>

ነፍጠኛ...!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

ነፍጠኛ…!!!

አቻምየለህ ታምሩ

ነፍጠኛ ሲሉን የሰደቡን የሚመስላቸው ኦነጋውያን ከባሌ በታች ተነስተው ባባቶቻችን ባድማ እና ባያቶቻችን ርስት ላይ በየስምንት ዓመቱ ዘመቻ እያካሄዱ በያዙት ምድራችን ላይ ለምደው የቀሩ ሕገ ወጥ ወራሪዎች ናቸው። በመሰረቱ ፍጠኛ ማለት የተነጠቀ ርስቱን ለማስመለስ፣ በወራሪ የተቀማውን ባድማ ለማስከበርና አገሩን ከወራሪ ለመጠበቅ የተሰማራ አርበኛ ማለት ነው።
በመሆኑም ኦነጋውያን አማራውን የሰደቡ እየመሰላቸው ነፍጠኛ ሲሉ የሚውሉት አማራው ነፍጠኛ የሆነው የነጠቁትን ርስቱን ለማስመለስ፤ የቀሙትን ባድማውን ለማስከበርና አገሩን ለመጠበቅ መሆኑን፤ እነሱ ደግሞ ሕገ ወጥ ወራሪዎች መሆናቸውን ሳይታወቃቸው እየመሰከሩ ነው። ርስቱን ለማስመለስ፣ ባድማውን ለማስከበርና አገሩን ለመጠበቅ የዘመተ አርበኛን የሚጠሉ ቢኖሩ ከርስቱ ያፈለሱት፣ ባድማውን የወሰዱበትና አገሩን ያጠፉ ሕገ ወጥ ወራሪዎች ብቻ ነው።
ባጭሩ አማራውን የሰደቡ እየመሰላቸው «ነፍጠኛ» ሲሉ የሚውሉት ኦነጋውያን የሰፈሩበት ምድር በወረራ የያዙት ያያቶቻችን ርስትና ያባቶቻችን ባድማ መሆኑን በሰልፍ እውቅና እየሰጡ በመሆኑ ሊመሰገኑ ይገባል! ቀጣዩ ትግል አማራውን ነፍጠኛ ሲሉ ወራሪ መሆናቸውን ምስክርነት የሰጡበትን ያያቶቻችንን ርስትና ያባቶቻችን ባድማ አፈላማ ከፍለው down down የሚሉትን አገራችን ለቀው አገራችን ወደሚሉት እንዲሄዱ ማድረግ ነው።
ከታች የታተመው ፎቶ  አቻ  ያልተገኘለት  ድንቅ  የረጅም  ርቀት  ሯጩ ኃይሌ  ገብረ  ሥላሴ  ከ200 በላይ የወርቅ ሜዳሊያና ከ26 በላይ የዓለም ክብረ-ወሰኖችን  የሰበረበት ጫማ ነው። ይህ ኃይሌ  በትዕዛዝ ያሰራው የሩጫ ጫማው  ነፍጠኛ ጫማ ይባላል። በጫማው ላይ  በእንግሊዝኛ ፊደል ከተጻፈው የጫማው ሞዴል ማየት እንደሚቻለው የጫማው  መለያ ምልክት  “Neftegna” ይላል። ኃይሌ ሩጫውን ሲጨርስ ፈርሞ የሰቀለውም ይህን ነፍጠኛ  ሲል ባሰራው ጫማ ላይ ስምና ፊርማውን አስቀምጦ ነው። ኃይሌም ልክ እንዳባቶቹ  ሁሉ አገሩን  በዓለም መድረክ ያስከበረና ሰንደቃችንን የክብረ ወሰን ሰባሪዎች ምልክት ያደረገ ዐሊም ነፍጠኛ ነው!
Filed in: Amharic