>

 ከ"ዳቦ ልሰጣችሁ ነው" ዜና በስተጀርባ...!!!  (ሀብታሙ አያሌው)

ከ”ዳቦ ልሰጣችሁ ነው” ዜና በስተጀርባ…!!! 

ሀብታሙ አያሌው

መቼም እነዚህ ለጉድ የፈጠራቸው ተረኞች ለህዝብ ያላቸው ንቀት አጃይብ የሚያሰኝ ነው። ማሊያ ቀያሪው አብነት ገብረ መስቀል በንብ ቲሸርት ቧልስ እንዳልደነሰ ሁሉ አሁን ደግሞ ተረኞቹ ስፍራቸውን ሲይዙ የኦሮሞነት ካርታውን መዝዞ አዛዥ ናዛዥ ሆነ።
ታከለ አዲስ አበባ በተመደበ ማግስት የሼህ አላሙዲ ይዞታዎችን በሙሉ ወረሰ፤ በለማ መገርሳ በኩል ደግሞ ኦሮሚያ ያሉ የሜድሮክ ድርጅቶች በሙሉ በቄሮ እንዲዘረፉ እና የባለቤትነት ጥያቄ እንዲነሳባቸው ተደረገ።
የሜድሮክ ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር አረጋ ከአንድ ዓመት በላይ ለመዓድን ሰራተኞች ብቻ ያለምንም ስራ 4መቶ ሚሊዮን ብር ደሞዝ እየከፈለ በብዙ ወጪ በመስኩ የሰለጠኑ ባለሙያዎች እንዳይበተኑ አድርጎ መንግስትን ሲማፀን ቆየ።
በመጨረሻ ግን ከተረኞቹ አጭር ቀጭን ትዕዛዝ ለሼሁ ተላከ “የሜድሮክ ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር አረጋ ከኦሮሚያ መንግግስት ጋር ተግባብቶ መስራት ስላልቻለ ቀይር” የሚል። ሼሁ ትዕዛዝ ከማክበር ውጪ ምርጫ አልነበረውም ወይ የተረኞቹን ትዕዛዝ ተቀብሎ ድርጅቱን ማቆየት አለያም ሰባራ ሳንቲም ሳይዝ ንብረቶቹን ትቶ ወክ ማድረግ …
በተለይ ለማ መገርሳ “ወሎዬው ዶ/ር አረጋ ዘመዱም ይሁን ወዳጁ በኦሮሚያ ያሉ ድርጅቶቹን የሚመራ ኦሮሞ አጣሁ ካለ ፋብሪካዎቹን ወሎ ወስዶ ይትከላቸው” ማለቱ እንደ ጀግንነት ተቆጥሮለታል።
ዶ/ር አረጋ ተሰናበተ አብነት ገብረመስቀል ኦሮሞነቱን ዘወድ አድርጎ በሚድሮክ ላይ ነገሰ። ወዲያው ፒያሳ ካለው መሬት በቀር በአዲስ አበባ የተቀሙት መሬቶችም ሆኑ በኦሮሚያ በቄሮ እጅ ስር እንዲቆዩ የተደረጉት ድርጅቶችም በማንኛውም የስራ መስክ ቅድሚያ እድሉ ለቄሮ እንዲሰጥ በመስማማት ለሼሁ ተመለሱ።
ለፒያሳው መሬት ማካካሻ የተዘጋጀው መሬት ዳቦ መጋገሪያ መጋዘን እንዲሰራበት በሚል አብነት ገብረመስቀል ከታከለ ኡማ እጅ ተረከበው። አንድ እውነት ልንገርህ ለማ መገርሳ “አምጥተን ያሰፈርናቸው ከተማ መኖር ቢቸገሩም ጥቂት ጊዜ ነው፤ ለፓለቲካውም ለኢኮኖሚውም ከተማን መያዝ ወሳኝ ነው ብለን ከሶማሌ የተፈናቀሉትን አስፍረናል፤ ዴሞግራፊውን እየቀየርነው፤ አልሰራችሁም ልንባል አይገባም ለኦሮሞ እየሰራን ነው” ሲል አባ ገዳዎችን እና ካድሬዎችን ሰብስቦ የተናገረው ሾልኮ ወጥቶ መጋለጡ ታስታውሳለህ።
 የስራ መስኩ ሌላ እንዳይመስልህ በለማ ቃል መሰረት አፓርታይዳዊ ቅጥር ተፈፅሞበታል። የታቀደውን ልንገርህ መንግስት በቅርቡ በተናገረው መሰረት በ4.6 ቢሊዬን ብር የሚያመጣውን ስንዴ 60% ደጉሞ ወደነ አብነት መጋዘን ያስገባዋል በከተማው ያሉ ከ1ሺህ አምስት መቶ በላይ ዳቦ ቤቶች (ሸዋ ዳቦን ጨምሮ) ከጫወታው ይወጣሉ።
በቅርቡ በኪራይ ቤቶች ስር ያሉ የንግድ ቤቶች እስከ 200% ኪራይ ተጨምሮባቸው ጮህው አልቅሰው የሚሰማቸው አጥተው ቤቱን እያስረከቡ ነው። ኮንደሚንየም ብቻ ሳይሆን በኪራይ ቤቶች ስር ያሉት የንግድ ተቋማትም ሆኑ መኖሪያ ቤቶች በብርሃን ፍጥነት እየተሸጋገሩ ነው።
“እውነት ነው ታከለ ኡማ ጥሩ አሻጋሪ  ወጥቶታል !”
ዛሬ ደግሞ በአሀጫሉ እና በሱሌይማን ደደፎ በኩል በተሰጠው አጀንዳም ሆነ በአባይ ግድብ ተከልሎ የሰራው ዘረፋ ሲጋለጥ ህዳር ላይ ሥራ ይጀምራል ያለውን የዳቦ መገገሪያ ዛሬ ሐምሌ መባቻ ላይ እንዲመረቅና አጀንዳ እንዲቀለበሰ ካሜራና ጋዜጠኞቹን ሊያሰማራ ተሰናድቷል። በተረኝነት ኮንደሚንየም ዘርፎ ፣ የአዲስ አበባን መሬት በአፓርታይዳዊ ስርዓት ተቀራምቶ ” ዳቦ ከገበያ ዋጋ ቀንሼ የምሸጥበት መጋገሪያ መጋዘን ሊመረቅ ነው እልል በሉ “. ሊለን ነው። አወይ አለማፈር!!!
Filed in: Amharic