>
5:13 pm - Tuesday April 19, 4078

የጆርጅ ፍሎይድ ዘረኛ ግድያ የአለምን ህዝቦች ለጸረ ዘረኝነት አመጽ ያስነሳ!!!  (አስገደ ገብረስላሴ - መቐለ፤) 

የጆርጅ ፍሎይድ ዘረኛ ግድያ የአለምን ህዝቦች ለጸረ ዘረኝነት አመጽ ያስነሳ!!!

 አስገደ ገብረስላሴ – መቐለ ፤

የአለም ህዝቦች አንድ ያደረገ  ክቡር ሂወቱ በመክፈል አንድነት ያስተማረ የጆርጅ ፍሎይድ መሰዋእት ነፍሱ  በሰማአት ቦታ በክብር ያኑራት ! ! ! 
በ U  S A  አመሪካ አንድ ጥቂር አመሪካዊ ጆርጅ  ፍሎይድ የተባለው  በዘረኞች  ነጮች ፓሊሶች   በግፍ  ሲገደል የአመሪካ ህዝብ ግን የንቃተ ህሊና ከፍታ  እጅጉን የመጠቀ በመሆኑ የዜጎች ( የህዝቦች ) የሰብአዊ መብት  ክብር የሚገባቸው በመሆኑ በአንድ ጫፍ የአመሪካ ግዛቶች ሞንስታብል ግዛት በግፍ ስለተገደለ ይህ ጆርጅ ፍሎይድ የሚባለው ጥቁር አመሪካዊ በመገደሉ የአመሪካ 54 ግዛቶች ነዋሪ ህዝብ ነጭ ፣ቀይ ፣ጥቁር ፣አፍሪካዊ ፣አውሮፓዊ ፣ ኢሲያዊ ፣ ከናዳዊ ፣ አውስትራሊያዊ የአመሪካ ጥቁር ዜገች ፣ሀይማኖት ፣ የመንግስት ፣የኩባንያዎ ሰራቶኞች ፣ጾታ ሳይለያዩ በአንድነት ስለሰብአዊ መብት ጥሰት ፣ወግነው አደባባይ በመውጣት  የኮቪድ 19 አሸኳይ አዋጅ ሳያግዳቸው ልክ እንደ አንድሰው አንድ ልብ ሆነው በመላው የአመሪካ ስቴቶች እነሆ 8 ቀኑን ያስቆጠረ አመጽ ተቀጣጥሎ ይገኛል ።የሰብአዊ መብት ተጥሷል ብለው አመጽ እያደረጉ ያሉ ጥቁሮች ብቻ አይደሉም ። የተነሳው ቀለም ሳይለይ ሁሉ ነው አደባባይ እየወጣ ያለ ።
 የጡቁር አመሪካዊ ዘረኛ በሆነ የግፍ አገዳደል በመቃወም ሰልፍ እየወጡ ያሉ በአመሪካ ህዝቦች ታጥሮ አልቀረም ።ይህ ተቃውሞ አለማዊ ቁጣ አስነስቶ በከናዳ ፣አውሮፓ በላቲን አመሪካ እነ ብራዚል፣ በአውስትራሊያ፣ በነዚህ አገሮችም ቀለም ፣ዘር በማይለይ የተገደለው ሰው በመሆኑ ሰው ነውና ለምን ሰብአዊ መብቱ ይነጠቃል ከሚል ለሰብአዊ ክብር ተብሎ ነው ከባድ መስዋእት እየከፈሉ ያሉ ።
      ታዲያ በአመሪካ በመላው አለም የሚገኙ ታላላቅ አገሮች ለሰው ክብር ሲባል በአስርሸ  የሚቆጠር ማይል  ርቀት ሳይገድባቸው ለሰውልጅ ክብር ሲባል በሁሉም አገሮች  መንግስታቸው እየናጡ ያሉ ስንመለከት ።በአፍሪካ ስንመጣ ይህ ለሰው ልጅ ወገንተኝነት አለን ? በእኔ እምነት በሁሉም አፍሪካ አገሮች ሰው ከእንስሳ በታች የሚታይበት  ተርቦ ሲሞት ፣በፖሊሶች ሲገደል ፣ ሀፍቱና መኖርያ ቃያው ፣ሲቃጠል ሲወድም ፣ሰዎች በጎደና ተገድለው ሲጣሉ ፣ሴቶች ሲታመጹ ፣ይቅርና በዘር ወይ በቀለም ልዩነት አይተው ስለ የሰው ልጅ ክብር ሲሉ ተጣብቀው  ተቃውሞ ሊያሳዩስ ይቅር ፤በአፍሪካውያን ላይ ግድያ  ሲፈጸም እስከ መሸጥ የሚደርስ የሰው ክብር ሲነካም ትንሽም እንኳ የማያዝኑ ናቸው። እንዳው በአንድ አንድ የአፍሪካ አገሮችች  ጥቁር ሰው መሸጥ ቅቡል አድርገው የሚያምኑም እንዳሉ  ።ለዚሁ የማያዝኑ መሆናቸው  መራጋገጫ አንዱ  ሰሙኑ በጥቁር አፍሪካዊ የደረሰ ዘረኛ የግፍ አገዳደለ ከአፍሪካና ከአረቦች ተቃውሞ አልታየም ። የአለም መሪዎች ፣ህዝቦች ተቆጥተው በአደባባይ ወጥተው  ቁጣቸው ባሳዩበት ወቅት ፣የአፍሪካ መሪዎች ከነህዝቦቻቸው ለጥቁሩ ወግነው ተቃውሞ ለማሰማት ሲችሉ ዝምታ መምረጣቸው እጅጉን አሳዛኝ ያደርገዋል ።
                 ሌላስ  የአፍሪካ አህጉር አለመነሳት ለሰብአዊ  መብት ጥበቃ፣ ክብር የሚሰጡት  ቦታ ዜሮ መስጠታቸው ይቆይና ፤በሀገራችን ኢትዮጱያ ያለ ሰው በዘሩ ፣በቢሄሩ ፣በቋንቋው ፣በባህሉ ከመወገዝም አልፎ በዘሩ ምክንያት ሲታሰር ፣ሲገረፍ ፣በጎደና ሲገደል ፣ሲሰቀል ፣ሲፈናቀል ይቅርና አንዱ ቢሄር ወይ ቀለም ሲነካ ለምን ያንን ዘር ወይ ቀለም ፣ ለምን ተነካ ብሎ አንዱ ክልል ለሌላው ክልል  ( ለግለ ሰው )ወግኖ ለሌላው ክልል ህዝብ ሲጣበቅ ፣መስዋእቲ ሲከፍል አይታይም ። በሌላ ይቅርና እንደሰለጠኑ አገሮች  ከአህጉር ወደ አህጉር  ተሻግሮ ለሌላ አህጉር በማስብ ማድረግ ይቅርና  አይታሰበም ።
           ለዚሁ ሀቅ ኢትዮጱያ ሀገራችን አንዱ ዜጋ ፣ ቢሄር ፣ቡዱን ፣ዘርህ ሲበደል ለዜግነትህ  አለመወገን ( አለመጣበቅ) በሞዴልነት  ትጠቀሳለች።ይህም በአዋሳ  ፤በሲዳማ ፣ በወላይታ በጉጅ ከ6 ሚሌን በላይ ህዝቦች ተፈናቅለው ቡዙ ህጻናት  ነብሰ ጥሮች ፣አዛውንቶች በበረሀ ሲጣሉ ! !  በአንድ ቀን ብቻ  በአዋሳ  ከተማ 170 ሰዎች በላይ  በአንድ ሰአት ውስጥ  ሲገደሉ በሞቶዎች የሚቆጠሩ ቆስለዋል ።ሞቶዋል ሀፍት ወድሟል ፣ተዘርፋል ፣ውቢቱ አዋሳ ከተማ ጠቁራለች ።በዛን ጊዜ የኢትዮጱያ ህዝቦች የአዋሳ አደጋ አስመልክተው  በግለሰው ፣በቡዱን ፣ወይ በቢሄር የተቃውም ምልክት አላሳዩም ።ወይ አልጠየቁም ።  በሙሁራን በተማሪዎችም አልታየም ።
                   በሱሟልና በኦሮሞ  መካከል የክልል መሪዎች በአቃጣጠሉት የዘረኝነት እሳት ሰደድ በሽዎች ተፋናቅለዋል በሞቶ የሚቆጠሩ ወገኖች  በአንድ ቀን  ከ150 በላይ ሞተዋል ።አመራ ፣ከኦሮም    በሁሉም አካባቢ ተፈጅተዋል በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝቦች ተፈናቅለዋል ።እጅግ ቡዙ ወገኖች ሞተዋል ።  ከ600 በላይ ትግሪያኖች ትግራይ በመሆናቸው የአማራ እና የኦሮሞ ጽንፈኛ አማራሮች ከህዋሓት መሪዎች በጥቅም ፣በስልጣን ሽኩቻ፣ ከነበራቸው ቂም በቀል ለሚስኪኑ ጉልቦቱ እና ጭንቅላቱ ረክሶ ( አፍስሶ )ሰርቶ ለሚኖሮው ህዝብ የቂማቸው መዋጣጫ በማድረግ ቡዙ ትግሪያኖች ተገድለዋል ። ያሁሉ ህዝብ ተፈናቅሎ፣ ተገድሎ ፣ሀፍታቸው ተወሮ  ፣ጭራሹም ለዘመናት ሀገራችን ነው ብለው  የኖሩበት  ተወረው በባዶ እጃቸው ተነቅለው ተባረሩ ።እስከ አሁንም አልተቋቋሙም ።የህዋሓት መሪዎች ርብርባቸው የተቀማነው ስልጣን እናስመልሳለን በማለት በጭንቀት ተጠምደው  ፤ህዝቡ ግን እስከ አሁን አልተቋቋመም  ።በተፈናቃይ ስም በአገር ወስጥ፣ በዲያስፖራ የተሰበሰበ ወደ አንድ ቢሌን የሚጠጋ ብር ፣እጅግ ቡዙ ቁሳቁስም እስከ አሁን አልተሰጣቸውም   አሁንም እየተንከራተቱ ይገኛሉ ።ፈደራል መንግስትም ለተፈናቀሉ የትግራይ ህዝቦች ይቅርና ሊቋቋሙ ጥረት ሊያደርግስ እንደባእድ በመመልከት ገልሎዋቸዋል ። የጭካኔ  ጭካኔው ግፍ ግን በኦሮሞ ዞናች ሄዶ ከእንግዲህ ወዲህ  ተግሬዎችም ጠራርገን ከሚደርሱበት አድርሰናቸዋል በማለት ዘረኛ ዲስኩሩ ለኢትዮጱያ ህዝቦች አስተጋባ ።አዬ የሀገር  መሪ ነውን ? በዚህ ላይም የኢትዮጱያ ህዝብ የተማረም ይሁን ያልተማረ ፣ነጋዴ ፣ባለሀፍት ፣የሰብአዊ መብት ተጣባቂዎች ትንፍሽ አላሉም ።ቨ
        ሌላስ በአማራ ፣በቤልሸንጎል ፣በቤልሸንጎልና በኦሮሞ መካከል የሰወስቱ መሪዎች በመሩት ግጭት የሰወሰቱ ህዝቦች ተላልቀዋል በየቀኑ የሞተው የአማራ ፣የትግራይ ፣የኦሮሞ ፣የቤልሻንጎል ፣ለሸቅል ከሌሎች ክልሎች የመጡ  ወገኖች እንተዎው እና ፤ በአንድ  ቀን ከቤል ሸንጎል ጉሙዝ ብቻ  200 ከአማራ ከ40 በላይ ከትግራይ ከኦሮሞ ፣ከጋንቤላ ፣ከሌሎች ክልሎች ለሸቅል የመጡ ወገኖች ቁጠር የላቸውም ሞተዋል ።የሰው ልጅ ረሳ በቀን ጅብ ተበልቶዋል  ። በጋንቤላስ በአንድቀን ከ200 በላይ ህጻናት ታፍነው ተወስደዋል ። ሌሎች በውስጣቸው በተፈጠረ የዘር ፣ወይ የጎጥ ግጭት በአንድቀን ከ230 በላይ አልቀዋል ! !በአፋር፣በዒሳ መካከል የነበረ እልቂት ቡዙ  ወገኖች አልቀዋል። ሱማም ም/ ፕረዝዳንት መስጦፌ ስልጣን ከያዘ በስማል እርስ በእርስ በመገዳደል  ተጠምዷል ። በአማራ ፤በአፋር መካከል የነበረ ግጭት እና ሞት ። በሁለቱ በኩል ህዝቦች እልቂት ነበር ። ።
               በአማራ ውስጥ አማራ ከቅማንት ፣አማራ ከአገው የነበረ እልቂት መፈናቀል ።መቸ በህዝቦች መተላለቅ ብቻ  ፤በወቅቱ ገዱ እንዳርጋቸው ፣ደመቀ መኮነን ፣ንጉሱ ጥላሁን  ሌሎች የአማራ መሪዎች ፣የራሳቸው የስልጣን ወንበር ይጠቡቁልናል ከሚል እሳቤ የጎንደር ፣የጎጃም ፣የወሎ ወ ዘ ተ  ቦዞኔዎች ፣ ሽፍቶች የነበሩ በየጫካው የሰበሰቡዋቸው ሸፍቶች  ፣የመንደር ድሩዮዎች አሳባስበው ከቄሮ ለመመሳሰል ፋኖ የሚባል ስም ለጥፎው ለአማራ ህዝብ በመናቅ ጠቅልለው የሸፍታ ስራ በመስራት ከአባይ ድልድይ በጎጃሞ ጎንደር እስከ ሌማልሞ ፣ ሳንጃ ከደብረሲና እስከ ቆቦ ያሉ ጎደናዎች ጠቅልለው ወደ ዝርፍያ በመሰማራት  የእርድ እንስሳ  በጎች የቀንድ ከፍት  ከመኪና ፣እህል በማውረድ  ፣ በየጎደናው በማቆሞ መንግስት የማያውቀው የገንዘብ ዝርፊያ ፣ ሀፍታሞች በማስገደድ ከሞቶ ሽ እስከ ሚሊዮኖች ገንዘብ በመጠየቅ  የአርሶ አደሮች ልጅ ህጻናት በመጥለፍ ገነዘብ መጠየቅ፣ በአማራ ህዝቦች የማፍያ ወረራ አወጁበት ። ሌላስ ከዩንቨርስቲ የተጠለፉ  ልጃገሮዶች ተማሪዎችም በወላጆቻቸውና በሌሎች አገር ወዳድ ወገኖች  ትልቅ የስነልቦና ጭንቀት የፈጠረ ነው ። ይህም መልስ ማግኜት አለበት   ስለዚህ የአመራ ክልል ለሁለት አመት የሽፍፍቶች ያስተናገደች ሆና አለፈች ።በነገራችን ላይ ፋኖ የሚባል ስም በ60 ዎቹ ዓ ም የሀገራችን  ተራማጅ ሙሁራን የዘውዳዊ ስርአት ለመጣል እንደ መፎከር የያዙት ፋኖ ተሰማራ የሚል ተራማጅ መዝሙር የተወሰደ ነበር ። እነ ንጉሱ ፣ደመቀ ፣ገዱ ግን ለአገር አጥፊ ሸፍቶች ሸለሙዋቸዋል  ።
         የፈደራል መንግስት እኮ የሀገር መሪዎች ጀነራሎች ፣ክልል መሪዎች ሊጠብቅ አልቻለም ። በጠራራ ጸሀይ በማናቸው ሰወች በቤታቸው ፣ በቢሮዋቸው ተገድለው ተዘርረዋል ። የሀገራችን ብርቅየ ሙሁራን እንደነ እንጅነር  ስመኜው በቀለ የመሳሰሉ በጎዳና ፣በስራቸውላይ ተረሽነዋል ።የዜጎች ሞት በኢትየጱያ ክብሩ ከእንሳ በታች ሆኖዋል ።
              የተከበራቹሁ  ወገኖች በዘመነ አገዛዝ ነባሩ ኢህአደግ የነበረ የዘር ግጭት ፣እልቂት ጦርነት እጀግ ቡዙ ስለሆነ  ለታሪክ ንተወው  እና፤ የኢህአደግ አካል የሆነው  በሱ የሰለጠነ ጥሩ አስፈጸሚ የነበረ  አዲሱ የለውጥ ሀይል ነኝ እያለን ያለው   ወደ ስልጣን ከመጣ በሁለት አመት ወስጥ በዘረኝነት  ፣በማንነት ፣በግዛት ይገባኛል  ፣በስልጣን ሽኩቻ ምክንያት የተፈጠረ ግጭት በየቀኑ  በግፍ የሞቱት ፣የቆሰሉ ፣የተፈናቀሉ ፣ የታሰሩ ፣የተሰደዱ ዜጎች  ፣ኢትዮጱያውያን ቢቆጠሩ  ፣በደርግ  እና በህዋሓት መካከል በነበረ ዘግናኝ ጦርነት  የነበረ ሞት ፣ መፈ ናቀል  ፣ስደት ፣በኢትዮኤርትራ ጦርነት የተፈናቀሉ ፣የሞቱት ፣የተሰደዱት በድምር በአሁኑ አዲሱ ኢህአደግ  ክፉ የአጋዛዝ ዘመኑ በሁለት አመት ብቻ  ከላይ በጠቀስኩዋቸው  ምክንያቶች ሲወዳደር እኩል ( የሚጠጋጋ ) ሞት ስደተ ሀፍት ውድመት አጋጥሟል  ! ! !
                       ጦርነት መፈናቀል  ሞት ሰደት አሁንም መቸ ቆመና ፤አንዳ ማስረጃ  በምእራብ ፣ምሰራቅ ወለጋ  በሌሎች የኦሮሞ አካባቢዎች ከአንድ አመት በላይ ያስቆጠረ በሀገር መከላከያ እና በኦሮሞ ህዝቦች መካከል እየተካየደ ያለ ጦርነት ሰው በላና ሀፍት አውዳሚ ነው የምንመለከተው ያለን። አዲሱ የለወጥ ሀይል ከመጣ ወዲህ እኮ በመላው ሀገራችን ጦርነት የህዝቦች እልቂት አላቋረጠም ። ዘረኝነት እኮ ተባብሰዋል ።እች አገር በሁለት አመት ውስት እኮ  በግዚያዊ አሸኳይ አዋጅ አዋጅ  ነው እተዳደረች ያለቹ ።
        ከላይ ያስቀመጥኩት ሁሉ ምናልባች ይህ ሰውዬ መጥፎ መረጃ ይቆፍርናል የሚል ስሜት ላይ የሚከታቹሁ ወገኖች  ልትኖሩ ትችላላችሁ ፤እኔ ይህ አጀንዳ ያመጣሁበት  ምክንያት ሁሉ ጊዜ በጭንቅላቴ እየተሽከርከረ  ያስጨንቀኝ ነበር ።ዘሬ ግን የአለም ህዝቦች በውስጣቸው የነበረ የሀሳብ ልዩነት ወደ ጎን በመተው ወደ አንድ መስመር ያስገባቸው” የጆርጅ ፈሎይድ” ጥቁር አመሪካዊ የደረሰ  ዘረኛ ክፉ አገዳደል ምክንያት በማድረግ በቢሌን የሚቆጠር ህዝብ ለዘሮኞች በመቃወም በሁሉም የአለማችን አደባባዮች ፣ በቤተ መንግስታት  ፤አንባሳደሮች በቁጣ በመውጣት ለዘረኛ መንግስታት፣ ፖለቲኮኞች ያንቀጠቀጠ አመጽ በማድረጋቸው ፤በሀገራችን ፣ብሎም በአፍሪካ ያሉ አማጺ እና አጭበርባሪ  መንግስታት፣ ፖለቲኮኞች ማስጠንቀቅያ (ሽብር) የፈጠረላቸው ከመሆኑም በላይ ለኢትየጲያውያን አስተማሪ እኖ ስላገኘሁት ህዝባችን ይህንን ጥሩ የህዝቦች አንድነት የምሳሌ  ተግባር ሰንቆ  ወደ ኃላ መለስ  ብለን ካሁን በፊት በሀገራችን በሚሊዮኖች  የሚቆጠሩ ዜጎች ሲገደሉ ሲፈናቀሉ ፣ ሲሰደዲ ሳሉ እንደባእድ ሆነን የሩቅ ተመካች በመሆን  በመመልከታችን ትልቅ የህሊና ቅጣት ተቀብለን ለወደፊት ግን የሆነ ዜጋ ግፍ ሲፈጸም የሆነ አስተሳሰብ ይንረው ሰው በመሆኑ ብቻ ስለ የሰው ክብር ሲባል መስዋእት መክፈል እንዳለብን ለመጠቆም ነው ።   እስኪ ተመልከቱ በአንድ ጆርጅ ፍሎይድ ለም  እንደ አንድ ሰው ሲነሳ  እኛይህ ህዝብ በዘር ግጭት ምክንያት እንዲህ እተሰቃዬ ዝምታን ንመርጣለን?
 
Filed in: Amharic