>

"የ ብ/ጄ/ል ተፈራ ማሞ ምስክርነት ሲመረመር! (መስከረም አበራ) 

“የ ብ/ጄ/ል ተፈራ ማሞ ምስክርነት ሲመረመር!..

 

 መስከረም አበራ 

* የብ/ጄ/ል ተፈራ ማሞ ምስክርነትን ጨምሮ የሰኔ 15/2011 ግልጽ ያልሆነ ግድያ አስመልክቶ ያወጡት ጽሑፍ ዋና ዓላማ የፌደራል መንግሥቱን በተለይም ከሒደቱ የጠቅላይ ሚ/ር አብይን ሙሉ ለሙሉ ከተጠያቂነት ለማውጣት ያለመ ነበር። 
 
ኮ/ል አለበልም የፌደራሉን መንግስት አትንኩ የጉዳዩ መነሻ እና መድረሻ ብ/ጄ/ል አሳምነው ጽጌ ላይ ደምድሞ ብቅ ብሎዋል። የዚህ የሰሞኑ የተጠናከረ ዘመቻ ግድያው በግልጽ ምርመራ ይጣራ የሚለውን ጥያቄ ለማዳፈን እና እነሱ የሚነግሩንን እንድናምን ነበር ። አልሆነም ዘመቻውን የሚያደርጉት ራሳቸውን ትዝብት ላይ ከመጣል አልፈው ትላንት ከብአዴን ጋር የሕወሓት አሽከር ሆነው የህዝቡ መገደል ትዝ ብሏቸው የማያውቁ መንፈሰ ልሎች እና የፈረደበትን የአማራ ሕዝብ ለቅፈፋ ተጠቅመው በስሙ የሰበሰቡትን መንትፈው ጥጋቸውን የያዙ የጎ ፈንድ ሚ ኪስ አውላቂዎች ናቸው።
ፍትሕ የሚባለው በአንድ ወንጀል ጉዳይ የተጣራ መረጃ ቀርቦ፣ለገዳይም ሆነ ለሟች ያልወገነ አሰራር ባለበት የአንድ ወገን ሳይሆን የሁሉም ወገን ምስክሮች በግልጽ ችሎት ቀርበው ያዩትን እና የሚያውቁትን መስክረው ነጻና ገለልተኛ በሆነ ፍርድ ቤት የሚሰጥ ነው።
በሰኔ 15 ግልጽ ባልሆነ ግድያ ፍትህ እንፈልጋለን ሲባል ለሁሉም ወገን ቢያስደስትም ባያስደስትም በዚህ አሳማኝ እና ህጋዊ መንገድ ሲያልፍ እንጂ ቆስለው የተረፉ ምስክር መሆን የሚችሉትን ሁሉ ረሽኖ ፣አግበስብሰው ያሰርካቸው መካከል ጥቂት ከፈታህ በሁዋላ በፈለከው ጊዜ እያስለፈለፍክ ፣ከሰኔ 15 በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ በሟቾቹ አመራር ላይ ሲነሳ የነበረ ቅሬታ በተለይም የኦሮሞ  ጽንፈኞች በጠራራ ጸሐይ በከሚሴ እና በአጣዬ የፈጸሙት የዘር ጭፍጨፋ በመከላከያ ጭምር ሽፋን መሰጠቱ፣አማራው ተከቦዋል ብለው ብ/ጄ/ል አሳምነው ጽጌ በተናገሩ በጥቂት ሳምንት መገደላቸው ግድያው ፖለቲካዊ አይደለም ብሎ ለማመን ቀርቶ አለማሰብ ግብዝነት ነው።
 ይህም ይሁን የፈለከውን ክስ ይዘህ ቅረብ ግን የአንተ ወገን ክስ እንዲያሸንፍም ጉዳዩ በገለልተኛ አካል እንዳይጣራ መንገድ የምትዘጋ ከሆነ የአማራ ሕዝብ ከወያኔ ወደ መቀሌ መሔድ እስከ ሰኔ 15 ያለውን እውነታ የማያውቅ አድርጎ መቁጠር ነው። ከዚያስ በሁዋላ?
ከሰኔ 15 በሁዋላ ዜጎች አማራ በመሆናቸው ብቻ በኦሮሚያ ክልል ተጋድመው ጭምር ሲታረዱ፣ቤታቸው ሲቃጠል፣አካለ ጎደሎ ሲሆኑ ትንፍሽ ያላለው አዴፓ ዛሬ ደርሶ ስለ ሰኔ 15 እመኑኝ የሚለው ተቆርቋሪነት ውሃ አያነሳም። ያ ሁሉ ዘመቻ ብ/ጄ/ል አሳምነው ላይ የተደረገው ስልጣን ፈልጎ ሳይሆን ህዝባችንን አትንኩት የሚል ነው በዚህ ጥያቄ ላይ ዶ/ር አምባቸውም የተለየ አቋም የለውም ።በወቅቱ ከፌደራል መንግስቱ ጋር ጊዜያችን ነው ከሚለው ሀይል የገቡበትም ፍጥጫ ይሄው ነው። የቤተ መንግስቱ ግምገማና ከዚያ በፊት የነበሩ ክሶች በግልጽ መነገር ለሰኔ 15 የራሱን ድርሻ አለው።
ግድያው ፓለቲካዊ መሆኑን ራሳቸው ብ/ጄ/ል አሳምነው ጽጌ ዛሬም በሕይወት ላለች የፎርቹን ጋዜጣ አዘጋጅ “መፈንቅለ መንግሥት ብሎ ነገር የለም።የሚመስለኝ የፌደራል መንግሥቱ ክልልን ለመቆጣጠር ፈልጎ ነው። ለማንኛውም ሁሉንም መርምረን ጠዋት መግለጫ እንሰጣለን” ያሉት ህያው ቃል እነ ዶ/ር አምባቸውን እና ብ/ጄ/ል አሳምነው ጽጌን ሟች እና ገዳይ አድርጎ በጎጥ ተከፋፍሎ ለማናቆር ለሚፈልገው አካል ካልሆነ ከሰኔ 15 በፊት እና በሁዋላ የነበሩት ሁኔታዎች መመርመር የግድያውን ዓላማ በግልጽ ያሳያል። ለሁሉም ከወር በፊት ያወጣናቸውን የሰኔ 15 ግድያን ለምን በነጻ ወገን ይጣራ እንደምንል ሰንዝረናል። የሰማኑ ዘመቻ ግን አንዳቸውንም ጥያቄዎች ሳይመልሱ በራሳቸው ተጨማሪ ጥያቄ ፈጥረዋል።
Filed in: Amharic