>

በኢትዮጵያ እየሆነ ያለው ነገር ለሰሚው ግራ ነው!!! (ሉሉ ከበደ)

በኢትዮጵያ እየሆነ ያለው ነገር ለሰሚው ግራ ነው!!!

ሉሉ ከበደ

* ” መከላከያ ደርሶ ባያከሽፈው ኖሮ ጉዳቱ ከዚህ የከፋ ይሆን ነበር ” ለሚለን ቧልተኛው ኮሚሽነር …ሻሽመኔ’ ኮ ወድማለች የለችም እኮ… ከዚህ በላይ አጥፊዎቹ ምን እንዲያደርጉ ነበር የተፈለገው??? 
 
ገጀራ ፤ መጥረቢያ ፤ አጠና ፤ ድንጋይ ፤ ጠመንጃ ፤ ታጥቆ ፤ አስቦ ፤ አቅዶና ተዘጋጅቶ ፤ ሀይል አሰባስቦ ፤ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ወታደራዊ ጥቃት መፈጸም ፤ የነዳጅ ማደያዎችን በመቆጣጠርና ነዳጅ እየቀዱ በማመላለስ ፤ የዜጎችን መኖሪያ ቤቶች፤ የንግድ ተቋማትን  ፤ መጋዘኖችን  ማቃጠል ፤ የተቃውሞ ሰልፍ ሳይሆን በእቅድ የሚመራ ወታደራዊ ጥቃት ነው ። መንግስት ባለበት አገር ውስጥ የህዝብና የሀገር ጠላት የሆነ ወገን ያቀደውን የጥፋት እርምጃ ከውኖ  እስኪያበቃ የሀገርና የህዝብን ደህንነት እንዲጠብቅ ደሞዝ የሚከፈለው ጦርሰራዊት ፤ ፖሊስ ሰራዊት ፤ ምንም አይነት እርምጃ ሳይወስድ የሚገኝበት ምክንያት ድርጊቱ ሲከናወን እንዳይንቀሳቀስ ትዛዝ ሲሰጠው ብቻ ነው ። ወታደርም ሆነ ፖሊስ ከበላይ ትዛዝ ከተሰጠው ይፈጽማል ። ወታደርም ሆነ ፖሊስ አድርግ ሲባል ያደርጋል ፤ አታድርግ ሲባል አያደርግም ።
 ሁለቱም ሀይሎች በህዝብ ላይ አደጋ የሚያስከትል ድርጊት እንዲፈጽሙ ትዛዝ ቢሰጠቸው ትዛዙን ያለመፈጽም ህጋዊ መብት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ በኢትዮጵያ እየሆነ ያለው ነገር ለሰሚው ግራ ነው ፡፡
አሁን የኢትዮጵያ ህዝብ የተስማማበት ነገር ፤ የሀጫሉ ግድያ የታቀደና ብዙም የታሰበበት ነው ፡፡ በሴራ ፖለቲካ የካበተ ልምድ ባላችው የትግሬው ነጻ አውጭ ሰዎችና ጭካኔና ክፋት እንጂ እምብዛም እውቀትና ብልሀት ወኔም እንደሌላቸው የሚነገርላቸው ጽንፈኛ የኦሮሞ አክራሪዎች በግብጽ ዶላርና ደህነነት በመታገዝ ያደረጉት እንደሆነ መገመት አግባብነት አለው ፡፡
አንድ ጊዜ ይሁን ፤ ሁለትም ጊዜ ይሁን ፤ ባለፉት ሁለት አመታት ብዙ ቦታ ላይ  እያረፉ እያረፉ ዘር የማጽዳቱን ስራ ሲጀምሩ ፤ የተጀመረው እስኪጠናቀቅ አድፍጠው የሚጠብቁትና ሁሉ ነገር ከሆነ በኋላ የውድመቱን አካባቢ እንዲጎበኝ መከላከያን ወይም ፈዴራል ፖሊስን የሚልኩ ባለስልጣናት ” መከላከያና ፖሊስ ሀይላችን በቅንጅት ባይከላከል  ኖሮ ሊደርስ የሚችለው ጉዳት የከፋ ይሆን ነበር ” እያሉ የሚያላግጡብንን ሹሞች ፤ ” የመንግስት ተልኮ ምንድነው? ”  ብለን ብንጠይቃቸው ሥህተት ይሆናል ?
በመጀመሪያ ደረጃ መንግስት በወታደራዊው መስክም ሆነ በሲቪል አስተዳደር መስክ የሀገሪቱንና የህዝቡን ደህንነት ለማረጋገጥ የሚሰራ የስለላ ተቋም አለው ፡፡ በሀገሪቱ ያለው ወታደራዊና ስቢል ደህነነት ፤ በቀን 24 ሰአት 365 ቀን ሙሉ ስራ ላይ ነው ያለው ፡፡ እንኳን እዚህ የሚልከሰከሱ የወያኔና የኦነግን ገልቱዎች ቀርቶ የግብጽንና የሱዳንን ሴረኞች መከታተል እንዳለበት ይሰማኛል ፡፡
የቡራዩ ጭፍጨፋ ጊዜ ያካባቢው ፖሊስ አዛዥ  “ፖሊስ ለምን ደርሶ የሚጨፈጨፉትን ነዋሪዎች  አልተከላከለም ?” ሲባል ሀላፊው የሰጠው መልስ ” አካባቢው ለመኪና አመቺ ስላልሆነ ነው ”  የሚል ነበር ፡፡
ከሰሞኑ ጥቃት የሻሸመኔውን ብቻ እንውሰድ ሀያ ትልልቅ ፎቆችና 201 የግል ቤቶች ሲቃጠሉ ፤ 15 ፎቆችና 197 የግል ቤቶች ሲበባበሩ ፤ 78 መኪኖች ፤ 36 ባጃጆች ፤17 ሞተሮች ሲቃጠሉ ፤ ሁለት የግል ትምህርት ቤቶችና 28 ሱቆች ሲቃጠሉ ፤ 242 ቤተሰቦች ሲፈናቀሉ  ሰዎች ተገለው ሬሳቸው ሲጎተት ፤ ቤተሰብ አንድላይ አልቆ በሳት ሲነድ ፤ የአንድና የሁለት ሰ አት ስራ አይደለም ፡፡
ይህ ሁሉ ንብረትና ህይወት ቀርቶ  ገና የመጀረሪያዋ ቤት ተቃጥላ ስትጨስ ሀገሩን የሚገዛው መንግስት ይቅርና አውሮፓና አሜሪካ ያለ መንግስት እድሜ ለቴክኖሎጂ በአምስት ደቂቃ ውስጥ ይሰማል ፡፡ የተጀመረው እስኪጠናቀቅ የሚጠበቀው ለምንድነው ???
” መከላከያ ደርሶ ባያከሽፈው ኖሮ ጉዳቱ ከዚህ የከፋ ይሆን ነበር ” ለሚለው ኮሚሽነር ፤ ሻሽመኔ’ ኮ ወድማለች ፡፡ የለችም ፡፡ ከዚህ በላይ አጥፊዎቹ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ ? በልጅ ጉልበታችው ነውኮ ይህን ሲሰሩ የዋሉት ፡፡  ይደክማል እኮ !
Filed in: Amharic