>

ባልደራስ ለሁለተኛ ጊዜ ለአዲስ አበባ ፖሊስ የትብብር ጥያቄ በደብዳቤ አስገባ!!!

ባልደራስ ለሁለተኛ ጊዜ ለአዲስ አበባ ፖሊስ የትብብር ጥያቄ በደብዳቤ አስገባ!!!

ፖሊስ ደብዳቤዉን ፈርሞ ተቀብሏል።

________
ለአዲስ አበባ  ፖሊስ ከሚሽን
አ.አ
ጉዳዩ፡- ቤታቸው ፈርሶባቸው ችግር ላይ ለወደቁ ወገኖቻችን እርዳታ ለመስጠ እንድንችል ትብብር እንዲደረግልን መጠየቅ።
በርዕሱ እንደተጠቀሰው በ 27/09/12 ዓ.ም  ለፖሊስ ኮሚሽን ደብዳቤ ጽፈን የነበረ ሲሆን በዚህ ደብዳቤያችን ላይ በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ  ወረዳ 3 ልዩ ስሙ  ፋኑኤል ኔት ወርክ በሚባለው ቦታ ለተጎዱ ወገኖች የምግብ እርዳታ ለመስጠት ማሰባችንን ገልፀን በዚህ  ቀንና ቦታ ፖሊስ ሥነ ሥርዓት በማስከበሩ ረገድ ትብብር እንዲያደርግልን ጠይቀን ነበር፡፡
ይሁን እንጂ ባሳወቅነው ቀንና ቦታ ለእርዳታ ስንሄድ የኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ፖሊስና መስተዳድር የምናውቀው ነገር የለም በማለት እርዳታውን እንዳንሰጥ ከመከልከላቸውም በላይ የፓርቲያችንን አመራሮች ከነእርዳታው ለተወሰነ ጊዜ  አግተው ለቀዋል፡፡ እርዳታ ሊቀበሉ የመጡ ድሆች እርዳታ የሚቀበሉበትን እቃዎች ይዘው ባዷቸውን እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡  ያ ለድሆች የታሰበው ምግብ ዛሬም ድረስ በጽ/ቤታችን አዳራሽ ተቀምጦ  ይገኛል፡፡  ይህ ድርጊት በጣም አሳዝኖኗል፡፡
በመሆኑም አሁንም ፖሊስ ከሚመለከተው አካል ጋር ተነጋግሮ የማስተባበሩን ስራ እንዲሰራልንና የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 6/2012 ዓመተ ምህረት ቀደም ሲል በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት እርዳታውን ለተጎጂ ተወካዮች እንድናደርስ በትህትና እንጠይቃለን፡፡ እርዳታው የሚሰጠው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አክብረን በተራ በተራ አራት ሰዎች እየመጡ እንዲወስዱ ነው የሚደረገው፡፡ ስለዚህ ፖሊስ ለሚመለከተው አካል ትብብር ጽፎልን ለተራቡ ወገኖቻችን እርዳታውን አንድንሰጥ እንዲደረግልን እንደገና በትህትና  እጠይቃለን፡፡
ከሠላምታ ጋር
                                                                
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ
Filed in: Amharic