>
12:04 pm - Sunday December 4, 2022

"ባለስልጣናቱን መቀመጫ አሳጡዋቸው"  ፕ/ት ባራክ ኦባማ (ታምሩ ገዳ/ህብር ራዲዮ)

ባለስልጣናቱን መቀመጫ አሳጡዋቸው

ፕ/ት ባራክ ኦባማ

 የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የአገሪቱ የፖሊስ መዋቅር እንዲለወጥ ጠየቁ፣ተቃዎሚዎችም በስልጣን ላይ ባሉ ባለስልጣናት ላይ ሰላማዉ እና ህጋዊ ጫና እንዲፈጥሩ ጥሪ አቀረቡ።
በሚኒሶታ ግዛት ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፎሎይድ በነጭ ፖሊስ እጅ መግደል እንደ ጥቁር አሜሪካዊ አባት እና እንደ ቀድሞው የአገሪቱ መሪ ልባቸው የተነካው  ባራክ ኦባማ ዛሬ እሮብ በማህበራዊ መረብ አማካኝነት ለመጀመሪያ ጊዜ  ባስተላለፉት  ቀጥተኛ መልክታቸው” በአገሩቱ የፖሊስ መዋቅር ይቀየር ዘንድ ለሚወተውቱ ተቃዋሚዎች ይህ አጋጣሚ   ከፖለቲካዊ አተያየት አኳያ መልካም አጋጣሚ ነው”ሲሉ ለሰማዊ ተቃዎሚዎች ምክራቸውን ሰጥተዋል።
የመጀመሪያው ጥቁር አሜሪካዊ ፕሬዝዳንት በመሆን  ለስምንት አመታት ያገለገሉት  እና ለፕ/ት ትራምፕ ቦታውን የለቀቁት ኦባማ” እውነተኛ ለውጥ እንዲመጣ የምንሻ ከሆነ  ችግሮችን  በመንቀስ፣ በስልጣን ላይ የሚገኙ ባለስልጣናትን መቆሚያ እና መቀመጫ በማሳጣት ህግ እና ስርአትን ማክበርን ሳንዘነጋ ተቋማዊ ለውጦችን ማምጣት ይኖርብናል” ብለዋል።
ቀደም ሲል የፕሬዜዳንት ትራምፕ አስተዳደር በኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ዙሪያ የወሰደው እርምጃን የተቃወሙት ባራክ ኦባማ  የቆዳቸው ቀለም ለጠቆረ (ኮሎርድ) በስጡት ምክር”አዎ እናንተ ዋጋ  አላችሁ፣ህይወታችሁም ዋጋ አለው፣ህልማችሁም ዋጋ እንዳለው ልገልጽላችሁ እወዳለሁ ሲሉ መክረዋል።
እንደ ባራክ ኦባማ ሁለ በምድረ አሜሪካ እየተካሄደ ያለው ዘረኝነት እና ኢ -ፍትሃዊ ጭቆና  እንዲህም የጆርጅ አሟሟት ያስቆጣቸው የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዜዳንቶች መልእክት አስተላልፈዋል። ሰላሳ ዘጠነኛው የአሜሪካ ፕ/ት የሆኑት ዲሞክርቱ ጂሚ ካርተር “እንደ ህዝቡ መልካም የሆነ አስተዳደር ያስፈልገናል፣እንደ ነጭ  እና ከደቡባዉ የአሜሪካ ግዛት(ጆርጂያ) የመጣ ነጭ አሜሪካዊ የዘር ምድሎውን እና መገለሉን ጠንቅቄ አውቀዋለሁ፣በስልጣን ላይ ያላችሁ እባካችሁ ከተገፉት ጋር ቁሙ”ሱሉ ጥሩ አቅርበዋል።
በጥቁር አሜሪካዉው ጆርጅ ፍሎይድ አሟምት ልባቸው ክፈኛ የተነካው የቀድሞው የአሜሪካ ፕ/ት ቢል ክሊንተን “የጆርጅ አሟሟት  ለማንኛውም የሰው ልጅ የማይገባ ነው ።የቆዳህ ቀለምህ ቢነጣ እንደዚያ አይነት አሟሟት አይጠብቅህም። የሰው ልጆች ህይወት በቆዳቸው ቀለም ሲመዘን በእጅጉ ያሳዝናል፣ ለመሆኑ ጆርጅ ነጭ ቢሆን ኖሮ እጁ በካቴና ታስሮ ፣በደረቱ እንዲተኛ ተደርጎ በህይወት ይኖር ይሆን?” በማለት ጠይቀዋል።
ሪፖብሊካኑ የቀድሞው ፕ/ት ጆርጅ ቡሽ በበኩላቸው  ማክስኞ እለት ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጡት አስተያየት”  እኛ አሜሪካኖች  የውድቀታችን መንስኤን በጋራ ልንመረምረው ይገባናል፣አሁን ጊዜው ገለጻ የምናዥጎደጉድበት ጊዜ ሳይሆን ፣በጥሞና የምናዳምጥበት ጊዜ ሊሆን ይገባል፣ጆርጅ  ፎይልድ እንዲህ ታፍኖ ሲገደል ስናይ እኔም ሆንኩ ባለቤቴ ሎራ  በእጅጉ አዝንናል፣የታፈነው ጆርጅ ብቻ ሳይሆን አገራችንም ጭምር ነው”በማለት የፍትህ ስርዓቱ እንዲቀየር ጠይቀዋል።
ሰሞኑን  በኃላፊነት ካሉት ሆነ ከጡረኛ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት ተቃውሞ  የገጠማቸው ፕ/ት  ትራምፕ”ጥቁር አሜሪካኖችን ከድህነት እና ከስራአጥነት በማላቀቅ፣ለጥቁሮች በመቆም   ከሁሉም የአሜሪካ መሪዎች ተወዳዳሪ የለኝም”በማለት በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል ።
Filed in: Amharic