>

በአገሪቷ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች በፍጥነት ካልታከሙ ኢትዮጵያዊነት የማይድንበት ደረጃ ላይ ሊደርስ ይችላል!!! (ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት) 

በአገሪቷ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች በፍጥነት ካልታከሙ ኢትዮጵያዊነት የማይድንበት ደረጃ ላይ ሊደርስ ይችላል!!!

ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት 

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት፣ ሠላምና አንድነትን የዳሰሱ ወቅታዊ ጭብጦች ላይ ያተኮረ ሲሆን ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘመናት የተገነባ በቀላሉ የማይጠፋ መሰረት ነው።
ሌሎች በገንዘብ ኢትዮጵያን አፍርሱ ብለው ጥፋት እንደሰሩ ሁሉ እኛም በእውቀታችን ከሰራን ትውልዱን መመለስና ኢትዮጵያን ማዳን እንችላለን ።
የጥንት ኢትዮጵያዊያን የሰሯቸው የአንድነት ታሪኮች ሲዳሰሱ በተለይ በአድዋ ጦርነት ታሪክ የሰሩት በጀግንነት ተግባብተውና በሃገር ፍቅር ስሜት ተሳስረው ነው።
ኢትዮጵያዊነት ማለት ቅይጥነት፣ አብሮነት፣ ለሌላው መኖርና አዛኝነት፣ አትንኩኝ ባይነትና ጀግንነት ነው።
የአሁኑ የመከፋፈልና የልዩነት ታሪክ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተሰራ የሴራ ፖለቲካ የመጣ ነው።
በአድዋ ድል ለመጀመሪያ ጊዜ የጥቁርን አሸናፊነት በተግባር ያረጋገጠችው ኢትዮጵያ በሌላ በኩል ከአባይ ወንዝ የባለቤትነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ እድገቷን የማይፈልጉ የውጭ ጠላቶች እንዲኖራትም አድርጓታል።
ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት እንዲዳከም በውጭ ጠላትና በሃገር ውስጥ ባንዳዎች ሃይማኖትና ዘርን ትኩረት በማድረግ የመስራት አዝማሚያ ጥንትም የነበረ ነው።
ይሁን እንጂ ይህ ኢትዮጵያዊነትን የማዳከምና ልዩነትን የማስፋት ስራ መንግስታዊ መዋቅር ይዞ ላለፉት ዓመታት ሲሰራ መቆየቱ አሁን ላጋጠመው ችግር ዋነኛ ምክንያት ሆኗል።
ኢትዮጵያን የሚከፋፍል የጥላቻና የዘር ፖለቲካ የሚያመርቱት የውጭ አካላት ቢሆኑም በሃገር ውስጥ ደግሞ የጉዳዩ አስፈፃሚዎች መኖራቸው ችግሩን የባሰ አድርጎታል።
Filed in: Amharic