>

ጄኖሳይድና መከላከያ ብልሀቱ ! ክፍል ፪ (ሉሉ ከበደ)

ጄኖሳይድና መከላከያ ብልሀቱ !

ክፍል ፪
ሉሉ ከበደ

«ጄኖሳይድ ዋች » የዘር ፍጅት የሚያልፋቸውን እርከኖች ሲያስቀምጥ በአምስተኛ ደረጃ ላይ የሚኖረው ” አደረጃጀት”  ነው ፡፡ ጄኖሳይድ በተደራጀ መልኩ ነው የሚሰራው ፡፡ ድርጅት ፡፡
ምእራብ ሱዳን ዳርፉር ግዛት ውስጥ  በግመልና በፈረስ ርባታ የሚታወቁ አረብ ዘላኖች ፤ አካባቢው በጦርነትና በተፈጥሮ ቀውስ ሲታመስ ፤ ተደራጅተን ራሳችንን እንጠብቃለን በማለት  ወታደራዊ እንቅስቃሴ ጀመሩ ፡፡ ጃንጃዊድ ሚሊሽያ ተባሉ  ፡፡  የጥቁሮቹን ከብቶች መዝረፍ ፤ ንብረት ማውደም ፤ መውረስ ፤ ቀጠለ ፡፡ እ ኤ አ 2003/ 2004 የካርቱም መንግስት በወቅቱ ከደቡብ ሱዳን ጋር የመገንጠል ጦርነት ላይ ነበር ፡፡ እነዚያን በራሳቸው የተደራጁትን  ሽፍቶች ፤ እብረን እንስራ ብሎ ተዋዋለና በትጥቅ ፤ በስልጠና ፤ በስንቅ  ፤ እያገዘ እንዲያውም ሌሎች አረቦች ከሌላ ቦታ እየመጡ እንዲቀላቀሏቸው አድርጎ  ፤ ዳርፉር ግዛት ውስጥ ፤ ከባዶ ተነስቶ የራሱን ፈጥኖ ደራሽ አጥቂ ጦር  አደራጀ ፡፡ ፈጠረ  ፡፡ ጥቁሮቹን ሱዳኖች ከዳርፉር በማጽዳት ይህ ነው የማይባል ስራ ሰሩለት ፡፡ ጄኖሳይድ፡፡ የሱዳን መንግስት ግን እጄ የለበትም ብሎ እንደካደ ለመውደቅ በቃ ፡፡ አንድ በዚ መንገድ ጄኖሳይድ ይሰራል፡፡
ሁለተኛው መንገድ ደሞ አለ ፡፡ ጉደኞቹ የኦነግ ሰዎች ፤ ማለቴ ሁሉም የኦሮሞ ድርጅቶች የኦሮሞ ህዝብ ከኢትዮጵያ ህዝብ በቁጥር የሚበልጥ ስለሆነ ኢትዮጵያን በበላይነት ፤ በምንፈልገው መንገድ እኛ መግዛት አለብን እንደሚሉት ፤ ህንድ ውስጥም መቶ አመት አካባቢ እድሜ ያለው « ራሽትሪያ ዋያም ሴቫክ » ( RSS ) የሚባል ልክ ኦነግ እንደሚለው ፤ በህንድ ውስጥ የሂንዱ ዘሮች ቁጥር የላቀ ስለሆነ ፤ ህንድን መግዛት ያለበት ሒንዱ ነው ፡፡ « እኛ ነን መግዛት ያለብን» ብለው እንካሁን ይታገላሉ ፤ የህንድ መንግስት ፊት ባይሰጣቸውም ፡፡ እነዚህ ሰዎች ህንድ ፤ በሂንዱ መንፈሳዊ አስተዳደር ነው መገዛት ያለባት እንጂ አለማዊ መንግስት አያስፈልገንም ነው የሚሉት ፡፡ ልክ የኦነግ ጅሎች የገዳ ሲስተም እንዘረጋለን እንደሚሉት ፡፡ ክርስቲያኖችንና ሙስሊሞችን ከህንድ ማጽዳት የመጀመሪያ ግባቸው ነው ፡፡ በመንጋ ወረራ የታወቁ ናቸው ፡፡ በገጀራ፤ በቢላዎ ፤ በቆመጥ ፤ በድንጋይ ፤ ቀጥቅጦ መግለል መለያቸው  ነው ፡፡ በመንግስት እውቅና ያልተሰጠው ኢመደበኛ አደረጃጀት ይባላል ነገሩ ፡፡ ይህ ማለት ቄሮ ማለት ነው ፡፡  የጃዋር ሰራዊት ፡፡
ሶስተኛው መንገድ ደሞ አለ ፤ እንደናዚ ሂትለር ልዩ የሰለጠነ ኮማንዶ ተደራጅቶ በግልጽ ተፈላጊ ያልሆነውን ዘር የማጽዳት ስራ የሚሰራ ፡፡
 አራተኛውን ከሩዋንዳ እንፈልገው ፡፡ “ኢንተር ሀምዌ ”  አድገው ክንዳቸው ያልጠና ፤ ድህነት ያጎሳቆላቸው ፤ በከተማ ውስጥ እየተሯሯጡ ፤ እየሰረቁም ፤ እየተሽከሙም ፤ እየቀሙም ፤ የለት ጉርሳችውን የሚያገኙ ታዳጊዎች ፤ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያልጨረሱ ፤ መርዛማውን የዘር ፖለቲካ ሲ ጋቱ ያደጉ ወጣቶች ተመለመሉ ፡፡  የሁቱ መንግስት መሪዎች ያለበቂ ስልጠና ገጀራ ፤ ጠመንጃ ፤ መጥረቢያ ፤ አስታጥቀዋቸው (RTLM ) የሚባል ራዲዮ  ፤ በ ኦ ኤም ኤን ስታይል የሚሰራ ሁቱ ልጆችን መርዝና መመሪያ ይግታቸው ጀመር ፡፡ ቱትሲዎችን እንዳይምሩ ፤ ለዘብተኛችን እንዳይምሩ ፤ « እነዚህን በረሮዎች ግደሏቸው » እያለ  ፤ አረቄና ቢራ ከህዝቡ ቤትና መጋዘን  እየዘረፉ ፤ እየተጋቱ ፤ በስካር አጨዳውን ተያያዙት ፡፡ ወደ ሚሊዮን የሚጠጋ ሁቱና ለዘብተኛ ቱትሲ ሬሳ አመረቱ ፡፡
ወደ ሀገራችን ስንመጣ ምን አይነት አደረጃጀት ተዋቅሮ ነው  ጄኖሳይዱን እያስፈጸመ ያለው ያልን እንደሆን መጀመሪያ ቶሎ ወደ አ እምሮአችን የሚመጣው የጃዋር ቄሮ ኢመደበኛው አደረጃጀት ነው  ፡፡ እንልና ፤  ያ ብቻ አለመሆኑን የሚጠቁም ነገር ደሞ እናያለን ፡፡ በተለይ ካለፉት ሁለት አመታት ወዲህ ያየነው ታሪክ የተለየ ነው ፡፡ የመንግስት ጦር ሰራዊት ፤ ፖሊስ ፤ ደህነነት ባለበት ሀገር ውስጥ ዘር የማጽዳቱ ኦፕሬሽን በሰላም ተጀምሮ በሰላም ይጠናቀቃል ፡፡ ጭፍጨፋውን የሚመሩት ሰዎች እቅዳቸውን ካሳኩ በኋላ  «ሆይ ሆይ ሆይ»  ይባልና  « መከላከያ ባይደርስ ኖሮ ፤ ፌዴራል ባይደርስ ኖሮ » የሚል ዲስኩር ከመንግሰት ሰዎች ዘንድ ያደነቁረናል ፡፡ አብርሀ በላይ ሰሞኑን እንዳለው አንዲት መትረየስ የጫነች ወታደራዊ ጂፕ ልኮ መንጋውን ወደቤቱ መመለስ ምንም አያውክም ፡፡ መሳሪያ ታጥቆ ሊገድል ንብረት ሊያወድም የመጣ ህገወጥ መንጋ ነው ፡፡ በመሳሪያ ምላሽ ይሰጠዋል ፡፡ በቀላሉ የሚገባው ቋንቋ ነው ፡፡ ወደቤቱ ይመለሳል ፡፡ የሌላውን ነፍስ ነው እንጂ ኢንዲጠላ የተደረገው የራሱን ነፍስ እኮ ይወዳታል ፡፡
እና በመጨረሻ «ጄኖሳይድ ዋች»  ምፍትሄ ብሎ ያቀረበው ነገር አለ ፡፡ በህጋዊ መልክም ሆነ በህገወጥ መንገድ ተደራጅተው ጄኖሳይድ የሚፈጽሙ ስብስቦችን ህገወጥ ማድረግ ፡፡ መሪዎቻቸውን ከአለም አቀፍ በረራ ማገድና ለፍርድ ማቅረብ ፡፡ በውጭ ያላቸው ንብረትም እና ገንዘብ እንዲያዝ ማድረግ ፡፡ የዘር ማጽዳት ወንጀል በፈጸሙ መንግስታትና ቡድኖች ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጦር መሳሪያ ማእቀብ መጣል ፡፡ በሩዋንዳ ውስጥ እንደተደረገው የዘር ፍጅቱ በተፈጸመ ማግስት ፤  ገለልተኛ አጣሪ ኮሚሽን ማቋቋም ፡፡ የጥላቻ ንግግርና የጥላቻ ወንጀል የሚፈጽሙ  ዜጎችን ለፍርድ አቁሞ ጠንካራ  ቅጣት መስጠት ፡፡
ይቀጥላል…
Filed in: Amharic