>

የብርሃነመስቀል ሙሾ እና ለመባረሩ እውነታው!!! (ሙክታሮቪች)

የብርሃነመስቀል ሙሾ እና ለመባረሩ እውነታው!!!

(ሙክታሮቪች)

ብርሃነ መስቀል አበበ ሰኚ ተቃውሞ ሰልፍ እየጠራ መሆኑን አስመልክቶ ይህን ለመባረር ያበቃውን ሚስጢር አውጥቼ የነበረውን ልድገመው።
የ ብርሃነመስቀል አበበ ሰኚን ረጅም ሙሾ አነበብኩ። በጣም ነው የገረመኝ። በአሜሪካ በኢትዮጵያ ኢንባሲ የሌስአንጀለስ ቆንፅላ ፅ/ቤት ሀላፊ ነበረ። የአሜሪካ ዜግነት አለው። ቀድሞም የአሜሪካ ዜግነት እያለው በእንደዚህ ያለ የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስጠበቅ ወሳኝ ቦታ መሾሙ ስህተት ነበረ። በዚህ መንግስት መወቀስ አለበት። ሆኖም ዘግይቶም ቢሆን መንግስት ስህተቱን ማረሙ ይበል የሚያሰኝ ነው።
ስለብርሃነመስቀል  ከቦታው መነሳት ስረ ምክንያት
እኔ የሰማሁት የአሜሪካ ዜግነትህን መልሰህ ወደ ኢትዮጵያዊ ዜግነት መልስ ተብሎ የጊዜ ገደብ ተሰጠው። ተጠበቀ። ማቄን ጨርቄን እያለ ሳይመልስ ቀረ። ከቦታው ተነሳ።
በኢትየጵያ ኢንባሲ በውዷ ከተማ ሎስ አንጀለስ ለሀገሪቱ ጥብቅና ቆሞ የኢትዮጵያን ጉዳይ አደራ የተሰጠው ሰው፣ እሱ ግን የጥብቅናውን ስራ እያሯሯጠ በህዝብ ሀብት የራሱን ጥቅም ሲያሳድድ ነበረ።
በነገራችን ላይ
ዶክተር አይደለም። የህግ ዲግሪ JD Juris Doctor ለህግ የመጀመሪያ ዲግሪ የሚሰጥ ስያሜ ነው። Phd አልዘም፣ ሀኪምም አይደለም።
አሜሪካ ለግብፅ ማድላቷን ተከትሎ የቆንስላው ሚና ማነስ እና መመንመን አሳሳቢ ሆነ።
የአሜሪካ ዜግነቱም ለዚህ አስተዋፅኦ ሳያደርግ አይቀርም ተብሎ የአሜሪካ ዜግነትህን መልሰህ የኢትዮጵያን ፓስፖርት ውሰድ ተባለ። እምቢኝ አለ። ተባረረ።
ታሪኩ ይሄው ነው። አለቀ።
አሁን ጥቅሙ ሲጎድልበት የተቃውሞ ዘመቻ ጀመረ። ሰልፍ እየጠራ ነው።
አንድ ሰው የአሜሪካን ዜግነት ሲቀበል ቃለ መሀላ ይፈፅማል። Naturalization Oath of Allegiance ይባላል።
ቀኝ እጁን ከፍ አድርጎ። እየተነበበለት፣ የተነበበለትን እየደገመ መሃላ ይገባል።
መሃላው ምን ምን ያካትታል?
ጉዱ እዚህ ጋ ነው!
የመሀላው ይዘት የሚከተለው ነው።
🇺🇸🇺🇸🇺🇸
Naturalization Oath of Allegiance to the United States of America
“I hereby declare, on oath, that I absolutely and entirely renounce and abjure all allegiance and fidelity to any foreign prince, potentate, state, or sovereignty, of whom or which I have heretofore been a subject or citizen; that I will support and defend the Constitution and laws of the United States of America against all enemies, foreign and domestic; that I will bear true faith and allegiance to the same; that I will bear arms on behalf of the United States when required by the law; that I will perform noncombatant service in the Armed Forces of the United States when required by the law; that I will perform work of national importance under civilian direction when required by the law; and that I take this obligation freely, without any mental reservation or purpose of evasion; so help me God.”
Section 337(a) in the Immigration and Nationality Act (INA) መመልከት በቂ ነው። 🇺🇸🇺🇸🇺🇸
ተመልከቱ በአላህ።
እንዲህ የማለ ሰው ከቶ እንዴት የኢትዮጵያን ጥቅም ያስከብራል? በኢትዮጵያ እና በግብፅ የአባይ ድርድር አሜሪካ የያዘችው አሳፋሪ አቋምን በምን ሞራል ሽንጡን ገትሮ ለኢትዮጵያ ሊከራከር ይችላል?
I absolutely and entirely renounce and abjure all allegiance and fidelity to any foreign prince, potentate, state, or sovereignty, of whom or which I have heretofore been a subject or citizen;
እንዴ?!
በፍፁምነት እና በአጠቀላይ ለሌላ ሀገር የነበረኝን ታማኝነት እና አለኝታነትን ቁጭ አድርግ ተብለህ ቁጭ አድርገህ ስታበቃ በኢትዮጵያ ቆንፅላ እንሹምህ ሲባል መኃላህ ትዝ ብሎህ ኸረ ተዉ ብለህ አታቅማማም? ከተነቃም (እንደ አራዳ “ከተነቃ አይገደድም” ብለህ ላሽ ትላለህ እንጂ) ውልቅ ትላለህ እንጂ ሞሾ እና ለቅሶ ታወርዳለህ?
አሃዳዊያን ስሜን አጠፉት ወዮ ወዮ
እኔ ተራማጅ ነኝ ወዮ ወዮ
ለውጡ ተቀልብሷል ወዮ ወዮ
በዚህ አካሄዳቸው ሀገር ትፈርሳለች ወዮ ወዮ
ኤጭ!
አንተ መልስ የተባለከውን የሌላ ሀገር ዜግነት ባለመመለስህ ከሹመት ስለተነሳህ እንዴት ኢትዮጵያ ትፈርሳለች?
አናትህ ይፍረስ!  😀
በነገራችን ላይ ዜግነት መቀየር ምንም ማለት አይደለም። በወረቀት የሰው በደም የኛ ናቸው የሚለው የአብዱኪያር ዜማ ሀሳቤን ይገልፃል እና አላብራራውም። ሌላው አንዳንዱ በወያኔ ስርዓት ፓስፖርታቸው ስላልታደሰላቸው ተገደው የገቡበት እንደሆነ አይጠፋኝም። ስርዓት ሲቀየር ካልመለስክ፣ መልስ ተብለህ ካልመለስክ ንካው መባለህ ለምን ያምሃል?
ሆኖም፣ የውጭ ዜግነት ወስዴ በመንግስት ወሳኝ ፖለቲካዊ ሹመት መሾም አይቻልም። ለውጪ ሀገራት ዜጎች አይፈቀድም። ለሌላ ሀገር መኃላ የገባ፣ የመሀላውም ይዘት “ለኢትዮጵያ ያለኝን ታማኝነት አስቀምጬ ለአሜሪካ ልሟገት፣ ልዋጋላት፣ ላገለግላት” የሚል ከሆነ፣ በቃ ቆንፅላ ውስጥ ውሳኔ እየሰጠ እና እየፈረመ መቀጠል አይችልም። ከላስ!
ይህ ከብሄር እና ቋንቋ ጋር ምንም አያገናኘውም።
እርግጥ ነው።
መንግስት አድቫይዘር ሊያደርገው ይችላል። ምክር መለገስ እና ውሳኔ መስጠት ይለያያሉ።
እንኳን የሀገር ልጅ ነጭንም በአማካሪነት መቅጠር ይቻላል።
የኢትዮጵያ እግርኳስ ብሄራዊ ቡድንን ውጭ ዜጋ መቅጠር እንደማለት ነው። የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር መሆን ግን አይቻልም።
ውጪ ዜጋ ሆኖ እንዲህ አይነት ሹመት ቦታ የያዘ ሰው ካለ ከነመረጃው አቀብሉኝ። ዘመቻ እንከፍትበታለን።
ብርሃነመስቀል ግን ሲታወቅበት በኦሮሞነት ማልያ ይጫወታል። ተቃውሞ ሰልፍ ይጠራል። ወጣቶች ለእሱ ጥቅም አሳዳጅነት እንዲሞቱ ይጠራል።
ነፍጠኛ፣ አሀዳዊያን፣ የድሮ ስርዓት እያለ ይከፋፍላል።
ደረጃ ገረፋ ቱሉ እና ጃዋርም ያማሙቁለታል።
የአይጥ ምስክር ድንቢጥ አሉ ሂሂሂ 😀
ዘር በል ወዲያ ዱቄት አለ ዮኒ ማኛ …. (የሱ ልጅን ሳቅ እዚህ ጋ ልዋሰው )
(በነገራችን ላይ ጃዋርም ይህችን መኃላ ምሏል! መልስ ሲባል ለቅሶ )
Filed in: Amharic