>
5:14 pm - Saturday April 20, 3709

ጥፊ ያላት ከተማ ነጋሪት ቢጎሰም አትሰማ!"  (አምሳሉ ገ/ኪዳን)

ጥፊ ያላት ከተማ ነጋሪት ቢጎሰም አትሰማ!” 

አምሳሉ ገ/ኪዳን

 

* ይሄ የምታዩት የ31ኛው ዙር ኦሮሚያ የሚሉት ልዩ ኃይል ሠልጣኝ ሠራዊት ነው!!!
እኔ የምለው ደሴ ላይ ዐቢይና አምባቸው የአማራን ሕዝብ “ልዩ ኃይል ማሠልጠንና ማስታጠቅ ጠቃሚ አይደለምና አያስፈልግም!” ብለው አሳምነው ያሠለጠነውን የአማራ ልዩ ኃይል በትነው የአማራን ልዩ ኃይል በጥቂት ቁጥር እንዲወሰን አድርገው ሲያበቁ እነሱ ግን በየጊዜው እንደ አሸን የፈላ የልዩ ኃይል ሠራዊት እያሠለጥኑ ሲያስታጥቁ “ለምን?” ብሎ አደባባይ ወጥቶ የሚጠይቅና የሚቃወም አንድ እንኳ “ለአማራ እታገላለሁ!” የሚል ኃይል ይጥፋ???
ፀረ አማራው የጥፋት ኃይል ብአዴንና ቡችላው አብን ይሄንን ሊቃወሙና “ለምን?” ብለው ሊጠይቁ ያልቻሉት አማራን ለማስበላት ለጠላት የሚሠሩ በመሆናቸው ነው!!!
የተቀረው ግን እንዴት “ለምን?” ብሎ አይጠይቅም??? እንዴት “እኛ ተከልክለን ሌላው ለምን እንዲታጠቅ ይደረጋል?” ብሎ አይቃወምም??? እንዴት “ለሌላው ከተፈቀደ ለእኛም መፈቀድ አለበት! ለእኛ ካልተፈቀደ ለሌላውም መከልከል አለበት!” ብሎ አይጠይቅም???
ለነገሩ ለአማራ የሚታገልና ለአማራ የሚሠራ የተደራጀ ኃይል ማን አለና??? በሙሉ “ለአማራ እንታገላለን!” ከሚሉት ግማሽ ደርዘን ከሚሆኑት “የአማራ ድርጅት ነን!” ባይ የፖለቲካ ድርጅቶች እስከ በየአካባቢው የተመሠረቱ የአማራ ወጣት ማኅበራት ድረስ በፀረ አማራው የጥፋት ኃይል ብአዴን ቁጥጥር ስር ያሉ ናቸው፡፡ ስለዚህ ማን ነጻ የሆነ የአማራ ድርጅት ኖሮ ይሄንን ተግባር ይቃወማል??? እጅግ ያሳዝናል!!!
የአማራ ሕዝብ ግን ይሄንን ነገር በዝምታ መመልከት የለበትም!!! የኮረናን ወረርሽኝ ፈርቶም ነቅሎ ወጥቶ ከመቃወም መታቀብ የለበትም፡፡ የአሜሪካን ሕዝብ አላየህም ወይ ወገኔ??? “አንድ ሰው ነው የሞተው፣ በዚህም ላይ የኮረና ወረርሽኝ አለብን፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም ተደንግጓል!” ብሎ ፈርቶ ወጥቶ የተፈጸመበትን የመብት ጥቃት፣ ጥሰትና እረገጣ በኃይል ከመቃወም ታቀበ ወይ??? በአንተ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ ከዚህ ሽህ ጊዜ እጥፍ አይብስም ወይ??? በመሆኑም ኮረና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምናምን ሳትል ነቅለህ ውጣና መብትህን አስከብር!!! ምክንያቱም ከኮረና ወረርሽኝ በላይ የሚፈጅ መቅሰፍት እየተዘጋጀልህ ነውና!!!
አማራ በአሁኑ ሰዓት ቢላዋ ሲሳልበት ዝም ብሎ እንደሚመለከት የበዓል ዶሮ ወይም በግ ነው የሆነው፡፡ ሰው እንዴት ይሄ ሁሉ እንደአሸን የፈላ ልዩ ኃይል ሲሠለጥን እንዴት ሥጋት አያድርበትም??? እንደዶሮው ወይም በጉ ቢላዋው የሚሳለው ለሱ መሆኑን እያወቀ አንገቱን ለመስጠት ተዘጋጅቶ መቀመጥ አለበት ወይ??? ኧረ ተው ንቃ ተው ወገኔ??? አንተን ልዩ ኃይል እንዳታሠለጥን ከልክሎ፣ ፋኖችህንም በትኖ ዙሪያህን የከበበህና እየፎከረብህ ያለው ትግሬና ኦሮሞ ይሄንን ሁሉ ሠራዊት እያሠለጠነ ያለው አንተን ዕቃቃ እንዲያጫውት ይመስልሃል ወይ???
“ጥፊ ያላት ከተማ ነጋሪት ቢጎሰም አትሰማ!” እንደተባለው ሆኖብሃል መሰለኝ፡፡ “የበዓል ዶሮ ወይም በግ ነኝ!” ብለህ ቁጭ ካልክማ እንግዲህ “የራስህ ጉዳይ ነዋ!” እንጅ ሌላ ምን ይባላል???
Filed in: Amharic