>
5:13 pm - Saturday April 19, 0555

ባለፉት 2 ዓመታት ያሳለፍናቸው ጭፍጨፋዎችና መፈናቀሎች ሲታወሱ… (ዮናስ ሀጎስ)

ባለፉት 2 ዓመታት ያሳለፍናቸው ጭፍጨፋዎችና መፈናቀሎች ሲታወሱ…

ዮናስ ሀጎስ

1 – በሶማሌ ክልል ከ800 ሺህ በላይ ኦሮሞዎች የተፈናቀሉበትና ያንን ለመበቀል በኦሮሚያ ክልል የተካሄደው ሶማሌዎችን የማስወጣት ዘመቻ በሁለቱም ክልሎች ልዩ ሐይሎች የታገዘ ነበረ።

 2- በቡራዩ ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ የተቀጠፉበት፣ ሺህዎች የተፈናቀሉበት ዘመቻ በልዩ ሐይል ፖሊሶችና የአካባቢው መስተዳድር የታገዘ ነበረ።
3 – በመተከል ቁጥራቸው በውል ላልታወቀ የአማራ ክልል ተወላጆች ሞት የቤኒሻንጉል መስተዳድሮች ጭፍጨፋውን ሲያስተባብሩ እንደነበረ ቪኦኤ አረጋግጧል። በምላሹም የአማራ ልዩ ሐይል የአፃፋ እርምጃውን ከማስተባበርም ባሻገር ተሳታፊ ሆኖበታል።
4 – በቅማንት እና አካባቢዋ የሚካሄደው ጭፍጨፈሰ ብዙውን ጊዜ የትግራይና አማራ ክልል ልዩ ሐይሎች በወኪል የሚያካሂዱት ጦርነት እንደሆነ ይታወቃል።
 5- ከ1 ሚልዮን በላይ የጌድዮ ነዋሪ የተፈናቀለው የአካባቢው መስተዳድር ቤት ለቤት እየዞሩ «ከዚህ ካልለቀቃችሁ ትታረዳላችሁ!» በማለት ነዋሪዎቹን በማስፈራራትና ባስ ሲልም ጭፍጨፋ ለሚፈፅሙት ሽፋንና ከለላ በመስጠት እንደሆነ የጀርመን ድምፅ ስለ ጌድዮ ተፈናቃዮች በሰራው ዘጋቢ አጋልጧል። የፌደራል መንግስቱም የጌድዮ ተፈናቃዮችን በመክበብ እና እርዳታ እንዳይገባላቸው በማድረግ ለብዙ ወራት ተፈናቃዮቹን በረሐብ የጨረሰበት ሂደትም አንዱ የታሪካችን አካል ሆኖ ተመዝግቧል።
6 – በድሬዳዋና ሐረር ከማንነት ጋር በተያያዙ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች ሙሉ በሙሉ የሚቀናበሩት በመንግስት አስተዳደር ሰራተኞች ነው።
7 – ጃዋር ተከበብኩኝ ብሎ የ86 ሰዎች ነፍስ ባለፈበት ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ የብልፅግና አመራሮች ዝርዝር ይዘው በመጠቆም፤ ልዩ ሐይሉ ደሞ ባላየ በማለፍና ጀርባውን በመስጠት ለሟቾች ቁጥር 86 መድረስ የበኩላቸውን ሚና ተጫውተዋል።
8- አሁንም በኦሮሚያ ክልል መንግስት እስካመነው 166 ድረስ የሚደርሱ ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ ሕይወታቸው ስለማለፉ እየተዘገበ ነው። መንግስት ኢንተርኔት በማጥፋቱ እስካሁን እየተሰራጨ ያለው ዘገባ ሁሉ መንግስት እንዲሰራጭ የፈለገው ስለመሆኑ ጥርጥር የለውም። ነገር ግን ኢንተርኔቱ ተከፍቶ ሁሉም ወገን የጠራ መረጃ ማነፍነፍ ቢጀምር የኦሮሚያ ብልፅግናዎችና ልዩ ሐይሎች ከዚህ ጭፍጨፋ ጀርባ ረዘም ያለ እጃቸው እንደሚገኝበት ምንም ጥርጥር የለውም።
•°•
ምስል በኦሮሞና ሶማሌ መሐከል በነበረው ግጭት ለሞቱ መታሰቢያ የሻማ ስነ ስርዓት
Filed in: Amharic