>

እንዲያደምጡ እንመክራለን:- የኢትዮጵያ ጠላቶች እነማን ናቸው?፣ ምንስ እየሰሩ ነው...? (ህብር ሬዲዮ ከጋዜጠኛና አሳታሚ ኤሊያስ ወንድሙ ጋር እና...)

የኢትዮጵያ ጠላቶች እነማን ናቸው?፣ ምንስ እየሰሩ ነው…?

ህብር ሬዲዮ ከጋዜጠኛና አሳታሚ ኤሊያስ ወንድሙ ጋር እና…

ታምሩ ገዳ
የኢትዮጵያ ታሪኳን ለማጥፋት፣ ቀደምት መሪዎቿን የማንቋሸሸ ዘመቻ  መቼ ተጀመረ?፣ ለምን ተጀመረ? ፣የኢትዮጵያ ጣላቶች እነማን ናቸው?፣ወዳጆቿስ?፣ሰሞኑን በዲያስፖራ ውስጥ  እንደነጠላ ዜማ ሲዘፍን የሰነበተው “ዳውን፣ዳውን፣ዳውን ኢትዮጵያ፣ዳውን ፣ዳውን ምኒሊክ/ኢትዮጵያ ትውደም፣ምኒሊክ ይውደም…” እርግማን አቀንቃኞች ትምህርቱን ከየት ቀሰሙት ?፣ዛሬስ ተራ ዘለፋው ለምን አስፈለገ?።
እውን እነዚህ ወገኖችን  መጥላት አለብን?ለምን? ፣የኢትዮጵያ መጻኢ ፈተናዎች ፣ ትንሳኤዎቿ እና …ወዘተ ወቅታዊ ገዳዮች ዙሪያ  ልዩ ትምህርታዊ ወይይት ተካሄዷል። የተለያዩ ታሪካዊ መጻህፍቶችን እያሳተመ ከአንባቢዎች እና ከእውነተኛ ታሪክ እፍቃሪዎች እጅ  በማቅረብ ላይ ያሚገኘው የጸሐይ አሳታሚ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያ የሆነው ጋዜጠኛ ኤሊያስ ወንድሙ  ዛሬ በአሜሪካ አገር፣ በሎሳንጀለስ ከተማ በኢ/ኦ/ተ /ቤ/ን የድንግል ማሪያም ካቴድራል ፣በደ/ካሊፎርኒያ እና አላስካ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ  በሆኑት  ከአቡነ በርናባስ ፣የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪ  አባ ላከማሪያ አበበ እና የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊው  ሊቀ ህሩያን ቄሲስ  መላኩ ተፈራ ጋር በተደረገው  ሰፊ ውይይት ላይ  የተጋበዘው ጋዜጠኛ ኤሊያስ ለዘመናት ያሰባሰበው እጅግ ጥልቅ ፣ታሪካዊ  እና ሁሉን አቀፍ መረጀውን  ለወገኖቹ እንደሚከተለው አካፍሏል።
እርሶም በዚህ  ታሪካዊ አጋጣሚ በማውቅም ይሁን ባለማወቅ የኢትዮጵያን ታሪክን  ጥላሸት የሚቀቡት ወገኖች ወደ ልቦናቸው እንዲመለሱ በሚደረገው ዘመቻ አካል በመሆኖት የአምልኮት ልዩነት ሆነ የፖለቲካው መጠላለፉ አገር ሲኖር ብቻ በመሆኑ መረጃውን በማሰራጨት ወገናዊ ድርሻዎትን እንዲወጡ ተጋብዘዋል። ፈጣሪ  አገራችን ኢትዮጵያን እና ልጆቿን ከተደገሰላቸው ሴራ  ይታደግልን።(/ህብር ራዲዮ)
Filed in: Amharic