>

በኦሮሚያ የተካሄደው ጭፍጨፋ 10 ባህሪያት፣ (ኤርሚያስ ለገሰ)

በኦሮሚያ የተካሄደው ጭፍጨፋ 10 ባህሪያት፣

ኤርሚያስ ለገሰ

፩: ጨፍጫፊዎቹ ለተራዘመ ጊዜያቶች ሲዘጋጁ ነበር። ጥቃቶችንም ሲፈጽሙ ነበር። (ቢቢሲ)
፪: ጨፍጫፊዎቹ የሚገድሉአቸውን ሰዎች የስም ዝርዝር አስቀድመው ይዘው ነበር። (ቢቢሲ)
፫: ጨፍጫፊዎቹ ማንነታቸው እንዳይታወቅ ራሳቸውን ሸፍነው ነበር። (ቢቢሲ)
፬: ጭፍጨፋው ብሔር ተኮር ነው። (ቢቢሲ)
፭: ጭፍጨፋው ኃይማኖት ተኮር ነው። (ቢቢሲ)
፮: ጭፍጨፋው እጅግ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በገጀራ፣ በስለትና የጦር መሳሪያ የተፈፀመ ነው። (ቢቢሲ)
፯: ጭፍጨፋው ቤተሰብን ሙሉ ለሙሉ የማጥፋት አላማ ነበረው። ዝዋይ አንድ ሙሉ ቤተሰብ ተጨፍጭፏል(ዘሀበሻ)፣ ቀርሳ ከአንድ ቤተሰብ ሶስት ተጨፍጭፏል።(ቢቢሲ)
፰: የመንግስት ባለስልጣናት ጭፍጨፋው ማንነትና ኃይማኖት ተኮር መሆኑን ክደዋል። (ቢቢሲ)
፱: የፀጥታ ሀይሎች ጭፍጨፋው በሚካሄድ ሰአት መድረስ ባለባቸው ሰአት አልደረሱም። ከመጡም በኃላ “ገዳዬቹ ዳግም አይመጡም!” ብለው ጥለዋቸው ሲሄዱ ጨፍጫፊዎቹ ተመልሰው በመምጣት ጭፍጨፋውን አካሂደዋል። (ቢቢሲ)
፲: የመንግስት አስተዳደሩ የመፍትሔ አካል አልነበረም። ሰለባዎችንም ዞር ብሎ አልጠየቃቸውም (ቢቢሲ)
የፌዴራል መንግስትና የክልሉ መንግስት በክልሉ ስለደረሰው ጭፍጨፋ በዝርዝር አያቀርቡም። እንደ ሬዲዬ ፋና ያሉ የፓርቲ ሚዲያዎቹም ሆነ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን አይተው እንዳላዩ፣ ሰምተው እንዳልሰሙ ሆነዋል። ኢንተርኔት ሙሉ ለሙሉ ተዘግቷል።
Filed in: Amharic