>

የቆራጡ ሳሙኤል አወቀ ግዝፈት  (ብርሀኑ ተክለያሬድ)

የቆራጡ ሳሙኤል አወቀ ግዝፈት

 ብርሀኑ ተክለያሬድ

* ሁለቱ ሰማዕታት

  የሳሙኤል አወቀ ደም ከንቱ ሁኖ እንዳይቀር ካደረጉት ግለሰቦች ዋነኛውን ድርሻ የሚወስደው አቶ ምግባሩከበደ ነበር::  ምግባሩን ስንገድል ወይም ስናስገድል ሳሙኤልን ደግመን ገደልነው ::
 
“ሳሙኤል ከእኛ ከቤተቦቹ ከአሮጊት እናቱ ከህመምተኛ አባቱ አስበልጦ ይዞት እንጂ እርሱ በትምህርቱም ሆነ በሙያው የሚያኖረውና ቤተሰቦቹን የሚሠዳበት መንገድ አጥቶ አልነበረም እንደምታዩን ልጃችን የሞተው እርሱን መሸሸጊያ ቦታ አለኝታ መሆኛ ወኔ አጥተን አልነበረም እርሱ ለነፃነቴ ብሞትም ልሙት ቅድሚያ ለሀገሬ ብሎ በመነሳቱ እንጂ አሁንም እናንተ መንገዱን እስከቀጠላችሁበት ድረስ ልጃችን ሞተ አንልም”
የሳሙኤል አጎት በመታሰቢያ ዝግጅቱ ላይ ከተናገሩት
ብዙ ጊዜ ግደለኝ ብዬ ወደ አምላኬ ፀልያለሁ ልጄን ካጣሁ ጀምሮ ሁሉ ነገር ጨልሞብኛል አገዳደሉን ሳስበው ሁሌም መጠቃት ውስጤን ያንገበግበኛል ላለፉት 3 አመታት የአካባቢ ታጣቂዎችና ካድሬዎች እስኪ ታለቅሱና እያሉ ለልጄ የማፈሰውን  እንባ በዘበኛ ሲጠብቁብኝ ነበር ልጄ ወደተቀበረበት ቤተክርስቲያን ለመሳለም እንኳን እንዳልሔድ ተከልክያለሁ እግዚአብሔር ይመስገን ዛሬ እናንተ መጥታችሁ አላቀሳችሁኝ አለን አላችሁኝ እንደናንተ የልጄን ምትኮች ሳገኝ ደግሞ ግደለኝ ያልኩትን አምላክ እድሜ ስጠኝ ብዬ እለምነዋለሁ”      የሳሙኤል እናት
ሳሙኤል አወቀ ከቅንጅት ፖለቲካ ጀምሮ በአንድነትና በሰማያዊ ፓርቲዎች ውስጥ በአባልነት በአመራርነት ከፍተኛ ተሳትፎ አድርጓል በትግል ጉዞዎቹ ሁሉ ለመግለፅ የሚያታክቱ እስር እንግልትና ድብደባዎችን አስተናግዷል በሰማያዊ ፓርቲ ትታተም በነበረችው ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ አምደኛ የነበረ ሲሆን በጋዜጣዋ እርሱ በሚኖርበት አማራ ክልል በዜጎች ላይ የሚደርሰውን በደል አጋልጦባታል ሀገ ር ገንቢ ሀሳቦችንም አንፀባርቋል በጥብቅና ሙያው የብዙ ግፉአን አርሶ አደሮችን መዝገብ ይዞ ፍትህን ለማምጣት ሞግቷል።
ሳሙኤል በ2007 የሰማያዊ  ፓርቲ የምርጫ ተወዳዳሪ በነበረበት ወቅት የደረሰበትን የእንገልሀለን ዛቻና ማስፈራሪያ ከቁብ ሳይቆጥር የስርአቱን አስከፊነት ሲያጋልጥና ህዝቡን ሲያነቃ በነበረበት ወቅት ሀምሌ8 ቀን በደረሰበት የጭካኔ ድብደባ ህይወቱን ለውድ ሀገሩ በመስጠት አልፏል::
ይህን ቪድዮ ያድምጡና ሳሙኤልን በድጋሚ ይተዋወቁት
ሁሌም እናስበዋለን!!
Filed in: Amharic