>

እውነት ከፊትህ ቆሞ እንደ ጲላጦስ ‹‹እውነት ምንድነው›› እያልክ አትጠይቅ !! (ሀብታሙ አያሌው)

እውነት ከፊትህ ቆሞ እንደ ጲላጦስ ‹‹እውነት ምንድነው›› እያልክ አትጠይቅ !!

ሀብታሙ አያሌው
* የፌደራል ዐቃቤ ህግ ኃላፊዋ :-
 ‹‹ ባልደራስ ፤ ህወሓት እና ኦነግ›› ተናብበው ሰርተዋል ወደሚል የነውረኛነት ጥጓ ሂዳለች..!
* ሌላው ነውረኛ:- ‹‹ የኦነግ ሸኔው ጃልማሮ፤ የባልደራሱ እስክንድር፤  የህውሓቱ ጌታቸው አሰፋ ወይም ደብረጽዮን ለጋራ ዓላማ ሰርተዋል›› ሲል ሰቅጣጭ ነውር ተናግሯል
ከገቢዎች እና ጉምሩክ የአማራ እና የትግራይ ብሔረሰብ ተወላጆችን መንጥረው ተቋሙን በኦሮሞ ተወላጆች መሙላታቸውን ያጋለጠውን በተቋሙ በከፍተኛ ኃላፊነት ይሰራ የነበረውን ወጣት ምሁር ከስራ ማባረር ብቻ ሳይሆን አስረው አሰቃይተው ፈቱት፡፡
ያ ተረኝነት ብቻ ሳይሆን ነውረኝነት አልበቃቸው ብሎ የሀጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ በሚዲያ ብቅ ብለው ‹‹እስክንድር ነጋ የአዲስ አበባን ወጣት አደራጅቶ ሃዘኑን ለመግለፅ የወጣው ቄሮ በዱላ በገጀራ ለመጨፍጨፍ ስምሪት ሰጠ አላች›› አዳነች አቤቤ ይህ ነውር አልበቃትም፡፡ አምባቸው በቀለ የተባለ የአዲስ አበባ የፈረንስይ ለጋሲዮን ልጅ የሀጫሉ ገዳይ አሥመስላ የኢትዬጵያ ሰንደቅ ዓላማ ያለበት ጃኬት እንዲለብስ በማድረግ በቴሌቪዥን እንዲታይ አደረገች፡፡ ለጊዜው አላማዋ ተሳካ ‹‹የምኒልክ ባንዲራ የለበሰ ሀጫሉን ገደለ›› በሚል ጥላቻው ተራገበ ለዘር ማጥፋቱ ወንጀል ነዳጅ አቀብላ ዘወር አለች፡፡ ከእልቂቱ በኋላ ተመልሳ ደግሞ ዋነኛ ተኳሽ ሆኖ ሀጫሉን የገደለው ከኦነግ ሸኔ ተልዕኮ የተቀበለው ጥላሁን ያሚ የተባለ የሸኔ አባል ሲሆን አረዳቶቹም አብዲ አለማየሁ እና ከበደ ገመቹ ናቸው አላች፡፡
የፈረንሳዩ አምባቸው በቀለም ሆነ ሌላኛዋ አንድ ሴት ቢዲያ ለፖለቲካ ሰለባ አድርጋ አላማዋን ካስፈጸመች በኋላ ተወቻቸው፡፡ አሁን ደግሞ ፊቷን በጀመረችው መንገድ ወደ እስክንድር ነጋ መልሳ ‹‹ ባልደራስ ፤ ህወሓት እና ኦነግ›› ተናብበው ሰርተዋል ወደሚል የነውረኛነት ጥጓ ሂዳለች፡፡ የጠቅላይ ሚንስትሩ ጸ/ቤት ኃላፊ ንጉሱ ጥላሁንም ዛሬ በሰጠው መግለጫ ነውረኝነቱ መንግስታዊ መሆኑን ሲያረጋግጥ ‹‹ የኦነግ ሸኔው ጃልማሮ፤ የባልደራሱ እስክንድር፤ የህውሓቱ ጌታቸው አሰፋ ወይም ደብረጽዮን ለጋራ ዓላማ ሰርተዋል›› ሲል ሰቅጣጭ ነውር ተናግሯል፡፡
በመንግስት ፍረጃ እንደ ድርጅት ከዳውድ ኢብሳ – ኦነግ ከጃዋር እና በቀለ – ኦፌኮ ይልቅ ለህወሓትና ለሸኔ የእስክንድር ነጋ ባልደራስ ይቀርባል በጋራ ሰርቷል ሲሉህ ይሄን ተቀብለህ መንግስተ ሰማያት ከምትገባ ሲዖልን መርጠህ ከጽድቅህ ጋር ብትቃጠል ይበጅሃል፡፡ ጽድቅ እውነት ነው፡፡ እንደ ጲላጦስ እውነት ከፊትህ ቆሞ እውነት ምንድነው ብለህ አትጠይቅ፡፡ እውነት ከፊትህ ቆሞ እንደ ጲላጦስ ‹‹እውነት ምንድነው›› እያልክ አትጠይቅ፡፡
Filed in: Amharic