>

ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሞ ክልል ፕሬዚደንት ሆኖ ይቀጥል ይሆን!? (ሰይፍ ፍርድ አምደጽዮን)

ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሞ ክልል ፕሬዚደንት ሆኖ ይቀጥል ይሆን!?

ሰይፍ ፍርድ አምደጽዮን


• ግንቦት 17, 1955 ዓ/ም( May 25, 1963 G.C) በኢትዮጵያ የተቋቋመው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት OAU: ከ1998 ዓ/ም/2006 G.C ጀምሮ የአፍሪካ ህብረት AU: ባለበት ሀገር ውስጥ:-
• በ1950 ዓ/ም( 1958 G.C) በኢትዮጵያ የተቋቋመው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን(UNECA) ባለበት ሀገር ውስጥ:-
• ከ120 ሀገራትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በላይ ኢምባሲያቸውን ከፍተው በሚኖሩባት ሀገር ኢትዮጵያ ውስጥ:-
ይህ ሁሉ ግፍ: የዘር ማጥፋት እና የዘር ማፅዳት ወንጀል መፍፀሙ እጅግ አሳዛኝና አሳፋሪ ነው::
በሌላ በኩል በሁላችንም መራራ ትግልና ብሎም ድጋፍ ወደስልጣን የመጡት የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ኦዴፓ መራሽ ሀይሎች ወይም ተረኞቹ ሀገር እና ህዝብ በወጉ ለመምራት የሚያስችላቸውን በትረስልጣን ጨብጠው ሲያበቁ እስካፍንጫው የታጠቀ ሀይል በስራቸው አጭቀው ያልታጠቀው ሲቪል ህዝብ በማንነቱ: በዘሩ እና በሀይማኖቱ እየተለየ ሲጨፈጨፍ: አካሉ ሲጎድል እና ንብረቱ በጠራራ ፀሀይ በአክራሪና አሸባሪ ሀይል ሲነድ የወሰዱት የቅድመ መከላከል ጥናት ክትትል እና እርምጃ: ድርጊቱም እየተፈፀመ ባለበት በፍጥነት አደጋው ሳይባባስና ከፍተኛ ጉዳት ሳያስከትል ለማስቆም የወሰዱት እርምጃ የለም ወይም እጅግ የዘገየ እና የግብር ይውጣ: ዳተኝነት: ግዴለሽነት: ቸልተኝነት እና ባወጣ ያውጣው የሚል ርካሽ ሗላ ቀር ባህሪ የተስተዋለበት ሲሆን የሀላፊነት ግዴታን ለመወጣት የወሰዱት አጠቃላይ እርምጃም እጅግ አሳዛኝና አሳፋሪ ነበር::
የደረሰው ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት ታሪክ ይቅር የማይለው ጠባሳ ጥሎ ያለፈ ሲሆን እነሱም ሱፍ ለብሰው ከራባት አስረው ከዚህ በሗላ ህዝብ ፊት ሲቀርቡና በቴሌቪዥን ሲታዩ እጅግ ሊያፍሩ በህግም እንደየሚናቸው ሊጠየቁ ይገባል!!!
እርግጥ ነው አንድ ሀጫሉን በሊቀሰይጣን ወያኔና በቃንጃው ሊቀጂኒው ኦነግ ክብረነክ ጋብቻና ሴራወለድ የጋራ ጥምር ነውር እርምጃ አማካኝነት ተገደለ:: ይህን የወንጀል ድርጊት ተከትሎ ከ31 ዙር በላይ ፓራ ሚሊተሪ በማሰልጠን ሲመፃደቅ የነበረው የኦሮሞ ክልል ፕሬዚደንት ሽመልስ አብዲሳ ይህ ሁሉ የግፍ ግፍ በአክራሪውና አሸባሪው ቄሮ ህዝብን በዘሩ እና በሀይማኖቱ ምክንያት እየለየ ቤት ለቤት በተደረገ አሰሳ ሲጨፈጨፍ: አክራሪው ቄሮ የዘር ማጥፋት ወንጀል እና የአካል ማጉደል ወንጀል ሲፈፅም: ቤተክርስቲያን ሲያቃጥል: እልቁ መሳፍርት ንብረት በእሳት ሲያነድ: ከለሊት አልፎ በጠራራ ፀሀይ ከተሞችን ከአ/አ ጀምሮ ናዝሬትን: ዝዋይን: ቡልቡላን: አርሲነጌሌን: ሻሸመኔን: ኮፈሌን: ዴራን: አሰላን: ቀርሳን: አሳሳን: አዳባን: ባሌ ሮቤን: አጋርፋን: እያለ ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ ዋቤ አውራጃ ውስጥ ጊንርን አልፎ: ሰወይናን ሀወጡን አልፎ ቤልቱ እና ራይቱ ውስጥ አማራውን እና ክርስቲያኖችን ዒላማ አድርጎ ሰው እንደ እንሰሳ እያረደ ንብረት ሲያወድም በ21ኛው ክፍለዘመን ህዝብ ሲፈናቀል በመሀል ሀገር ሊባል በሚችል ደረጃ ዛሬም በሻሸመኔ ህዝብ በቤተክርስቲያን ለመጠለል ሲገደድ የማንን ጎፈሬ ያበጥር ነበር!??
በኢትዮጵያ ህዝብ በጀት የሰለጠነው የኦሮሚያ ፓራሚሊተሪስ: በአባሪነት: በአስተባባሪነት: ካልተሳተፈበት በስተቀር: የመከላከያ ሰራዊት: የፌደራል ፖሊስ: የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት: አጠቃላይ የፀጥታ ሀይሉ ይህ ሁሉ ዘግናኝ ጉድ ሲፈፀም ምን ይሰራል? ምንስ ይጠብቃል?? ክቡር የሰው ህይወት መታደግ ካልቻለ እጁን እየሰቀለ ህግን አክብሮ ለማስከበር: የዜጎችን መብት አክብሮ ለማስከበር የገባው ቃል ኪዳን ምን ትርጉም አለው!? የመኖሩ ሚስጥር ምንድነው!?
በእውኑ ሽመልስ አብዲሳ የዘሬ ያንዘርዝረኝ ካልሆነ በስተቀር በቀጥታ የቴሌቭዥን ስርጭት ለሀጫሉ ያፈሰሰው እንባ እራሱ በፕሬዚደንትነት በሚመራው ክልል በግፍ በገጀራና በሜንጫ ለታረዱ ለተጨፈጨፉ ህዝቦች አንዲት ዘለላ እንባ ለማፍሰስ ለምን አልዳዳውም!?
አሁን ከዚህ ሁሉ የግፍ ተግባር በሗላ የክልሉ ፕሬዚደንት ሆኖ የመቀጠል ብቃትና ሞራል ይኖረው ይሆን!? ሾተላዩ ጠ/ሚ እውን የክልሉ ፕሬዚደንት ሆኖ እንዲቀጥል ይፈቅድለት ይሆን?
Filed in: Amharic