>

በጀዋራዊያን የምትመራ ኢትዮጵያን ሳስብ ....!?! (መክብብ አበረ)

በጀዋራዊያን የምትመራ ኢትዮጵያን ሳስብ ….!?!

መክብብ አበረ

ባለ ሜንጫው ፣ ባለ ጨፈቃው ፣ ባለ ገጀራው ፣ ባለ ድንጋዩ ጀውር ፤ …..
የጥላቻ ፣ የክፋት ፣ የዘረኝነት ማደሪያና ጉሮኖ የሆነው ጀዋር ፤ ….
ባለ ” ተከበብኩኝ ! ” ባዩ ፣ ባለ ሽብሩ ፣ ባለ ሁከቱ ፣ ጀዋር ….
እነዚህ ሁሉ እኩያቶች የተሸከመው ጀዋር የሚመራት ኢትዮጵያ ምን ልትመስል እንደምትችል መገመት ቀላል ነው ።
.
” አንተ 99% ነህና ፤ እንቢ ካለ በሜንጫ አንገቱን በለው ! ” እያለ የሐረር ወንድሞቻችንን …. በወንድሞቻቸው ኢትዮጵያውያን ላይ እንዲነሱ ሲቀሰቅስ የኖረው ጀዋርና ቡድኑ ምን አይነት የአገር መሪ ሊሆኑ እንደሚቾሉ ማሰብ በራሱ ያጥወለውላል ። እነሱ የሚገቡበት ቤተ-መንግስትም ቆርጣሚ ጭራቆች የሚርመሰመሱበት መድረክ ሆኖ ነው የሚታየኝ ።
.
ጀዋር ባሌና አርሲ ፣ ሲሄድ እስልምናን ከፖለቲካ ጋር አብኩቶ ይጋግራል ። የጋገረውንም መርዝ በሐይማኖት እንጀራ እየጠቀለለ ለመንጋዎቹ ያጎርሳል ። አንቦ ሲሄድ ቱለማን ይሰብካል ። ፍቼ ሲሄድ ጀነራል ታደሰ ብሩን ያሞጋግሳል ፤ ” ደብረ-ሊባኖስ ገዳምን ተቆጣጠሩ ፤ በዚያ ያለውን ደብተራ አሶጥታችሁ ርስታችሁን ተረከቡ ! ” ይላል ።
.
ኦርቶዶክስ ሐይማኖት የኦሮሞን መሬት በወረራ የያዘ የነፍጠኛው ስረአት መጠለያ እንደሆነች በተላላኪቹ ያስነግራል ። ጀዋራዊያን ” ኦርቶዶክሶች ውሃ እየረጩ ኦሮሞን አማራ ያደርጋሉ ! ” ሲሉም አስቂኝ ግን ክፉ ስብከት ያሰራጫሉ ፤ ይህ ዶ/ር ገመቹ የተባለ ሰው በLTV ቀርቦ ያስተላለፈው መልእክት ነው ። ዶክተሩ ይህንን ሲሉ ጋዜጠኛዋ ቤተልሄም ” ኦሮሞነት በሚረጭ ውሃ የሚለቅ ባእድ መንፈስ ነው እንዴ ? ” ብላ መጠየቅ ነበረባት ። እንደ ቄስ በላይን የመሰሉ ከፊት በማሰለፍም የኦሮሚያን ሲኖዶስ ለመመስረትና ኦርቶዶክስን ለመበታተን ፕሮጀክት ነድፈው ይንቀሳቀሳሉ ።……
.
ጅማ ሲሄዱ ስለ “ዲቃላ ኦሮሞዎች ” እንቅፋትነት ይደሰኩራሉ ። ዲቃላ ከኦሮሞ ምድር መጥረግ ካልተቻለ የኦሮሞ ነፃነት ቅዠት ሆኖ እንደሚቀር ያስተምራሉ ። ” ዲቃላ ” ሲሉ ኦሮሞ ከሌላው የወለደውን ዜጋ ነው ። ጀዋር ወሎን ፣ ራያን ና ሐሶሳን ሲያይ የኦሮሞ ነባር ርስት እንደሆነ በድፍረት ይናገራል ። ሚኖሶታ ሲሆን ደግሞ ” Ethiopia out of ormiya ” ይላሉ ። ” ኦሮሚያ ” የምትባል አገር …. ” ኢትዮጵያ ” በምትባል ሌላ አገር በቅኝ የተያዘች አስመሰሎ ያቀርባሉ ። አሉታን እየዘሩ ከጨቅላ ወጣቶች አእምሮ ውስጥ ኢትዮዮጵያን ነቅሎ ለማውጣት ይተጋሉ ።
.
እነጀዋር የጥፋት አጀንዳቸው በኢትዮጵያ አለያም ሊመሰርቷት በሚፈልጓት ” አገረ ኦሮሚያ ” ለማንበር ከሰይጣንም ለመተባበር ፈቃደኞች መሆናቸውን ይናገራሉ ። በዚህም መሰረት ከሕወሓት ጋር ተናበው እየሰሩ እንደነበር ከሰሞኑ ተግባራቸው አይተናል ። የወያኔ አፈ-ቀላጤ የሆነው ጌታቸው ረዳ የኮሙኒኬሽን ሚንስትር በነበረበት ወቅት የሐጫሉና የቄሮ ጓደኞቹን እንቅስቃሴና ትግል ” የጋኔን ሙቭመንት ” ሲል ነበር የተዘባቡተው ። እነጀዋር ከነዚህ ጋር ነው በመተባቡር ቤተ-መንግስት ለሠግባት የሚጎመዡት ።
.
ሕወሓት/ወያኔ ኢትዮጵያዊነታቸውን ካመከነባቸው ትውልዶች አንዱ ጀዋርና ተከታዮቹ ናቸው ። እነሱ በተራቸው እንደ መንፈስ አባታቸው ሕወሓት የእናት አባቱን አገር የሚረግም ፣ በአገሩ ታሪክና ክብር ላይ የሚዘባበት እንዲሁም አፉን አብዝቶ የሚከፍት ትውልድ እየቀፈቀፉልን ። የእናታቸውን ሆድ እንደሚባጭሩ ቀደውም እንደሚወጡ የእፉኝት ልጆች እየሆኑ ነው ። በነዚህ የምትመራ ኢትዮጵያን ማሰብ ዘግናኝ ነው ።
.
ከሐጫሉ ሞት ጋር ተያይዞ ጀዋራዊያን በብዙ ባሕር ማዶ ከተሞች ” Dawon-Dawon Ethiop ! … Dawon -Dawon Habesha ! ” እያሉ መፈክር ሲያሰሙ ታይተዋል ። ነሐሴ 2/2012 በሙካከለኛው ምስራቅ (በተባቡሩት ኢምሬት ) የሚገኙ እንስት ተከተያዮቹ ይህንኑ መፈክር አፅፈውና ተሸክመው አደባባይ ይወጣሉ ። ከኮሮና ጋር ተያይዞ ጥብቅ የሆነውን በአደባባይ ያለመሰብሰብ መመሪያ በመጣሳቸው በፓሊስ ይከበባሉ ። ሰልፈኛኞቹ በፖሊሶች ” ምንድናቹ ? ” ይባላሉ ።
” ኢትዮጵያዊያን ነን ” ይላሉ ።
መቼም ፖሊሶቹ ” ኢትዮጵያ ትውደም ! ሐበሻ ይውደም ! ” የሚሉ ፤ …… ደግሞም ” ትውደም ! ” የሚሏትን አገር ዜግነትና ፓስፖርት የያዙ ሰልፈኞች ሲገጥማቸው ሳይገረሙ አይቀሩም ። ፖሊሶቹ ጉደኞቹና አገራቸውን በአደባባይ የሚረግሙትን ወደ 300 የሚጠጉ ሴቶች ወደ እስር ቤት ይወረውራቸዋል ። እያንዳንዳቸውም በኢትዮጵያ ሲመነዘር 60 ሺህ ብር በመቅጣት ከማስጠንቀቂያ ጋር ይፈታቸዋል ። እንግዲህ ይህ የመሰለ በአገርና በወገን ጥላቻ የነደደ ቡድን አገር ለመምራት መንበረ-ስልጣን ቢይዝ አገርና ዜጋን ከማንደድ የተሻለ እድል አይሰጥም ።
.
ጀዋር …. እሱ በቀደደው ቦይ ፤ አለያም በዘረጋው ሐዲድ የሚፈሱለት መንጋዎችን ከየትኛውም ብሔር ይመለምላል ። ኦሮሚያ ውስጥ ሊተክለው ለሚፈልገው ስርአት ግብአት ሊሆኑት የሚችሉ ተመሳሳይ ቡድኖች በሁሉም ብሔሮች ውስጥ እንዲኖሩ መርዙን ይዘራል ። ከሲዳማ ፣ ከወላይታ ፣ ከስልጤ ፣ ከሐረሪ ፣ ከቅማንት ፣ ከጉራጌ ለጥፋቱ የሚያሰማራቸው ጥቂት ወጣቶችን አደራጅቷል ።
.
” የሲዳማን ክልልነት በሐይል እናስፈፅማለን ! ” ሲል በአደባባይ ለእጀቶ ያስተላለፈውን መልእክት ተንተርሶ ” 11-11-11 ” በተባለው የሲዳማ የክልልነት ፕሮግራም ወቅት ብዙ ውድመት ተፈፅሟል ። ባለፈው ሁለትና አንድ አመት የጀዋር የእጅ ስራ ውጤት የሆነው እጀቶ በሐዋሳ ሳይቀር በጠራራ ፀሐይ ፣ ሰው በሚጎርፍበት አደባባይ ወጣቶችን በጋዝ አቃጥሏል ። በኮብል ስቶንና በዱላ እየቀጠቀጠ ገሏል ፤ ንብረት እንዲዘረፍና እንዲወድም አድርጓል ። እነዚህ ጥፋቶች ሁሉ የጀዋር ቀመሮች ናቸው ። ጀዋር በተመሪዎቹ አማካይነት የሚያስፈፅማቸው መገለጫዎቹ ናቸው ።
.
ጀዋር በንስሀ-ዘመናቸው ጀሌዎቹ ለመሆን የፈቀዱ አዛውንቶችን ጭምር ከጎኑ አሰልፎ ” የኦሮሞ ዘር ፣ ታሪክ ፣ ቋንቋና ባህል የተበላሸው ኦሮሞ ከሌላው ጋር በመጋባቱ ነው ። ኦሮሞ በርስቱና በራሱ ከተማ … ቤት ተከራይቶ የሚኖረው ከመጤውና ከወራሪው ብሔር ነው ። እሱ ቤት ሰርቶ ለማከራየት ቀርቶ የራሱን ደሳሳ ጎጆ ቀልሶ ለመኖርም እድል አልተሰጠውም ” የሚል እጅግ መርዘኛ ቅስቀሳ በመርጨት እልቂትና ጥላቻ እንዲነግስ ሲሰራ ቆይቷል ። በየመድረኩም ቀጥታ በልሳናቸው በOMN በሚተላለፍ ” ከነፍጠኛ የተጋባህ ተፋታ ፤ እናፋታለን ። ” ሲሉ ይናገራሉ ። በእነዚህ የምትመራዋን ኢትዮጵያን ማሰብ ዘግናኝ ነው።
.
ጀዋራዊያን አጋጣሚዎችን እየተጠቀሙና አንዳንዴም እየፈጠሩ አገር ያምሳሉ ፤ ዜጎችን በደቦ ያስገድላሉ ። ንብረት ያሶድማሉ ፤ በአመፅና በሆታ ቤተ-መንግስቱን ለመቆጣጠር ይሻሉ ። ለዚሁም አጠና የተሸከሙ ተከታዮቻቸውን ወደ ከተማ ያተማሉ ። ” ሂድ ! … የነፃነትህ ቀን ዛሬ ነው ፤ ሂድ ! … ቤተመንግስቱን ተቆጣጠር ፤ … ይህን የነፍጠኛ ተላላኪ አብይን ከቤተ-መንግስቱ ኮሌታውን ይዘህ አውጣ ! …. ሂድ ወደ ፊንፊኔ ! ” እያሉ በሚዲያ ያውጃሉ ። ይህ ” ሂድ ! ” የሚል ቅስቀሳ ሐጫሉ በሞተበት እለት እስቄል ጋቢሳ በOMN ቀጥታ ከአሜሪካ ሲያስተላልፈው የነበረው መልእክት ነው ። ጀዋርና ጀዋራዊያን የሽብር ፊት አውራሪዎች ፣ የጥላቻ መፈልፈያ ማሺኖች ናቸው ።
.
ጀዋር ሰሞኑን ደግሞ አንድ አዲስ ደቀ መዝሙር መልምሏል ፤ ብርሃነ መስቀል አበበ ሰኚ የሚባል ። ይህ ሰው በሚኒሶታ የኢትዮጵያ ቆንሲላ ዳይሬክተር ሆኖ የተሾመ ነበር ። አሜሪካዊ ፓስፖርት የያዘ በመሆኑ የአሜሪካ ፓስፖርት መልሶ በሐላፊነቱ እንዲቀጥል ትእዛዝ ቢሰጠውም ለመመለስ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ስልጣኑን ለቋል ። በዚህም ” ኦሮሞ በመሆኔ ከሐላፊነት ተነሳሁ ” ሲል የፅንፈኞቹን ሚዲያ አጣቧል ። ቄሮ ኦሮሚያ ውስጥ ባለ ነፍጠኛ ላይ እንዲዘምት አረፋ እስኪደፍቅ ፣ የግንባር ደም ስሩ እስኪገተር እንዲሁም ጎሮሮውን በሚተናነቀው እልህ ጭምር ጥሪ ያስተላልፋል ። የብርሃነ መስቀል አበበ ሰኚ ሁኔታ ” የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ ” አይነት ነው የሆነብን ። እሱ ኢትዮጵያዊ ባለመሆኑ በኢትዮጵያ ፖለታካ ጉዳይ ምንም አያገባውም ። የኢትዮጵያ ፖለታካ ባለጉዳዮች እኛ ኢትዮዮጵያዊያኖች ብቻ ነን ። አጠፋንም አለማን እኛው በፖለቲካችን ጉዳይ የምንለውን እንላለን ። እንግዲህ አንዱ በአንዱ ላይ እንዲነሳ የሚቀሰቅሱ እንደነዚህ እንደ ብርሃነ መስቀል አይነት ናቸው ኢትዮጵያን ለመምራት የሚቃዡት ።
.
ከብዙ የነጀዋር አጀንዳዎች አንፃር ኢትዮጵያ በነሱ ልትመራ እንደምትችል ማሰብ በራሱ ሽብር ነው ። መቼም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የመጨረሻውን የርግማን መአት ካሎረደባቸው በስተቀር በነሱ እጅ ሊወድቁ አይችሉም ። አለያም የተቀረው ዜጋ እጅግ በጠለቀ ድንዛዜ ውስጥ ካልሰጠመ በቀር የኢትዮጵያን መንበረ-ስልጣን አይጨብጡም ። ” ኢትዮጵያ በነዚህ እጅ ወደቀች ” ማለት ፤ ” የሞት ሸለቆ ፣ የደም መሬት ፣ ገሃነምን የምታስንቅ የመከራ ስፍራ ሆነች ! ” እንደ ማለት ነው ። ” ከሩዋንዳም ፣ ከዩጎዝላቪያም ፣ ከየመንም ፣ ከሶሪያም ፣ ከሊቢያም ፣ ከአፍጋኒስታም የከፋች የስቃይ ምድር ለመሆን ታጨች ” ማለት ይቻላል ። በጀዋራውያን የምትመራ እትዮጵያን ማሰብ ….. ኢትዮጵያዊያን በጋለ የዳቢሎስ ብረት ምጣድ ላይ ሲታመሱ የማየት ያህል ነው ። አማሹ ጀዋር ስለሚሆን …
Filed in: Amharic