካዊ ትርፍ ብየ እንዳነሳሁት አድርጋችሁ እንዳትቆጥሩብኝ ማሳሰቤን የሚመለከት ነው። እንዲህ ያለው አረዳድ ከቶም የሚያግባባን አይሆንምና!
➤ #እናታችን ሀኪም አበበች በአገር በቀል እውቀቶች ወረርሽኙን ስለመከላከልም ሆነ ስለ በህላዊ መድኃኒቶች አስመልክቶ አንዳችም ዓይነት መረጃ ለህዝቡ ይፋ እንዳያደርጉ፣ ከመንግስት በተለይም ከሁለቱ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ጋር ወረርሽኙን በአገር በቀል እውቀቶች ለመከላከል ስለጀመሩት እንቅስቃሴ በሚመለከት ሃሳብ እንዳይሰነዝሩ #እገዳ/#እገታ? ተደርጎባቸዋል። እናታችን ሀኪም አበበችን ፈልጓቸው! አታገኟቸውም።
➤ #የግል #ሚዲያ #ባለቤቶች እንደ አገር በዚህ ጊዜ የተደቀነብንን ፈተናና መከራ መወጣት-ማለፍም እንድንችል ኃላፊነታችሁን ተወጡ!!! የወረርሽኙን ከፍተኛ ሥርጭት በቁጥር፣ በቦታ፣ በሁኔታዎች አገናዝቦ ለህብረተሰቡ ማስረዳት፣ መረጃዎችን በየወቅቱ ማድረስ በእርግጥም ጥሩ ተግባር ነው። የሚዲያም ኃላፊነት ነው።
ህብረተሰቡ ራሱን ከወረርሽኙ መከላከል ስለሚችልባቸው ጉዳዮች መረጃዎችን ቶሎ ቶሎ በማድረሳችሁ በእርግጥም ልትደነቁ እንጂ ልትወቀሱ እንደማይገባ አምናለሁ። ግን እስከመቼ በዚህ ተግባር ብቻ ተወስናችሁ ትቀጥላላችሁ? የቫይረሱ ሥርጭት በቁጥር 10 በደረሰበት ወቅትና 100ዎችን እያለፈ በመጣበት ወቅት የሚዲያ እንቅስቃሴና ተግባራችሁ አንድ ዓይነት ነው? ያው ነው? ከወረርሽኙ ከፍተኛ ሥርጭትና መስፋፋት አንፃር የሚዲያ ኃላፊነታችሁ #መክበድ የለበትም? #መምረርስ የለበትም? እና የግል ሚዲያዎች ያን እያደረጋችሁ ነው? እና ምን ይሻላል? ፍጠኑ!! የአገር በቀል እውቀቶችና የባህል ህክምና/መድኃኒቶችን ህብረተሰቡ ተጠቅሞ ከማለቅ እንዲድን ተረባረቡ!! እናታችን ሀኪም አበበችና የመሳሰሉትን የባህል ህክምናና መድኃኒት አዋቂዎችን የየዕለት ጉዳያችሁ አድርጓቸው!! እነዚህን ባለሙያዎች እያደናችሁ በማቅረብና የዘወትር አጀንዳችሁ በማድረግ ከህብረተሰቡ ጋር በጊዜ አገናኟቸው!! የወረርሽኙ መከላከያና መፈወሻ መድኃኒቶች አሉ!!!! ህዝቡን መድኃኒቶቹ ጋር አገናኙት!!! ድፈሩ!!! ቁረጡ!!! ወስኑ!!! ወገናችሁን የማዳን ቀዳሚው ኃላፊነትና ተግባር የእናንተ እንደሆነ እወቁ!!! ነገም በታሪክ የመጀመሪያ ተወቃሾች እናንተው እንደሆናችሁ ተረዱ!!!
➤ #አሁንም የጠበበ ጥቂት ጊዜ አለን። እንጠቀምበት። ከአምላካችን በታች እንደ ሌሎች ህዝቦች የሚጠብቀንና የሚቆምልን መንግሥት የለንም። ለራሳችን ያለነው ራሳችን ብቻ ነን። አምነን እንፀልይ/ዱዓ እናድርግ!! ፈጣሪ የሰጠንን መድኃኒቶች እንጠቀምባቸው ዘንድ መገለጥን ይስጠን!! ያግባባን!! ያረዳዳን!! ክፉውን ሁሉ ያርቅልን!!!
ምንጭ ፦ የሐኪም አበበች ሺፈራው ዕውቀት ተረካቢዎች ገጽ የተገኘ።
Filed in: Amharic