>

ኦሮሞን እየታገሉት ወይስ ለኦሮሞ እየታገሉ?!? [ቢቢ ሽጉጤ]

ኦሮሞን እየታገሉት ወይስ ለኦሮሞ እየታገሉ?!?

ቢቢ ሽጉጤ 

  * ግቡ የማይታወቀው የኦነግ መሪዎች እና የቄሮ ትግል…!
 
ኦሮሞ ሃገር እየመራ የኦሮሞ ጥያቄ ካልተመለሰ፡ጥያቄውን መመርመር ነው፡ጥያቄው ላይ ችግር አለ ማለት ነው…
 
  የኢትዮጵያ ፖለቲካ እንደ ሰልባጅ ከውጭ የሚቀበለው ርዕዮት፡ለሃገሪቷ ልክ አልሆን እያለ ፤ህዝቡን ከርሃብ እና ከችጋር ፈቀቅ ሳያደርው እንደ ቋያ እሳት መለብለብ ከጀመረ ግማሽ ክፍለ ዘመን ሊሞላው ነው።
  ንጉሳዊውን ስርአት ለመታገል የተማሪ ፖለቲከኞች መሠረቱን የሰራተኛው መደብ ላይ የሚያደርገውን ሶሻሊዝም፡ ሰራተኛ በሌለበት ሃገር ሊያስገቡ ሞክረው ፡ማጣፊያው ሲያጥሯቸው ፡በቀላሉ ህዝቡን ማንቀሳቀስ የሚችሉት በብሄር እንደሆነ ሲያውቁ፤ ምስራቅ አውሮፓ ውስጥ ተሞክሮ የከሸፈውን የቃረደ የብሄር ፖለቲካ ቃርመው “ኢትዮጵያ የብሄረሰቦች እስር ቤት ናት ” ብለው ተነሱ።
   ይንን ተከትሎ በንጉሱ ጊዜ ከነበረው የመጀመሪያው ‘ሜጫና ቱለማ’ የኦሮሞ ማህበር መፍረስ ቀጥሎ ፡ልክ እንደ ኤርትራ እና ትግራይ ተማሪዎች ፤የኦሮሞ ተማሪዎችም “የኦሮሞ ነፃ አውጪ ነን” ብለው ጫካ ገቡ።
   ረጅጅጅም አመት ጫካ ከርመው አንድም ቀበሌ ነፃ ሳያወጡ፤ ምስጋና ለሻዕብያ እና ወያነ በ1983 ዓ.ም አማጭ አድርገዋቸው ወደ ኢትዮጵያ ገቡ፤ ከዚያም ወያኔ በካልቾ መትቶ እንደገና ወደጫካ መለሳቸው።
   “የኦነግ መሪ ነን” የሚሉት ሰዎች ሲጠየቁ አንዳንዶቹ “ኦሮሚያን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ነው የምንታገል” ይላሉ፤ሌሎቹ “የኦሮሞ መብት እንዲከበር ነው የምንታገል” ሲሉ፤ ገሚሱ “የብሄር ጭቆና ስላለ ነው የምታገለው ” ይላል፤ “የትኛው ብሄር ነው  ኦሮሞን የጨቆነ”ተብለው ሲጠየቁ ፤መልሰው “የመደብ ጭቆና ነው” ይላሉ።
  እንደዚህ ግራ ተጋብተው ፡ህዝቡንም ግራ አጋብተው፤እንደ አሜባ እየተበጣጠሱ ተባዝተው ፡አንዳንዶቹ አውሮፓ እና አሜሪካ ፣የተወሰኑት አፍሪካ ውስጥ ሲኖሩ፤ በእነሱ ዳፋ ወያኔ አይኑ ያላማረውን ኦሮምኛ ተናጋሪ ሁሉ ጥፍር ከመንቀል አንስቶ እግር ጭምር እየቆረጠ እስር ቤቶችን በኦሮሞ ልጆች ሞላው ፣ብዙዎችንም ገደለ።
   ወያኔ መራሹ መንግስት ፡በኦህዴድ መራሹ ሲለወጥ ከሌንጮ ለታ እስከ ጃል ማሮ ወደ ሃገር ቤት ገቡ።
    የረጅጅጅም ጊዜ ታጋዩ ሌንጮ ባቲን ጨምሮ አንዳንዶቹ “የኦሮሞ ጥያቄ ተመልሷል ከአሁን በሗላ ኦሮሞ ኢትዮጵያን ሦስት ሺ አመት ይገዛል” ብለው የበላይነቱን መቆጣጠራቸውን ሲያውጁ፤ ጃል ማሮ ጫካ ገብቶ የንፁሃንን ደም ማፍሰሱን ቀጠለ፤ዳውድ ኢብሳ አንድ እግሩን ምርጫ ላይ ሌላ እግሩን፡ጫካ አድርጎ አድፍጧል፤ ጃዋር በአንድ እጁ ኦፌኮን በሌላ እጁ እራሱን “ቄሮ”ብሎ የሚጠራ አራጅ ቡድን ይዞ ኮሽ ባለ ቁጥር ተከላካይ የሌላቸው ምስኪኖችን ያሳርዳል።
   ከኦፌኮ አንስቶ እስከ ኦዴግ “ኦሮምኛ የፌደራሉ የስራ ቋንቋ ያልሆነው ኦሮሞ ስለተረገጠ ነው” ብለው ሲነጫነጩ ፤ ‘እሺ ኦሮምኛን ጨምሮ ተጨማሪ የስራ ቋንቋ በፌደራል ስራ ላይ ለማዋል ህገመንግስቱ ይቀየር” ሲባሉ  “ህገመንግስቱማ አንድ ቃል መነካት የለበትም” ብለው እርርርሪ ይላሉ።
  ባለፉት ሰላሳ አመታት የሃሰት ታሪክ እና ጥላቻ በካሪኩለም ተቀርፆ ተምሮ ያደገው ተከታያቸው የሆነው የኦሮሞ ወጣትም(ቄሮ) ፡ልክ እንደመሪዎቹ ተደበላልቆበት ፡የበታችነት ስሜት ውስጥ ተዘፍቆ ፤ በሃገር ውስጥ ያለው ሲሻው ከሃውልት ጋር እየተጣላ፣ በል ሲለው ከአያቶቹ ጋር አብሮ ኑሮ አብሮ ያረጀውን አማራ፣ጉራጌ፣ጋሞ ወዘተ በሜንጫ እያረደ፣ለኦሮሞ ልጆች የስራ እድል የፈጠሩ ተቋማትን ያወድማል፤በወያኔ ተሳዶ ከሃገር የወጣው በሰለጠነው አለም እየኖረ የኦሮሞ ልጆችን ሲያሰቃይ ከኖረው ወያኔ ጋር እጅለእጅ ተያይዞ አደባባይ ወጥቶ  “ዳወን ዳወን ምኒሊክ፣ዳወን ዳወን ቴዲ አፍሮ ፣ዳወን ዳወን አስቴር አወቀ… ” እያለ መፈክር አውርዶ ሳንፈልግ ያስቀናል።
_በርግጥ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ምንድነው?
_የኦሮሞ ብሄር ከተቀረው 80 የኢትዮጵያ ብሄር የተለዬ ጥያቄ አለው?
_ቄሮ እንደ ኢንተር ሃሞይ ብሄር እየመረጠ በሜንጫ የሚያርደው የኦሮሞን ጥያቄ ሊመልስ ነው?
_የኦሮሞን ጥያቄ ያነገበው ሌንጮ ነው ወይስ ጃል መሮ፣ ዳውድ ነው ወይስ መረራ፣ ሽመልስ አብዲሳ ነው ወይስ ህዝቄል ጋቢሳ፣ ደላሳ ዲልቦ ነው ወይስ ከማል ገልቹ?.
_አሁን ሃገር የሚመራው የኦህዲዱ አብይ ኦሮሞ አይደለም?
 ኦሮሞ ሃገር እየመራ የኦሮሞ ጥያቄ ካልተመለሰ፡ጥያቄውን መመርመር ነው፡ጥያቄው ላይ ችግር አለ ማለት ነው።
  እራስህ ለጠየከው ጥያቄ መልሱ ከጠፋህ፡መጀመሪያውኑ ጥያቄው ችግር አለበት ማለት ነው።
  በፖለቲካ ጥርት ያለ ግብ አስቀምጦ ፡የትግል ስልትን መቀያየር ሊያስፈልግ ይችላል፤የጠራ ግብ እና አላማ በሌለበት የፖለቲካ ትግል ማድረግ ፡መድረሻን ሳያውቁ ጉዞ እንደማድረግ ነው ።  መድረሻውን የማያውቅ መሄጃውንም አያውቅም።
  ይሄ  በየበታችነት ስሜት ወስጥ ሆኖ በራሱ ኢጎ እየተደናበረ እራሱን የታላቁ ኦሮሞ ህዝብ” መሪ እና ወኪል ነኝ” ባይ ሁሉ አይሆንም እንጂ ፡ቢሆን እና ‘ኦሮሞን ከኢትዮጵያ ገንጥላችሁ ምሩ’ ቢባሉ፤ አንድ ቀን ሳያድሩ ልክ እንደ ሱማሊያ ህዝቡን አጫርሰው፡አካባቢውንም “እብድ የበላው በሶ” ነው የሚያስመስሉት።
   ኦቦ ሌሳ!
  “ለኦሮሞ ህዝብ እኩልነት እና እድገት እታገላለሁ” ካልክ፤ ግልፅ አላማ ይዘህ ፡ሜንጫህን አስቀምጥ እና ከሃውልት ጋር መጣላቱን ትተህ ዘመኑ በሚፈቅደው መንገድ ታገል፤ያኔ ሌላውም ብሄር ያግዝሃል።
   በየዋሁ የኦሮሞ ህዝብ ስም ከሃውልት ጋር እየተጋጨህ፣በሜንጫ የንፁሃንን አንገት እየቀላህ ፣የኦሮሞ ህፃናት የሚማሩበትን ት/ቤትን እያቃጠልክ ፣አይ ሲ ስ፡ አይ ሲ ስ ተጫውተህ ስታበቃ ” ለኦሮሞ እየታገልኩ ነው”ብትል፤የኦሮሞን ህዝብ አሳፍረህ ፣ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ አንተም መቀመቅ ትወርዳለህ።
  ከኦሮሞ ጋር አብሮ ለዘመናት የኖረውን ህዝብ በገጀራ ቆርጠህ ፤ንብረቱን አውድመህ፤ የኦሮሞን ህዝብ አንገት አስደፍተህ “ለኦሮሞ ታገልኩ” እንዳትል፡”ኦሮሞ እንዳያድግ ታገልኩት “በል።”ኦሮሞ በሌሎች እንዲጠላ አደረኩ” በል።
Filed in: Amharic