>

በኦሮሚያ ዜጎች በአዲስ ጥቃት ስጋት ቤታቸውን ጥለው እየወጡ ነው!!! (ህብር ራድዮ)

በኦሮሚያ ዜጎች በአዲስ ጥቃት ስጋት ቤታቸውን ጥለው እየወጡ ነው!!!

ህብር ራድዮ

የክልሉ ልዩ ኃይል አባላት ጭምር.”ጥላችሁ ውጡ ቄሮ ይመጣል” እያሉ ማስፈሪያውን ያሰራጫሉ…!!!
በኦሮሚያ ክልል ሰሞኑን ጥቃት ከተፈጸመባቸው አንዱ ሻሸመኔ፣ዝዋይ ዶዶላ፣ባሌ ከጥቃት የተረፉ ጥላችሁ ውጡ ቄሮ ይመጣል የሚል ማስፈራሪያ በክልሉ አንዳንድ ልዩ ኃይል አባላት ጭምር በመተላለፉ ዜጎች በጭንቀት እና ፍርሃት ውስጥ ሲሆኑ ሽሽት የጀመሩም አሉ።
ከሻሸመኔ ለጊዜው ወደ ሀዋሳ እየሄድን ነው። አዲስ አባባም የሚሄዱ አሉ።የት እንደሚሄዱ ግራ ተጋብተው የተቀመጡም አሉ ሲሉ አስተያየታቸውን ያደረሱን አሉ።
ያሳዘናቸው ህግ እና ሥርዓት ማስከበር የነበረባቸው አንዳንድ አመራሮች እና የልዩ ኃይል አባላት የቄሮ መግለጫ ወጥቷል በሚል ጉዳት እንዳይዳርስባችሁ ለቃችሁ ውጡ እየተባሉ መሔጃ ማጣታቸውን ጠቁመዋል።
መንግሥት የዜጎችን ጩኸት ሰምቶ የሚያዳርገው የለም ዛሬም ተባባሪዎቻቸው አመራር እና ጠመንጃ ይዘው አሉ ሲሉ ቅሬታ አሰምተዋል።
እነ አቶ በቀለ ገርባ ከዚህ ቀደም ኦሮምኛ ቋንቋ ካልቻለ አትገበያዩ፣ጥለው እንዲወጡ አድርጉ ማለታቸው አይዘነጋም።
በኦሮሚያ ዘር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፣ዘረፋና ውድመት በአንዳንድ የአካባቢው ባለስልጣናት እና የጸጥታ ሰዎች የተደገፈ እንደናበር አስቀድመን መዘገባችን ይታወሳል።
Filed in: Amharic