>

ኬሪያ ኢብራሂም ከውቅሮ እስከ አራት ኪሎ!!! (ኣይተ የማነ ንጉሤ) 

ኬሪያ ኢብራሂም ከውቅሮ እስከ አራት ኪሎ!!!

ኣይተ የማነ ንጉሤ 

… እንግዲህ ይህቺ ሞራልና ስነምግባር የሌላት ሰው ነች ለሞራሌ ብየ ከስልጣኔ ለቅቄያለሁ የምትለን? ሞራል የሚጀምረው ከቤት ነው። ስብዕና የሚለካው ከትዳር ከታማኝነት ነው።
የኬሪያ አባት አቶ ኢብራሂም ሱቅ ነበራቸው። በሚኖሩባት ውቅሮ ከተማ በዚህች ሱቅ ይተዳደሩ ነበር። ሴት ልጃቸው ደግሞ ቆንጆና ጎበዝ ተማሪ ነበረች። በቤታቸው ደግሞ አንድ ታማኝ ሰራተኛ ነበራቸው። ሱቅ ላይ የሚሰራው እሱ ነበር። ብዙ አመታት ከቤታቸው ስለኖረና ታማኝነቱ ስላዩ ለሰራተኛቸው አቶ ኢብራሂም ቆንጆዋንና ጎበዝ ተማሪዋን ይሰጡታል። ትዳር መስረተው አብረው መኖር ጀመሩ።ጎበዝ ተማሪዋን የማትሪክ ውጤት አልቀናትምና የቀበሌ የእርሻ ባለ ሞያ ሆና መስራት ጀመረች። እሷ የመንግስት ሰራተኛ ሆና ባሏ ደግሞ ሱቅ እየሰራ የሞቀ ትዳር መሰረቱ፣ ሶስት ልጆችም ወለዱ። በስራ ምክንያት ግን ተራራቀው ይኖሩ ነበር። በይበልጥ እሷ ከውቅሮ ወደ ሒዋነ የምትባል ከተማ በመሄድ ነበር የገጠር የእርሻ ባለሙያ በመሆን የምትሰራው!!
የእርሻ ባለሙያ ሆና በምትሰራበት ግዜ ወደ ፖለቲካው አለም ማለትም ወደ ካድሬነት የምትገባበት ዕድል አገኘች። በአጭር ግዜም ወደ ህወሓት በመግባት ተወዳጅነትን አተረፈች። ቆንጆ ሴት እና ጥሩ ምላስ ያላት ሴት የሚፈልጉ የህወሓት ባለስልጣናትም ዓይናቸው አሳረፉባት። ከምትሰራው ቦታ ወደ ሁርሶ በመውሰድ የመካከለኛ አመራር ስልጠና ተሰጣት። በማሰልጠኛውም ሆን ተብሎ ተጋይ እንደሆነች እንዲወራ ተደረገ። በአጭሩ ወደ ቅጥፈትና የውሸት አለም ተቀላቀለች። በይበልጥ ደግሞ ከህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት በምስጢር መገናኘች ጀመረች። በአንድ ግዜም ከቀበሌ ወደ ክልል አደገች። የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ለመሆን በቃች። ዝናና ተወዳጅነት እያተረፈች መጣች። የህወሓት ባለስልጣናት ይሻሙባትና እስከ ሽጉጥ መማዘዝ  ተዳረሱ።
ስልጣንና ዝና ሲመጣ ትዳር ይበላሻል እንደሚባለው ያ የልጅነትና የልጆቿን አባት ናቀችው። ያ የልጅነት ፍቅሯን ተጠየፈችው። በወር አንዴ በምትመላለስበት ቤት ስራዋ እሱን ማዋረድና መሳደብ ሆነ፣ አትመጥነኝም አለችው። አንተ አንድ ተራ የሱቅ ሰራተኛ እኔ ዝነኛ ከዚህች ሃገር አስተዳዳሪዎች የምውል ነኝ አለችው። ግዜም አልፈጀችም ያ ባሏና ቃል ኪዳኗ እንደ የቤት ሰራተኛዋ ከቤት ሻንጣውንና ትንሽ ፍራሽ በመስጠት አባረረችው። እሱም በመቐለ ከተማ ትንሽ ቤት ተከራይቶ የሞቀ ቤቱ እና ሶስት ልጆቹን ትቶ ብቻውን የሰቆቃ ህይወት መግፋት ጀመረ። የሚያውቁትና ታሪኩ ያሳዘናቸው ሰዎች ሲንጄር የልብስ ስፌት ገዝተው ሰጡት። አሁን ልብስን እየሰፋ በመቐለ ከተማ ዓዲ ሓቂ ገበያ ይኖራል። ሁሌም ከአፉ የማትጠፋ ንግግር አለችው “ምስቴን ቀሙኝ” !
እንግዲህ ይህቺ ሞራልና ስነምግባር የሌላት ሰው ነች ለሞራሌ ብየ ከስልጣኔ ለቅቄያለሁ የምትለን? ሞራል የሚጀምረው ከቤት ነው። ስብዕና የሚለካው ከትዳር ከታማኝነት ነው። ትናንት ለስልጣንና ለዝና ብላ የገዛ ባሏን ዓይንህን ላፈር በማለት የሶስት ልጆች አባት ባለቤቷን ያባረረች ዛሬ ለህሊናየ ብየ ስልጣኔ ለቀቅኩ ብትል ማንም አያምናትም። ህሊናዋ ከሸጠችው ቆይቷል!!
ህሊና ቢሶች ህሊና አለን ሲሉ ደግሞ ያናናድል!!የዚህች ታሪክ ባለቤት የህወሓት ማእከላይ ኮሜቴ አባልና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ትናንት በገዛ ፈቃዴ ስልጣን ለቀቅኩ ያለችን ኬርያ ኢብራሂም ነች።
Filed in: Amharic