ልጅ ወንድወሰን ተሾመ ኢጆሌ ነገሌ ከዲሲ
“በኦሮሚያ ምድር በአረመኔዎችና በአክራሪ ኦሮሞዎች ኦሮሞ ባለመሆናቸው ብቻ በአደባባይ ታርደው የተገደሉትን፣ እሬሳቸውን የተጎተቱት ወገኖቻችን እንዲሁም በእሳት ተቃጥለው ለሞቱት ወገኖቻችን ነፍሳችሁን በገነት ያኑርልን።”
ገና ምንም ሳይጀመር እርቅ ሽምግልና የሚሉ ሰዎች ይበልጥ እያሳዘኑኝ ነው ። ያልተነካ ግልግል ያውቃል እንደሚባለው ፣ ምናልባት የናንተ ቤት ስላልተንኳኳ ይሆናል ። የኔ ምንግዜም ጥያቄ በቦታው የሌሉ ፣ በጉዳዩ ውስጥ ምንም የማያውቁ ዜጎች በብሔራቸው ብቻ የተገደሉ ማን ጥብቅና ይቁምላቸው ? የኦሮሞ ፖለቲከኞች ከአንዴም ሁለት ሶስት ግዜ በሽማግሌ ሲታረቁ ቆይተዋል ። እነሱ በተሻኮቱ ቁጥር ሌላው መስዕዋትነት የሚከፍልበት አድክሞናል ።
ተወልጄ ያደግኩት አርሲ ነጌሌ፤ ነጌሌ አርሲ ነው፡፡ ይሄንን ነገር ለመጻፍና ላለመጻፍ ከራሴም ከሰውም ተሟግቻለሁ፡፡ ባንድ በኩል ነገር ማባባስ መሰለኝ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ንጹሀን ደማቸው ደመከልብ ሲሆን ዝም ማለት ተባባሪነት ወይም ግዴለሽነት ሆነብኝ፡፡ በሁለት አስጨናቂ ጥያቄዎች ተፋጠጥኩ፡፡ የማከብረው ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ፤ “ልጅ ወንድወሰን ይሄንን ባትጽፍ ነው ስህተቱ“ አለኝ፡፡ ቢያንስ ሳንጨማመር እውነቱን ብንጽፍ ግን የሚመለከታቸው ሁሉ እርምጃ ሊወስዱ ይችላሉ፡፡ ይሄ የተጻፈው፤ ለማስተማሪያ ነው፡፡ ለቂም በቀል አይደለም፡፡ ለጊዜውተበቃይ አላህ/እግዚአብሄር ነው፡፡
ፍጹም ባረገው አብሮ አደጋችን ነው፡፡ ለፍቶ፤ ጥሮ ግሮ ያደገ ልጅ ነው፡፡ ደግ፤ ርህሩህ ነው፡፡ በመጨረሻም ደግነቱ አስገደለው፡፡ ማክሰኞ፤ ሰኔ 23 ቀን፤የተወለደበት፤ እትብቱ የተቀበረበት ከተማ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደለ፡፡ የደሜን አስከሬን ለማዳን ብሎ፡፡ ደሜ ጎንደሬ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ ለአመታት አረቄ ነግዶ ባፈራው ሀብት ነው ቢዝነሱን የገነባው፡፡ አለም ምግብ ቤት፡፡ ቢዝነሱ በአመጸኞች ባንድ ቀን ወደመ፡፡ ንብረቱ ጦሱን ይዞ ቢሄድ ጥሩ ነበር፡፡አልሆነም፡፡ የሱንም የወንድሙንም ሕይወት በአሰቃቂሁኔታ ቀጠፉት፡፡ በገጀራና በመጥረቢያ ከትክተው፡፡ የደሜን አስከሬን ምድር ለምድር ሲጎትቱ ሲመለከት፤ አብሮ አደጋችን ፍጹም ባረገው “ተዉ እንጂ፤ ገደላችሁት ምናለ አሁን አስከሬኑን እንኳንብትተዉት“ ብሎ ጠየቀ፡፡ በመጥረቢያ ጭንቅላቱን ብለው የገደሉት፡፡
ቤተሰብ ከመፍራቱ የተነሳ፤ የልጃቸውን ግድያ በአጥር፤ በቀዳዳ አጮልቆ ከመመልከት ውጪ ምንም ማድረግ አልቻሉም፡፡ ወደኋላ ላይ፤ የነጌሌ ጎረቤት ከተሞች፤ አባወራዎች፤ ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን ጥለው ሲሸሹና ከኋላቸው ሲገደሉ እንመለከታለን፡፡ ለወትሮው፤ በጦርነት ሰዓት እንኳን ሴትና ሕጻን አይገደልማ፡፡ የኦሮሞም፤ የአማራም ባህል አይደለማ፡፡ በነጌሌና በዙሪያዋ የሆነው ግን ከባህልም፤ ከሕግም፤ ከሀይማኖትም ያፈነገጠ ነው፡፡ የሩዋንዳ ቅምሻ፡፡
ፍጹም እሱን እንደማይነኩት እርግጠኛ ነበር፡፡ ምክንያቱም የተወለደበት፤ ያደገበት፤ ቤተሰቦቹ የገነቧት ከተማ ነቻ፤ ነጌሌ አርሲ፤ አርሲ ነጌሌ፡፡ ይገድሉኛል አይደለም፤ ይቆጡኛል ብሎ አላሰበም፡፡ እነሱ ግን፤ ስልጣኔ ያልጎበኛቸው አረመኔዎች ናቸው፡፡ገዳዮቹን ማለቴ ነው፡፡ አይን የላቸውም፡፡ ከመካከላቸው አንዱ እጅ አያሳርፍ፡፡ ካሳረፈ፤ አበቃ፡፡ ሌሎቹ ሳያገናዝቡ፤ ሳይጠይቁ ይሰፍሩበታል፡፡ ይሄን የፈጸሙት፤ ከተማው ውስጥ ታይተው የማታወቁ ባእዶች ናቸው፡፡ ይሄን ኦሮሞ አይፈጽምም፡፡ እነዚህ ኦሮሞዎች አይደሉም፡፡ በምግባራቸው፤ በፈቃዳቸው ከኦሮሞነት ተገንጥለው ወጥተዋል፡፡ ስለዚህ ፍጹምን ገደሉት፡፡ መግደልም ብቻ አይደለም፤ እንደሰማሁት ከሆነ አስከሬኑን በገመድ ጎተቱት፤ ስልክ እንጨት ላይም ሊያንጠለጥሉት ታገሉ፡፡ ይሄ ሁሉ የተከሰተው ነጌሌ አርሲ ነው፡፡ የቀድሞው ምስራቅ ሸዋ ዞን፤ ምእራብ አርሲ ተብሏል አሁን፡፡
አስጨናቂ፤ ከሰውነት ጎዳና ወጥቶ፤ አተላ አገላብጦ ከብት ቀልቦ፤ እንደምንም ተሟሙቶ ቢዝነስ ከፈተ፡፡ ድርጅቱን እንዳለ አቃጠሉበት፡፡ አባቱንም ከአመታትበፊት በዚህ ሁኔታ እንደገደሉበት ሰምቻለሁ፡፡ እነሆ ነገሌ፤ ረቡእ ሰኔ 25 በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ 4 ሰዎች ቀበረች፡፡ ከተማው አዘነ፡፡ እንደራሄል እንባውን ረጨ፡፡ መጽናናትን ግን አላገኘም፡፡ የሚያጽናናው #መንግስት፤ የሚተማመንብት #ሕግ #የለም፡፡
ንብረታቸው የተቃጠለው የትየለሌ ናቸው፡፡ ይሄ በነጌሌ ብቻ የተከሰተው ነው፡፡ በጎረቤት ከተሞች የተከሰተው ግድያ እጥፍ ነው፡፡
እስካሁን ያለው የሙት እና የቁስለኛ ዝርዝር ይህንን ይመስላል:-
ቦታ ቁስለኛ የሞተ
አዲስ አበባ 42 13
አምቦ 115 27
ዝዋይ 17 8
ሻሸመኔ 23 9
አሰላ 29 13
አዳማ 11 9
ባሌ 21 11
ባቱ 17 6
ጊምቢ 4 2
ወሊሶ 10 9
ቢሾፍቱ 64 17
ሐረር 11 6
ጅማ 3 2
ነቀምት 12 5
ድምር 379 137
ለዚህ ሁሉ የዘር ጭፍጨፋ ተዋናይ የሆኑ ሁሉ ለፍርድ ይቅረቡ!!
ህዝቡስ እስከመቼ እየተሳቀቀ ይኖራል ? መንግስት እንደ መንግስትነቱ የዜጎቹን ደህንነት ማስጠበቅ አለበት ።ይህ የዘር ፖለቲካ፣ የዘር ሕግ መንግስት፣ የዘር አወቃቀር ውጤት ነው፡፡
ለሞቱት ነብስ ይማር
ለተጎዱት ቁስላቸውን የውሻ ቁስል ያድርግልን !
ሀገራችንን ህዝባችንን ሰላም ያድርግልን