>
5:13 pm - Monday April 19, 9137

ከንቲባ ታከለ ኡማን ፍርድ ቤት እናቆመዋለን!! (የአዲስ አበባ ባልደራስ)

ከንቲባ ታከለ ኡማን ፍርድ ቤት እናቆመዋለን!!

የአዲስ አበባ ባልደራስ
ስንታየሁ ቸኮል

 

 *  ለአዲስ አበባ ድሆች እንጠይቃለን !በሪከርድ ይመዘገባል ነገ ሂሳብ ያወራርዳል።
የአዲስ አበባ ነዋሪ አፈር ልሶ ቆጥቦ በሰራው ቤት  ከዝዋይ አምቦ እና ባሌ የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ሰራተኞች አደራጅተህ የሰዉ ቤት ማደል ከወንጀልም  በላይ አደገኛ ዘረኝነት ነው። የተሰጡ የኮንዶሚኒዮም ቤቶች በአስቸኳይ ይታገድ በማለት በፍ/ቤት እንጠይቃለን ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ በፍትህ አደባባይ እናቆመዋለን።
በአዲስ አበባ ነዋሪ የተጫነ ሕገ ወጡ የከተማው አስተዳደር ም/ከ ታከለ ዑማ  ያለ ህዝብ ምርጫና  ይሁንታ በኦህዴድ ፍቃድ በከንቲባነት  ከተቀመጡበት ዕለት አንስቶ  በመመሪያ ለአንድ ብሔረሰብ አባላት ከዛም በታች ለፓርቲ ተቧዳኝ ግለሰቦች ያስተላለፏቸው የኮንዶሚኒዮም የጋራ መኖሪያ ቤቶች በፍትህ አደበባይ እንፋረደዋለን ሕግ ካለ የተሰጡት መኖሪያ ቤቶች በአስኳይ ይታገድ! ጥያቄ እናቀርባለን።
አዲስ አበቤዎች ከዕለት ቀለባቸው ቀንሰው በቀን አንዴ አየበሉ ነገን የተሻለ ለማድረግ  ያደረጉት የአንድ ጎረምሳ ዕድሜ ተስፋ ዛሬም በሕገወጡ ከንቲባ ታከለ ዑማ መሪነት ያለሃፍረት መንገዱን ስቷል ዘረኝነቱ ተባብሷል።
እስካሁን ድረስ በሕገወጡ ከንቲባ ከ33 ሺህ በላይ በአዲስ አበቤዎች የቁጠባ ብር የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለተፈናቃይ #አርሶ አደሮችና #ለብልፅግና ፓርቲ ታማኝ ቅጥረኞች ያለሀፍረት ተስጥቷል።
ዛሬም!  ሕገ ወጡ ከንቲባ ታከለ ዑማ 10 ሺህ ብር ለዕጣ በማስከፈል ከ14ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች #ከቦሌ ፕሮጀክት 4 በቀን 16/10/2012( በትላንትናው ዕለት ) ከ 14 ሺ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች #ለኦሮምያ ቢሮ ሰራተኞች ባሳፋሪ ሁናቴ ተሰጥቷል።
በመሪ ሳይት በቦሌ ቡልቡላ  በሰንጋ ተራ (ሜክሲኮ) እንዲሁም በሌሎች ሳይቶች ገንዘብ ከፍለው ለዓመታት አየተጠባበቁ ያሉ የአዲስ አበባ ከተማ ኗሪዎችን በመናቅ ለተመረጡ የአንድ ብሔረሰብ አባላት ለመስጠት ዝግጅቱ እንደተጠናቀቀ መረጃው ደርሶናል።
በመሆኑም የአገሪቱ ፍ/ቤቶች ይህንን ፍፁም ሕገ ወጥ ድርጊት ስለ ድሆች እንባ ሲል ባስቸኳይ የዕግድ ትዕዛዝ በማውጣት እንዲያስቆም  እንጠይቃለን!!
በዚህ የቅሬታ አቤቱታ ላይ የበኩልዎን ይወጡ
ባልደራስ በአዲስ አበባ ውስጥ አምስት ቢሮዎች ያሉን ሲሆን ለእርስዎ በሚቀርብዎ ቢሮ በበምጣት መመዝገብ ይቻላል።
1.ስድስት ኪሎ ቢሮ፡- መድሃኒአለም መስካይዙና አካባቢ  ብራይት ኮሌጅ 3ኛ ፎቅ  ስልክ፡- 09 05 00 25 25
2.መገናኛ  ቢሮ፡- ገነት ኮሜርሻል 6ኛ ፎቅ
  ስልክ ፡- 09 19 39 50 02
3.ሜክሲኮ ቢሮ፡-  ልደታ ባልቻ ሆ/ል አህመድ የገበያ አዳራሽ 3ኛ ፎቅ   ስልክ፡-  09 62 72 52 84
4.መርካቶ ቢሮ ፡- መሳለሚያ እህል በረንዳ ውልና ማስረጃ 2ኛ ፎቅ   ስልክ ፡- 09 11 68 12 40
5.አቃቂ ቃሊቲ ቢሮ፡-   ወረዳ 8 ካፍደም 2ኛ ፎቅ     ስልክ ፡- 09 68 05 38 43
ለተጨማሪ መረጃ
ስልክ: 09  05 00 25 25/0963159763 ይደውሉ።
..”ለህዝብ ጥያቄ እንሰራለን! እንተጋለን!
____
Filed in: Amharic