
አብይ ጉንዳናቸው…!!!

በእውቀቱ ስዩም
“…ጠቅላያችን አንድ ሚሊዮን ጉንዳን ተሸክሜ ነው ያለሁት…” ሲሉ ሰማሁልበል? ለመሆኑ አንድ ሚሊዮን ጉንዳን ስንት ኪሎ ይመዝናል?…
ብቻ አያድርስ ብዬ ልለፈውና …
—
ከሁለት አመት በፊት” በሰላም አውለኝ “ የሚል ጥቅስ ግንባሩ ላይ የለጠፈ የህዝብ አውቶብስ አቃጥሎ ፤ በፖሊስ ተይዞ” ለምን እንዲህ አደረግህ ሲባል” ሰላም ባስ” መስሎኝ ነው” ያለው ጎረምሳ አሁን የወያኔንና እና የወነግን ባንዲራ ደርቦ ይዞ ፎቶ ሲነሳ ታየዋለህ!
“ገብቶት ነው ? አውቆት ነው? በድለነው ነው?” አለ መንግስቱ ‘ማረ ፋከ ‘ ሃይለማርያም!
ኢትዮጵያ ውስጥ የደረሰው ግድያና ውድመት በጥፍራም ብሄርተኝነት ጦስ ምክንያት የመጣ ቢሆንም መንግስትም ከተጠያቂነት አይድንም፤ በቸልታም ሆነ ባቅመቢስነት 
የህዝቡን ደህንነት የማስጠበቅ አቅም እንደሌለው ተባኖበታል፤አሁን ደሞ ‘የጨዋ ልጅ ካፈረ በግ ከበረረ አይመለስም ‘ ሆኖበት የከርቸሌ ዙሩን አክርሮታል! ለመሆኑ ቤትሄለም ታፈሰ ምን አድርጋ ነው የታሰረችው? በዚህ አካሄድ ኩኩ ሰብስቤንስ መች እንጠብቅ?

ስሙማ ቅድም ዩቲውብ ላይ “ ተቀበል ቁጥር አራት “ የሚለውን ዘፈን ሳዳምጥ ከሁለት አመት በፊት የነበረውን አንጀባችን ትዝ ብሎኝ ሳቅሁ፤
“ደመቀ አገሩ ገዱ ቢቀናቸው
የለማ ሆነና አቢይ ጉዳያቸው “
ይላል ዘፋኙ!
አቤት ! ወግ ወጉንኮ ይዘነው ነበር፤
አሁን ግጥሙን ትንሽ ማስተካከል የሚያስፈልግ ይመስለኛል፤
“ደመቀ አገሩ ገዱ ቢቀናቸው
የለማ ነገር ነው አቢይ ጉንዳናቸው ፤
ለማንኛውም፤
Abiy must go forward:-)