>

ለጃዋር ማጣፈጫ  እነ እስክንድር የጭዳ ዶሮ ሆኑ!!! (እንግዳ ታደሰ)

ለጃዋር ማጣፈጫ  እነ እስክንድር የጭዳ ዶሮ ሆኑ!!!

እንግዳ ታደሰ

• መንግስት ሆይ !!አማካሪዎችህን መርምር ! የመንግስትህን ጓዳ አጽዳ ! ግብጽ በተሽነቆረው ቀዳዳ ገብታ ጀሌዎቿን እያሰማራች አገር በምታስበጠብጥበት በዚህ ወቅት፣ በፈጠራ ድርሰት ከአዲስ አበባ ህዝብ ጋር አትናቆር ! ከአማራ ህዝብ ጋር አትላተም ። ከጉራጌ ህዝብ ጋር አትቃቃር ።  በፖለቲካ የአካሄድ ቅጥፈት አገርን ማረጋጋት አይቻልም!
*    *    *
 

• የቸገረ ነገር የጠፋ ለመላ ፩

 
 ማንም ሰው እንደዚህ የሹም ዶሮ ሰው እንደልቡ የፈለገውን የተናገረ የለም ።  ስለ- አዲስ አበባ ህዝብ መብት እስክንድር የድርሻውን ፥ የዜግነቱን ሲናገር ግን ፣ ባልደራስ ከሚባለው ጋር ግልጽ ጦርነት እንገባለን ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ገና ከጅምሩ ነበር ።
የሹም ዶሮውን ጃዋር ማንም #እሽሽሽሽ ሳይለው ፥ ጫፉን ማንም ሳይነካው በአዲስ አበባ የራሱ ዘብ ተመድቦለት ሲፏልልና ሲቀብጥ ፣ ህዝብ! ኧረ ተዉ ሲል  የሰማው ማንም የለም፣ ጭራሽ ወንድማችን፥ስኮርቲ ጎማ ሲባልለት ተከርሟል። ነገ የፈረደበት በሬ ተጎትቶ ፥ የአባ ገዳ ሽማግሌዎች ገብተውበት ይህ ሰው በሽምግልና እንደሚለቀቅ አልጠራጠርም። ያኔ #አሽቃባጩ ! ስለዉነት የማይጨነቀው ፥ ስለህግ የበላይነት ደንታ የሌለው ፣በሞቀበት የሚቆመውን ማየት ነው ።
ኢትዮጵያ አንድነቷ ተጠብቆ እንዳትበታተን የሚፈልገው ብዙ ሚልዮን ህዝብ ነገሮች በርደው ! አገር በሰላም እንድትኖር ይፈልጋል ። ነገር ግን በዚህ ሚዛናዊነትን ባልጠበቀ የፖለቲካ አካሄድ  በወታደራዊ ዩኒፎርም ቢወጡ ፥ አማላይ ቃላትንም ቢጠቀሙ ፣ ይህን ክፍል ለማስደሰት ከነኛ’ ክልል ሰዎችም የተወሰኑትን ትንሽ ቆሎ ይዘህ ካሻሮ ተጠጋ ፖለቲካ እንደባልቅ የፖለቲካ ቁማር ለጊዜው ውጥረቱን ቀለል ያደርግ ይሆናል እንጂ ! እዚህ ጋር ቋጥሮ እዚያ እንደመፍታት ነው ።
የሃገሪቱ ቁልፍ ችግር ሽቅብም ተወጣ ቁልቁል ! #ህገመንግስቱ ነው ። በህገ መንግስቱ ደግሞ ህወሃትም ፥ አብይም ፥ ጃዋርም ፥ ኦነግም በፍጹም አይደራደሩም ። ለዚህም ምስቅልቅል መፍቻ ነገ ይዘውልን የሚመጡት እንደ መፍትሄም የሚጠቅሱልን አንቀጽ የወያኔውን ህገመንግስት ነው ። በዚህ አንድ ናቸው። በሬው ተጎትቶ ሲታረድ በነሱ መሃል ለጊዜው እርቅ ይወርዳል ። እሽቃባጩ ግን ዳር ይወጣል ።
      !! ሰልስቱ ብየ የህሊናዬን ፈጣሪ በሰጠኝ ነጻነት ቃሌን በነጻነት ገልጫለሁ ። የተመቻችሁም ያልተመቻችሁም ሰላም ሁኑ። ጨረስኩ !! ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ያስባት።
መንግስት ሆይ ! አሁንም አማካሪዎችህን ፈትሽ ! ውስጥህን አጥራ ! የእብድ ገላጋዮችን ጭፍራና ጭብጨባ አታዳምጥ ! ቆዳው እየተመተረና ! እየተገደለ ያለ ህዝብ ይዘህ የተረጋጋ አገር መፍጠር አይቻልም ።

• የቸገረ ነገር የጠፋ ለመላ ፪

 
ቀደም ሲል ባሳሰበኝ የአገራችን ጉዳይ፣ መንግስት ሆይ ! አማካሪዎችህን አጽዳ ! የእውር ድንብር አትጓዝ ! #ብራቾ እንደተሰበረበት መኪና ስትሄድ አትወላከፍ ! በሚል ስጋቴን ገልጨ ነበር ።
ይኽው እንደተባለው የፌዴራል መንግስቱ የፖሊስ አካል ፣ መንግስትን የሚያህል ታላቅ ተቋም እየመራ ፣ #አብን ከባልደራስ ጋር ሁኖ የአዲስ አበባን ወጣት ካኒቴራ በማልበስ ለብጥብጥ ወጥቶ ነበር ያለውን ክስ ፣ ስህተት ነበር በማለት ለአብኖች ገልጿል ።
አገር በብላኔ አትመራም ። አንድ ከትልቅ የመንግሥት ተቋም ከባድ ጉዳት የሚያደርስ የስም ማጥፋት ከተካሄደ በኋላ ስምን ለማደስ ጊዜ ይፈጃል ። ጊዜ መፍጀቱ ብቻ ሳይሆን ለኦሮሞ ህዝብ የሚሰጠው ምስል ከባድ ነው። አብን መንግስት በይፋ ወጥቶ በአደባባይ ይቅርታ እንዲል ማሳሰብ አለበት ።
የውስጥ ይቅርታ ነገም የፈለጉትን እየሰሩ አገርን ማበጣበጥ ነው ። ኢትዮጵያ ! ግብጽን የሚያህል የውስጥ አንድነቷን የምታናጋ ጠላት አገር ከፊቷ አስቀምጣ !የነታከለን ሙስና ለምን አጋለጠ በሚል ባልደራስም ላይ እየተካሄደ ያለው ክስ በገለልተኛ አካል ተጣርቶ ቶሎ መፍትሄ በመስጠት ወደ ተረጋጋ ሁኔታ አገሪቱን መመለስ አለብት ። መንግስት ሆይ ውስጥህን ፈትሽ ! አማካሪዎችህን ለይ !

•የቸገረ ነገር የጠፋ ለመላ ፫

 መንግሥት ተብየው ከማን ጋር እንደተሰለፈ በማይታወቅበት ሁኔታ #ብራቾውን እንደሰበረ መኪና እየተወላከፈ ይጓዛል ። በዚህ ሁኔታ ይህን ክፉ ጊዜ እንዴት እንደምናልፈው የሚያውቀው ፈጣሪ ብቻ ነው!
 
በዚያ ታላቋ የአገራችን ጠላት ግብጽ አለች ። በዚህ የኦሮሞ ጽንፈኞች አማራውንና ጉራጌውን አርደው ስጋውን ከልኳንዳ ቤት ያንጠለጥሉታል።
 የኦሮሞ ጽንፈኞች በየመንደራችን ተደራጅተው እየመጡ ተቋማትን ሲያፈራርሱ  እና ንብረት ሲያቃጥሉ ለምን ብሎ የወጣውን የአዲስ አበባ ወጣትና ህዝብ በተጭበረበር ክስ #አብንና_ባልደራስ ካኒቴራ አዘጋጅተው ወጣቱ የዘር ግጭት እንዲፈጥር እያነሳሱ ነው በሚል የውሸት ትርክት መንግስት እየከሰሰ ነው ።
ትንሽ ቆሎ ይዘህ ካሻሮ ተጠጋ እንዲሉ ፣ ኦፒድዮ ብልጽግና መገኛውና ህዝባዊ መሰረቱ የሆነውን የኦሮሞ ክልልን ህዝብ ለማማለል በሚመስል መልኩ የሃይል ሚዛኑን ለማስጠበቅ ሲል #አብንና_ባልደርስን የጭዳ ዶሮ በማድረግ በፌዴራል ፖሊሱ በኩል ክሱን እያዘነበ ነው ።
ይህ የፈጠራ ክስ አካሄድ በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ብዙ ዋጋ ያስከፍለዋል ። የኦሮሞ ጽንፈኞችን አረጋጋለሁ ብሎ አብንና ባልደራስ ላይ የፈጠራ ክስ መፍጠር እዚህ ሲቋጥሩ እዚያ እንደመፍታት ነው ። ማንም ሰው ፥ ማንም ድርጅት ከህግ በላይ ሊሆን አይችልም። መንግስት ጥፋተኛውን አጣርቶ ለህግ የማቅረብ መብቱ የተጠበቀ ነው ። ከዚያ ውጭ ግን በፖለቲካዊ ቁማር ፣ ተሳትፎ የሌላቸውን አካሎች ማጣፈጫ ማድረግ አላዋቂነት ነው ።
መንግስት ሆይ !!አማካሪዎችህን መርምር ! የመንግስትህን ጓዳ አጽዳ ! ግብጽ በተሽነቆረው ቀዳዳ ገብታ ጀሌዎቿን እያሰማራች አገር በምታስበጠብጥበት በዚህ ወቅት፣ በፈጠራ ድርሰት ከአዲስ አበባ ህዝብ ጋር አትናቆር ! ከአማራ ህዝብ ጋር አትላተም ። ከጉራጌ ህዝብ ጋር አትቃቃር ።  በፖለቲካ የአካሄድ ቅጥፈት አገርን ማረጋጋት አይቻልም ።
የሰው ልጅ ታርዶ ስጋው ልኳንዳ ቤት ሲሰቀል የሚያይና የሚሰማ ህዝብ ሆ ! ብሎ ሊነሳብህ ይችላል። ወዳጅና ጠላትህን ለይ !!   ጨረስኩ !!
Filed in: Amharic