>

"ኮሮና ሐኪም ነው ብሎ አልፈራኝም ፣ የኮሮና ማዕከል ላይ ነው የሚሰራው ብሎም አልተወኝም..." .(ዶ/ር ዘሪሁን አበራ )

“ኮሮና ሐኪም ነው ብሎ አልፈራኝም ፣ የኮሮና ማዕከል ላይ ነው የሚሰራው ብሎም አልተወኝም…”

.ዶ/ር ዘሪሁን አበራ ፤ የውስጥ ደዌ ሕክምና ስፔሻሊቲ ሬዚደንት
 
ሐኪም ነኝ ስራዬን በጣም እወደዋለሁ። ያስተማረኝ ምስኪን ማሕበረሰብ እና የድሀ ሀገሬም ውለታ አለብኝ ። እነዚህ ሁሉ በስራዬ ጠንካራ እንድንሆን አድርገውኛል…ስለዚህም እንደ አብዛኞቹ የሞያ አጋሮቼ ብዙ ነገር የጎደለው የጤና ስርአት ሳይገድበኝ እየታገልኩ እገኛለሁ …
ኮሮና ሐኪም ነው ብሎ አልፈራኝም ፣ ለሀገር ይጠቅማል ብሎ አላዘነልኝም፣ በቀጥታ የኮሮና ማዕከል ላይ አይደለም የሚሰራው ብሎ አልተወኝም… ለነገሩ እኔም ያንን አልጠብቅም። ነገር ግን ፈጣሪ ቸር ስለሆነ ምንም የሕመም ምልክት ሳላሣይ በ 2ሳምንት ውስጥ አገገምኩ…
በነዚያ ሳምንታት ብዙ ነገሮች በአዕምሮዬ ተመላለሱ…. እንዴት ከ114 ሚሊዮን + ሕዝብ የመጀመሪያ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ተጠቂዎች አንዱ ልሆን ቻልኩ? ስራዬ ምን ያህል ተጋላጭ እንዳደረገኝ አሰብኩ።
.
ቤተሰቦቼም በእኔ ምክንያት quarantine ነበሩ። ሐኪም በመሆኔ አልተጸጸትኩም፣ እንዲያውም በሚንከባከቡኝ ባለሞያዎች ውስጥ ራሴን ሳገኘው ደስ አለኝ። በሌላ በኩል ደግሞ ካገገምኩ በኋላ በቂ ትጥቅ ወዳልተዘጋጀበት ጦር ሜዳ እንደምሔድ ሳስብ ፍርሃት ፍርሃት አለኝ።
.
በስራችን ምክንያት ከኮሮና ውጪ የብዙ ተላላፊ ሕመም ተጋላጭ እንደነበርን አስታወስኩ። ብዙ የቅርብ ጓደኞቼን ጨምሮ TB (የሣምባ ነቀርሳ) ፣ hepatitis (የጉበት በሽታ ) እንዲሁም HIV ተይዘው እንደነበር አስታወስኩ…የሕክምና ስርዓቱ መቀየር አለበት …ባለሞያዎች ኮሮና ማዕከል ላይ በቀጥታ /በተዘዋዋሪ ፤ ስፔሻሊስት ሐኪም/የጽዳት ሰራተኛ ሳይባል ለሁሉም እኩል የህይወት እንዲሁም የጤና መድሕን ዋስትና ያስፈልጋል .. ወታደሮቹ ደሕና ካልሆኑ ጦርነቱን ማሸነፍ ከቶ አይታሰብም!! የሚመለከተው አካል ቢያስብበት እላለሁ።(ከሐኪም ያገኘነው)
Filed in: Amharic