>

ፖሊስ የፍ/ቤቱን ትእዛዝ "አልቀበልም" ማለቱ  የኢንጂነር ይልቃልን የጤንነት ሁኔታ አሳሳቢ አድርጎታል!!! (ጋዜጠኛ መአዛ መሀመድ)

ፖሊስ የፍ/ቤቱን ትእዛዝ “አልቀበልም” ማለቱ  የኢንጂነር ይልቃልን የጤንነት ሁኔታ አሳሳቢ አድርጎታል!!!

ጋዜጠኛ መአዛ መሀመድ

*  “አንድ የዪኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ቤተመንግሥቱን አፍርሼ የኔን ዘመድ ሀውልት ነው የምሰራበት ብሎ የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርግ ፋሽዝም ዕድሜም ትምህርትም የማይለውጠው ነገር መሆኑን practical example ጥራ ብባል የምጠራው ፕሮፌሰር መራራ ጉዲናን ነው።” በሚለው ንግግራቸው በባለጊዜዎች ጥርስ ውስጥ እንደገቡ የሚታመነው ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የጤንነት ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል
*   *   *
ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ፍርድ ቤት በቀረቡበት ወቅት እሳቸውና አብረዋቸው የታሰሩ ሰዎች ከኮሮና ነጻ መሆናቸው ታውቆ አንድላይ እንዲቆዩ የተደረገ ቢሆንም ሌሎች ሁለት በስርቆት ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ ወጣቶች የምርመራ ውጤታቸው ሳይታወቅ ወደነሱ እንዲቀላቀሉ የተደረጉ ሲሆን በኋላ ላይ ውጤታቸው ፖሰቲቭ መሆኑ ስጋት እንዳሳደረባቸው ገልፀው ነበር።
ፍ/ቤቱም ጉዳዩ አሳሳቢ መሆኑን ተረድቶ ለብቻቸው እንዲደረጉ ለጉዳዩ መፍትሄ እንዲሰው በፅሁፍ ቢታዘዘም ፖሊስ ግን ለመፈፀም ፈቃደኛ አልሆነም።
  ኢንጂነር ይልቃልም ቤተሰብ ሊያናግረኝ ሲመጣ ሲመናጨቁና ሲዋከቡ ላለማየት እና ቫይረሱ ይኑር አይኑርባቸው ሳያውቁ ከክፍላቸው ላለመውጣት በመወሰናቸው ከትላንትና ጀምሮ ከቤተሰቦቻቸው መገናኘት እና ምግብ መቀበል ማቆማቸውን ወንድማቸው ነግረውኛል።
Filed in: Amharic