>

"ልጄን ፊት ለፊቴ ገደሉብኝ" - እናት (ቪ.ኦ.ኤ)

“የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ 177 ሰዎች ተገድለዋል ”

 ፌደራል ፖሊስ 

 “ልጄን ፊት ለፊቴ ገደሉብኝ”

  እናት
ቪ.ኦ.ኤ

የታሳሪዎች እንጂ የሟቾች ቁጥርከትላንት አለመጨመሩን የፌደራል ፖሊስአስታወቀ። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ሕዝብግንኙነት ኃላፊት ጄይላን አብዲ እስከ ዛሬከሰዓት በኋላ የተመዘገበው የሟቾች ቁጥር ሪፖርት በኦሮሚያ ክልል 167 ሰዎች በሁከት ውስጥ መገደላቸውን አረጋግጠዋል።በአዲስ አበባ ደግሞ 10 ሰዎች ሕይወታቸውአልፏል ብለዋል።
በአጠቃላይ 229 ሰዎች የአካል ጉዳትእንደደረሰባቸውም ገልፀዋል። ዛሬ የኦሮሚያክልል ተጠባባቂ ፖሊስ ኮሚሽነር ሙስጠፋ ከድር በአጠቃላይ 239 ሰዎች መገደላቸውንለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅትየገለፁትን ከዚያ ወደ ሌሎች ዓለም አቀፍሚዲያዎች የተሰራጨው በስህተትመሆኑንም አቶ ጄይላን አብዲ ጠቁመዋል።
በኦሮሚያ ክልል 3,100 በአዲስ አበባ ደግሞ1600 ሰዎች መታሰራቸውን አረጋግጠዋል። ከቁጥር ባለፈ ያለውን መረጃ  እየተመረመረ በመሆኑ ተጣርቶ ሲያልቅ ለሕዝብ ይፋ እናደርጋለን ብለዋል። በሌላ በኩል በዚህ ጥቃት ቤተሰቦቻቸውን  ያጡ በዝዋይ ዱግዳ የሚገኙ ቤተሰቦች እና ንብረታቸውየተቃጠሉ ኢትዮጵያዊያን ያለ ምንም እርዳታ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ተጠልለን እንገኛለን ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ። ዘገባውን ያዳመጡ።
Filed in: Amharic