>

ከትላንት እስከ ዛሬ ማቆሚያ የሌለው ጭካኔና ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ልያውም ሴት ልጅ ላይ - እስከ መቼ ...???  (ናፍቆት እስክንድር)

ከትላንት እስከ ዛሬ ማቆሚያ የሌለው ጭካኔና ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ልያውም ሴት ልጅ ላይ – እስከ መቼ …??? 

ናፍቆት እስክንድር

አስቴር ስዩም በህወሀት እስር ወቅት የሆነችውን እንደጎርርፍ በሚወርደው እንባዋ ውስጥ ገልጻልናለች። የ1 አመት ከ6 ወር ልጇን ጥላ ታስራለች። ስትወጣ ልጇ አለምዳት ብሎ ተጎድታ ነበር። ዛሬም የ1 አመት ከ2 ወር ልጇን ጥላ ዳግም እስር ላይ ናት…
 
የባልደራስ ለእውነተኛዲሞክራሲ ፓርቲ አባል የሆነችው አስቴር ስዩም ሰኔ 26/2012 መታሰርዋ ይታወሳል። ይሁን እንጅ  ፣ አስቴር ከተያዘችበት ዕለት አንስቶ  እስከዛሬ (ሐምሌ 1/2012)  መቀየሪያ ልብስም ሆነ ስንቅ ሊገባላት እንዳልቻለ ከስፍራው የደረሰን ዜና ያስረዳል። የአስቴር ስዩም ቤተሰቦች በየዕለቱ ስንቅና ቅያሬ ልብስ ይዘው ማዕከላዊ ቢመላለሱም ፣ ጠባቂ ፖሊሶች “አንቀበልም” እያሉ እንደሚመልስዋቸው ገልፀዋል።
 ባለቤቷ እንኩዋን እንዲጠይቃት ካለመፈቀዱም በላይ እስካሁን ፍርድቤት አልቀረበችም።
አስቴር ስዩም ከዚህ በፊት ጡት ከሚጠባ ልጇን ነጥለው ለ 4 ዓመታት አሰቃቂ ግፍ ተፈፅሞባት መታሰሯ ይታወሳል።  በእስር ላይ እያለችም  እናቷን  በሞት ማጥትዋ አይዘነጋም።
* በተያያዘ ዜና:- ፩
ከ አዲስ አበባ አሁን የደረሰን መረጃ በላፍቶ ክ/ከተማ የባልደራስ ፅ/ቤት ሰብሳቢ  የሆኑት እና በ አስቴር ስዩም ስር የሚሰሩት አቶ ቢኒያም መታሰራቸውን እና ሌላ የባልደራስ አመራር አቶ ሳሙኤል የተባሉ እስካሁን የት እንዳሉ አይታወቅም በሌሎች የባልደራስ አመራሮች እና አባላት ላይ የእጅ ስልካቸው ላይ እየተደወለ ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው  እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
ዜና:- ፪
–  እስካሁን ባልደራስ ባጣራው መረጃ 10 የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መገደላቸውንም ጨምረው ገልፀውልናል ሌሎች መረጃዎችን እየተከታተልን እናቀርባለን
Filed in: Amharic