መረጃ:- በቀለ (አቡዬ) ጥላሁን ያሚ አይደለም!!!
ሀብታሙ አያሌው
* የእነ ነውር ጌጡ ተልካሻ ሴራ ሲጋለጥ..!
—————————— ——————————
ገዳዮች ሐጢያታቸውን ለመደበቅ የሚያደርጉት ጥረት ሁሉ የበለጠ እያጋለጣቸው ነው። በምስሉ ላይ የሚታየው ወጣት የሐጫሉ ገዳይ የኦነጉ ጥላዬ ዋሚ ነው በማለት በማህበራዊ ሚዲያው ላይ እላይ እታች እያሉ ነው።
በምስሉ ላይ የሚታየው ወጣት ታዋቂው የቡና ደጋፊ ወጣት አምባቸው በቀለ በሰፈር ስሙ (አቡዬ) ይባላል። የእግርኳስ አስጨፋሪዎቹ የነ አደነ፣ የነ አቼኖ ጓደኛ አምባቸው የእምዬ ሸገር የፈረንሳይ ሌጋስዮን ልጅ ነው።
ነውረኞቹ የፍትህ ስርዓቱ ቁማርተኞች የሀጫሉ ገዳይ የተባሉትን “ሦስት የኦነግ ተልዕኮ ተቀባዮች” ለይተው አጣርተው ማቅረብ ሲገባቸው በመጀመርያ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ሁለት ወንድ አንድ ሴት ጠርጥረን ይዘናል በማለት በሚዲያ ሲያሳዩ ይሄንኑ የፈረንሳይ ልጅ አብረው አሳዩ።
ለሰሩት ነውር ይቅርታ ሳይጠይቁ ሴቷንም ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት የሌለውን አምባቸውንም እዛው አስቀምጠው ትክክለኛ ገዳዮቹን አገኘን በማለት ይፋ አደረጉ።
እነ ወጣት አምባቸው (አቡዬ) ለጊዜው በኦነግ ዳፋ ገዳይ የሚል ታርጋ ተለጥፎባቸው ጭዳ ከመሆን ተረፉ።
ገዳዮች ግን ሐጢያታቸውን ማዳፈን የሚችሉ መስሏቸው የቡና ክለብ ደጋፊ አምባቸው በቀለ ከታዋቂዎቹ ፖለቲከኞች ከነ አንዳርጋቸው ፅጌ፣ እስክንድር ነጋ …ጋር የተነሳውን ፎቶ በመለጠፍ በአቃቤ ህግ በኩል ዋነኛ ተኩሶ ገዳይ ተብሎ የተነገረው (ጥላሁን ዋሚ) ይህ ነው በማለት መረጃ ለማምታታት እየሞከሩ ነው።
የፈረንሳይ ለጋሲዮኑ ልጅ አምባቸው በቀለ (አቡዬ) የኦነግ ሸኔው ጥላሁን የሚ አይደለም። ገዳይ ተብለው ከተጠቀሱት ከሦስቱ የስም ዝርዝርም ውስጥም የለም።