>

በኢትዮጵያ ምድር የተንሰራፋው አፓርታይዳዊ አገዛዝና ግብረ በላዎቹ ...!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

በኢትዮጵያ ምድር የተንሰራፋው አፓርታይዳዊ አገዛዝና ግብረ በላዎቹ …!!!

አቻምየለህ ታምሩ

የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝና ግብረ በላዎቹ በሻሽመኔ፣ በአርሲ፣ በባሌ፣ በሐረርጌና በዝዋይ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ተድበስብሶ እንዲታለፍና ዓለም እንዳያውቀው ታትረው በመስራት ላይ ይገኛሉ። የዘር ፍጅት ፈጻሚዎች ሩዋንዳ እንደተደረገው መታወቂያ እየጠየቁና አስቀድመው ባዘጋጁት የስም ዝርዝር መሰረት የዘር ማጥፋቱን ያካሄዱ መሆኑ እየታወቀ የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝና ግብረ በላዎቹ  ግን  የዘር ፍጅቱን  ግጭት  አድርገው እያስወሩት ይገኛሉ።

የዘር ፍጅቱን ግጭት ብሎ የተፈጸመውን አለማቀፋዊ ወንጀል እንዳልተፈጠረ  ከሚሰራ አገዛዝ  ለግፉዓንና ለሰለባዎቹ ፍትሕ ይሰጣል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው። የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝና ግብረ በላዎቹ  ይህን የሚያደርጉበት ዋናው ምክንያት  ከላይ እስከ ታች ድረስ ያሉት አመራሮች  በሙሉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በዘር ማጥፋቱ   ተካፋይ ስለሆኑ  ራሳቸውን ከፍርድ ለማሸሽ  ነው።  በዚህ ሴራ ምክንያት  ዘግናኙ ፍጅትና የዘር ማጥፋት ተድበሶብሶ ከታለፈ ሕዝባችን  እየተካሄደ ካለው የዘፍ ፍጅት  የከፋ እልቂት ወደፊት እንደሚጠብቀው ለመናገር ጠንቋይ መቀለብ አይጠይቅም። በመሆኑም በተለይ በውጭ አገር ያለው የሚጣላ ኅሊና ያለው ወገን ሁሉ የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ ወንጀሎችን ግብረ በላዎቹ  ተድበስብሶ እንዲታለፍ እያደረጉት ያለውን ፍጅትና የዘር ማጥፋት አለም እንዲያውቀው፤ ከላይ እስከ ታች ያሉ ተጠያቂዎች በሙሉ እንዲያዙና ለወንጀላቸው ተመጣጣኝ  የሆነ ፍርድ እንዲሰጣቸው  በመታገል  ወገናዊ  ኃላፊነቱን መወጣት ይኖርበታል።

Filed in: Amharic