>

ለምን ኢትዮጵያን ሀጫሉ አትሉዋትም...!?!  (አቤል ዘመን)

ለምን ኢትዮጵያን ሀጫሉ አትሉዋትም…!?! 

አቤል ዘመን

ይገርማል ሰው ምን ይለናል የአገሪቱ ህዝብ ምን ይታዘባል ? ምን እያደረግን ነው የሚል ጠፋ።
በሀጫሉ ሞት ያላዘነ የለም ሁሉም የአገሪቱ ህዝብ ነው ያዘነው ሞት አይገባውም ገና ወጣት ብዙ ህይወትን ማየት የነበረበት ነው ።
ሁሉም ኢትዮጵያዊ አዝኖ በጣም ትልቅ የሀዘን ድባብ ነበር ።
ለሀጫሉ ለምን ይህ ተደረገ ለማለት አይደለም ምንም ቢደረግ ቅር አይለኝም ።  ግን አንዳንዴ ህዝብ ይታዘበናል ይባላል እኮ የልጁን ክብር ዝቅ ማድረግም ጭምር ይመስለኛል።
ኢትዮጵያ ለሁሉም ዜጎቹዋ እኩል ከሆነች እኩል የሆነ አመራር እና መንግስት ካለ ፍትህም ርትዕም የሚመጣው እውነት ላይ ሲሆን ብቻ ነው ።
 
በአዲስ አበባ በድምጻዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ስም   ምን ያልተሰየመ አለ…  ገና ይቀጥላል
==>> በአቃቂ ክፍለ ከተማ ገላን አካባቢ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
==>>ከኃይሌ ጋርመንት ወደ ጀሞ የሚወስደው መንገድ
==>> ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ የሚገኘው ድልድይ
==>>ሂልተን ሆቴል አካባቢ ያለው ፓርክ ናቸው።
በስሙም የመታሰቢያ ሐውልት በከተማዋ ለማቆም በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አካባቢ የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል።
Wow ይደንቃል ይህ በአገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ነው ይህን ያክል የተሰየመ ሰው አላየንም አገሪቱን የመሩዋት እንኩዋን ይህን ያህል አልተሰየሙም።ምንም እኮ የቀረ የለም አዲስ አበባን ወይም ኢትዮጵያን በሙሉ ሀጫሉ ብትሉዋት ይቀላል።የአገሪቱ ብቸኛው ሰው እሱ አረጋችሁት ልጁን ያለቦታው እራሱ ቢሰማ እንኩዋን ቢቻል ኖሮ ላይቀበላችሁ ይችላል።
የአገሪቱ ህዝብስ ምን ይላል አትሉም እንዴ?
እንዳለ አገሪቱን ሀጫሉ ለምን አትሉዋትም ብለው እኮ ብዙወች ሲናገሩ ሰማሁ። ሀጫሉ ፍትህ የሚያገኘው የገደሉት ሲዳኙ ብቻ ነው ከዛ ውጭ የፈለገ ብትሉት ምንም ታምር አይፈጥርም።ከዛ ውጭ ሀጫሉን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የታገለ የሚለው ከየት እንዳመጣችሁት ህዝቡም ገርሞታል ሀጫሉ National Hero ሊባል አይችልም ” የታገልኩት ለኦሮሞ ህዝብ ነው ” ሲል በራሱ አንደበት ተናግሮዋል። ለአንድ ብሄር መታገል እና ለአገሪቱ ብሄሮች በሙሉ መታገል ይለያል። ህዝብ ያየውን በማይሆን አልብሶ ለአገሪቱ ህዝብ የታገለ የአገር ጀግና ማድረግ ያው በቃላት በባለ ጊዜነት ይቻላል እውነታውን ግን ህዝቡ ስለሚያውቀው ያን ያክል ለውጥ አያመጣም።
አወ ጀግና ልጅ ነው ላመነበት ብዙ መስዋትነት ከፍሎዋል ለኦሮሞ ህዝባችን የቻለውን ሁሉ አድርጎዋል ያም ቢሆን ግን ሀጫሉ አይደለም የኢትዮጵያ ህዝብ በኦሮሞ ህዝብ የትግል ታሪክ ከሱ በላይ ከፍ ብለው የሚቀመጡ አሉ።የአገራቸው ጀግና የሆኑ ታሪክ የሰሩ ስማቸው በሁሉም የአገሪቱ ህዝብ የተወደደ በታሪክ የሰፈሩ ጀግና የኦሮሞም የኢትዮጵያም ጀግኖች ነበሩ   እነኛ ጀግኖች በአገራቸውም በህዝባቸውም የሚታወቁ የሚከበሩ ናቸው ።
የሀጫሉ ግድያው አሳዛኝ የፖለቲካ ቁማር በመሆኑ ልብ ይሰብራል ከዛ ውጭ ግን ለኦሮሞ ህዝብም ለአገራቸውም ከፍተኛውን ክብር ከሰጡት በላይ አርጎ ለመሳል መሞከር ለጊዜው እንጅ እውነታውን ህዝቡ ስለሚያውቀው የሚፈጥረው ነገር አይኖርም ባለጊዜነት ወይም የተፈጠሩትን ችግሮች ህዝብ ለማረሳሻነት እንደሆነ ግልፅ ነው ።
የአገሪቱ ህዝብ እና እራሱ የኦሮሞ ህዝብ የሰጠውን አስተያየት ተመልከቱና ፍርዱን ታገኙታላችሁ።
የአገሪቱ የጦር መሪ የኢትዮጵያን ጦር የመራ የተከበረ ጀነራል ባሳዛኝ ሁኔታ ተገድሎ ለሱ መታሰቢያ እንኩዋን በቅጡ አገሪቱ አዲስ አበባ ላይ አላኖረችም አንዲት ነጠላ መንገድ ብቻ በስሙ ተሰየመች ትግራይ ላይ ህወሀት የመንግስትን ነውር አስንቆ ሀውልት አቆመለት በቃ።
አስቡት የአገሪቱ የጦር መሪ ጀነራልን ያህል እንዲከበር ያላደረጉ አመራሮች  ከዛም ደግሞ አስቡት ለአገሪቱ ህዝብ ከጫፍ ጫፍ ጀግና የሆነ የበረሀው ሰው ከርታታው ኢንጅነር ስመኘው ያ መስኪን ” እኔ ደክሜ እኔ ጠቁሬ ሁሉም የአገሬ ህዝቦች ቢለወጡልኝ ለኔ ሽልማቴ ያ ነው” ብሎ በአባይ በረሀ መከራውን ሲያይ የኖረ በግፍ መስቀል አደባባይ ከዛች መኪና አንገቱ ቁልምም ብሎ ደሞ የፈሰሰውን የአገር ሙሉ ባለውለታ ጀግና ከተገደለበት ደሙ ከፈሰሰበት ስፍራ ላይ ሀውልት እንኩዋን አልቆመለትም።
ብቻ ታምር ነው የአገሪቱን ጀነራል እንደዛ ተገለው የአገር ታላቅ ባለውለታ እራሱን ለህዝብ የሰጠ የበረሀው ሰው ያ እንቁ ልጁዋ ተገድለው እንዲህ ሲሆን አላየንም።
ጥሩ ለውጥ ነው ለሀጫሉ የፈጠነው የህግ እና ፍትህ መንገድ እንዲህ ባጭሩ ህግ ካስገኘ የስመኘው ደም ፍትህ ለምን ተነፍጎት ታፍኖ ቀረ ? የአገሪቱ የጦር መሪ ያ ታላቅ የአገር ጀግና ሞትስ እንዲሁ እንዴት እስካሁን ዘገየ?
ሌሎች የተገደሉትስ ?
በሀጫሉ ሞት ምክንያት የሚጠብቅ ለህልውናቸው እንኩዋን ዋስ የሚሰጥ መንግስት ባለመኖሩ በግፍ የተገደሉ ከ239 በላይ ንፁሀን ህይወትስ? እነሱ ኢትዮጵያውያን አይደሉም ? ምንም ባላደረጉ ባልበደሉ በመንግስት እጦት በህግ አለመኖር ባሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉት የዚህ ሁሉ ከ 239 በላይ ህዝብ ሞት እንደ ሰው አይቆጠሩም?
ነው ወይስ ኢትዮጵያውያን አይደሉም ፍትህንስ አይሹም?
ፍትህ እማይመጣው ከሀቅ ማዶ የቆመ ስርአት እና አመራር ስላለ ነው ። ዜጎቹን መጠበቅ አቅቶት ከ 239 በላይ ንፁሀንን ያስጨረሰው መንግስት የአገሪቱን ባንዲራ እንኩዋን  ዝቅ አላደረገም ታምር ነው ።
ለአገር ብሎ ለህዝብ ብሎ እራሱን በዛ ሀሩር በረሀ አሰቃይቶ ከዛ ሁሉ በላይ በግፍ ተገድሎ የሱን ልጆች እና ወላጅ አባቱን እንኩዋን ዞር ብለው ያላዩ ባለሀብት እና መንግስት ዛሬ ላይ ግን ሁሉን ለማድረግ ህዝብ እንኩዋን አልጠየቁም የህዝብን ሀብት በትዛዝ ብቻ ይቅር ።
ዜጎቹዋን እኩል የምታይ አገር ለፍትህ እና እኩልነት የቆመ ስርአት ሲኖር ሁሌም የለውጥ መስመር ትክክል ይሆናል።ለማንኛውም የሞቱትን የሁሉንም ነብስ ይማር።
በፖለቲካ ሴራ ለተገደለው ወንድሜ አጫሉም ነብስ ይማርልን። አስተውሉ ለሀጫሉ ለምን ይህ ሁሉ ሆነ ብየ እየተቃወምኩ አይደለም ግን በዜጎቹዋ ላይ እኩል የማታይ አገር መንግስት ዘላቂ አይሆኑም። ፍትህ ያለባት አገር መንግስት ያንዱን ፍትህ ለማስገኘት ሙሉ ዘመቻ የሚገባ ሀውልት ለማቆም የሚሮጥ ገንዘብ ከህዝብ ካዝና ለዛ ተግባር የሚያወጣ በሌላ በኩል እኩል ለተጎዱ ዜጎቹ አይደለም ፍትህ ሊያገኙ ብዙ ግፍ ተሰርቶባቸዋል የ239 ዜጎቹን መገደል እንኩዋን እንደ ሰው ነብስ ቆጥሮ ያላዘነ የአገሪቱን ባንዲራ እንኩዋን ዝቅ አርጎ ያላውለበለበ አመራር ኢፍትሀዊ ብቻ ሳይሆን የዘቀጠ እና አሳፋሪም ነው .
Filed in: Amharic