>

የሽፍታዎቹ ውልና በኢትዮጵያ ፍርስራሽ ላይ ትንንሽ ቁርጥራጭ አገር የመመስረት ሴራ ፦ (ሰብስቤ ገብሬ ኦዳ)

የሽፍታዎቹ ውልና በኢትዮጵያ ፍርስራሽ ላይ ትንንሽ ቁርጥራጭ አገር የመመስረት ሴራ ፦

.
.ሰብስቤ ገብሬ ኦዳ

የኢትዮጵያን ጠላቶች ኢትዮጵያን ለማምከንና ከአለም ካርታ ላይ ለመሰረዝ የዘመናት ሴራ ሲጎነጉኑ ኖረዋል ። በሻቢያ ጋሻ ጃግሬነት የተፈለፈሉ ድርጅቶችም በኢትዮጵያ ፍርሰራሽ ላይ ትንንሽ የራሳቸው ጎጆ ሊያበጁ ሸፍተዋል ። እነዚህ ኢትዮጵያን አምርረው የሚጠሉ ድርጅቶችና አመራሮቻቸው ኢትዮጵያን በጣጥሰው እንዴት እንደሚቀራመቷት በ1980 ዓ.ም አንድ የትግል አንድነት ሰነድ ተፈራርመው ነበር ።
.
የዚህ የስምምነት ጭብጥ ሐሳብ ….. ፀሐፊ ታደሰ ቴሌ ሳልቫኖ በ2010 ባሳተመው ” ፍጅት ” በሚለው መፅሓፉ እንዲህ አስቀምጦታል ። ፀሐፊው በኢትዮጵያ ሬዲዮ የኦሮሚኛ ፕሮግራም ጋዜጠኛ ሆኖ ይሰራ በነበረበት ወቅት  የኦነግ ፖሊት ቢሮ አባልና የወታደራዊ ስትራቴጂ ኃላፊ ከነበሩትን ከታጋይ ነዲ ገመዳ ቃለ ምልልስ አድርጓል ። አቶ  ነዲም በሱዳን/ካርቱም ስለተደረገው  ስምምነቱ እንዲህ ሲሉ ገልፀውታል ።
.
” …. ደርግ የካቲት 1981 ዓ.ም በሽሬ ውጊያ በተሸንፈ ጊዜ … መቀሌን በመልቀቁ ትግራይ ተፃነቷን ያገኘች በመሆኑ እጅግ ተደስተን ነበር ።
.
የደስታችንም ምንጭ ቀደም ሲል በ1980 መለስ ፣ ኢሳያስ ፣ ሌንጮ ለታ ፣ ታምራት ላይኔ ካርቱም ላይ የተፈራረሙት ስምምነት ተግባራዊ ሊሆን እንደሚችል በማሰብ ነው ። ስምምነቱም ፦
.
1 . የኤርትራ ሕዝብ ከአማራ ቅኝ-አገዛዝ ነፃ እንድትወጣ እና የራሷን መንግስት  እንድትመሰርት ፣
.
2 . ትግራይ ከኢትዮጵያ ተገንጥላ የራሷ ሪፐፕሊክ መንግስት እንድትመሰርት ፣
.
3 . የኦሮም ሕዝብ ከአማራ ቀኝ ግዛት ነፃ ወጥቶ የራሱን መንግስት እንዲመሰርት ፣
.
4 . የአማራ ሕዝብ ከደርግ ጭቆና ነፃ ወጥቶ የራሱን መንግስት እንዲመሰርት ፤ የሚል ስምምነት ተፈራርመዋል ።
.
ይህን ሰነድ ሁሉም ታጋይ ሰምቶ ደስታውን ገለፆ ነበር ።
በተጨማሪም ሰሜን ወሎ ፣ ሰሜን ምስራቅ ጎንደር የመሳሰሉት ትግርኛ ተናጋሪዎች ያሉበት ወረዳዎች ወደ ትግራይ እንዲካለሉ የሚል ውሳኔም ነበረበት ። ….. ነባር ታጋዮችም በደንብ እናውቅ ነበር ።
.
በሌላ መልኩ የተቀሩት በተለይ የሱማሌና የአፋር ሕዝብ የሰፈሩበትን ግዛት አካሎ የራሳቸውን መንግስት ይመሰርታሉ ።……  የሲዳሞ ፣ የአርባ-ምንጭ ፣ የከፋ ፣ የጋንቤላ ፣ የቤኒሻንጉል ጉምዝ ፣ የሐረሪ ፣ የጉራጌ እና የተለያዩ ብሔር-ብሔረሰቦች የራስን እድል በራስ መወሰን በሚለው መርህ መሠረት ያለጦርነት በሰላማዊ መንገድ ሪፈረንደም ተካሒዶ የጋራና የተናጠል ነፃነታቸውን ያገኛሉ ። የሚል ውሳኔ ላይ ደርሶ አራቱ የፖለቲካ ድርጅቶች ተፈራርመው ነበር ።
.
ወደብም በተመለከተ  ትግራይ አሰብ ወደብን በነፃ ፣ አማራ በትንሽ ኪራይ ፣ ኦሮሞ የጅቡቲ ወደብን በኪራይ በተጨማሪ የኬንያ ሞንባሳን ወደብ ፣ የሱማሌን ሪፐፕሊክ ሐርጌሳ ወደብ ፣ ፖርት ሱዳን እና የመሳሰሉት አገልግሎት ያገኛሉ ። “
Filed in: Amharic