>

አፓርታይድ በአዲስ አበባ !?! (ስንታየሁ ቸኮል)

አፓርታይድ በአዲስ አበባ !?!

” ኦሮምኛ ቋንቋ ባለመቻላችን ከሥራ ቅጥር ታገድን!” የዜጎች እሮሮ 

ስንታየሁ ቸኮል
በአዲስ አበባ አስተዳደር ባለፉት ሁለት ዓመታት የሚወሰዱ ከተማዋን ከህገ መንግስትም ውጭ በለጠጠ ትርጉም የኦሮሚያ ክልል አካል አድርጎ በመቁጠር ልዩ ልዩ አስተዳደራዊ እና ፖለቲካዊ እርምጃ ተወስዷል። 
የመሬት ቅርምቱ፣በሲቪል ሰርቪስ ውስጥ እየተፈጠረ የመጣው ዜጎች ለከተማው ሁለተኛ ዜጋ ሆነው እንዲሰማቸው የተደረጉ ጥረቶች፣ለዓመታት ነዋሪዎች ባጠራቀሙት ገንዘብ የተሰራን ኮንደሚኒየም በጠራራ ጸሐይ ሁከት ከመከልከል ጀምሮ ብሄርን ማንነት ያደረገ ማፈናቀል የኮሮና ቫይረስ እንኳን ሳይገታው ሲፈጸም ቆይቷል።
 ከ4000 ሺህ በላይ የሥራ ቅጥር አመልካቾች ከዚህ ቀደም መስፈርቱን አሟልተው ፈተናውን ከወሰዱ በሁዋላ በፖለቲካ የውስጥ ትዕዛዝ ብሄራቸውን መሰረት ያደረገ ማግለል ተፈጽሞ ከሥራ ቅጥር ሲከለከሉ በምትኩ ግልጽ ባልሆነ ሂደት ጊዜያቸው ነው የተባለ ተቀጥረዋል።
 ይህ በዜጎች መካከል የሚፈጸም የአፓርታይድ እርምጃ ለውጥ እና የለውጥ ደጋፊ በሚሉ እበላ ባዮች ድምጻቸው እየታፈነ፣ሥልጣኑን ይዞ በማን አለብኝነት የልቡን እየሰራ ያለው ሀይል ከዕለት ዕለት እርምጃው ይሄንኑ አጠናክሮ መቀጠሉን ያሳያል። ባልደራስ የሚያወጣቸውን ህዝባዊ ጥቆማዎች ትኩረት ሰጥቶ ይህ መሰሉ ዜጎችን በገዛ አገራቸው የዘረኛ ሥርዓት እርምጃ ሰላባ የሚያደርግ አሰራር እንዲቆም ከመጠየቅ ይልቅ በተቃራኒው ይህንን እያጋለጠ ገበናቸውን ጸሐይ እንዲሞቀው ያደረገውን ባልደራስን ማውገዝ ለብዙዎች ቀላል ነው። ዛሬም ባልደራሱ በከተማዋ የሚፈጸመውን አፓርታይድ እንዲህ አጋልጦዋል። 
 
“ኦሮምኛ ቋንቋ ባለመቻላችን ከስራ ቅጥር ታገድን !”
የአዲስ አበባ ነዋሪች
//
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት /ቢሮ የደረሰን ጥቆማ! 
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የክ/ከተማ እና ወረዳ አስተዳደር ት/ጽ/ ቤቶች በዝውውር የትምህርት ሙያተኞች ለመቅጠር ባወጣዉ ማስታወቂያ ከአማረኛ በተጨማሪ ኦሮምኛ ቋንቋ መናገር ማዳመጥ እንደ መስፈርት ተቀምጧል በዚህም መናገርና መስማት ያልቻሉ ወገኖች ከሂደቱ ተባረዋል። የአዲስ አበባ ነዋሪ በከተማዉ ተቀጥሮ ለመስራት ኦሮሞ ካልሆንክ አንቀጥርም እያሉት ይገኛል።
ይህ የሆነው በአዲስ አበባ ት/ት ቢሮ ውስጥ ለመቀጠር የሄዱ ሰዎች አባረሩን ሲሉ ያቀረቡት አቤቱታ መሰረት ተደርጎ ሲሆን ሁሉንም አመልካች ተጨማሪ ቋንቋ አትችሉም በማለት አሰናብተዋቸዋል።
የስራ ቅጥሩ ኦሮሞ ለሆነ ብቻ እንደሚሰጥ ተነግሯቸው  እንዲመለሱ ተደርጓል። በአዲስ አበባ እየተፈጸመ ያለዉ አድሎ ልዩ ጥቅም አምርረን ስንቃወም የነበረው ነውረኝነት በመንግስት ተቋማት በአደባባይ ተፈጻሚ እየተደረገ ይገኛል።
አዲስ አበባ ልብ በል!
Filed in: Amharic