>

ይድረስ ለፊንፊኔ ኢንተርሴብት ! (አቻምየለህ ታምሩ)

ይድረስ ለፊንፊኔ ኢንተርሴብት !

አቻምየለህ ታምሩ

* ጃዋር የሰዎችን ስልክና ኢንተርኔት እንደሚጠልፍ የተናገረውንና ባላፈው ሳምንት  አስታውሰን በፈስቡክ የጻፍነውን  ጉዳይ ፖሊስ ተብዬው ዛሬ  ማረጋገጡን ነግሮናል …! 
ባለፈው ሳምንት ከቴሌ እውቅና ውጭ የሚሰራ የሳተላይት መቀበያ ጃዋር መሐመድ ቤት ውስጥ መገኘቱን ከፖሊስ እንደሰማ ሪፖርተር ጋዜጣ መዘገቡት ተከትሎ ፖሊስ ጃዋር መሐመድ በአንደበቱ ከወራት በፊት አገር ቤት ካለ አንድ ሚዲያ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ሰዎች በስልክ የሚያወሩትንና በኢሜል የሚጻጻፉትን በመጥለፍ ሚስጥራዊ መረጃ እንደሚሰበስብ በአደባባይ የተናገረውን ፖሊስ አልሰማም ነበር ወይ? የሚል ጥያቄ አንስቼ ነበር።
[ ባለፈው ሳምንት የጻፍነውን ይህንን  ትር በመጫን ይመለከቷል፤  https://www.facebook.com/achamyeleh.tamiru.3/posts/3265548213467105]
ጃዋር ራሱ በኩራት የተናገረውን  ይህንን ጀብዱን አስታውሼ  ሳተላይት ቤቱ አገኘሁ ላለስ ፖሊስ  ቀደም ያለውን ጥያቄ በማንሳቴ  የጃዋር መንጋዎች  “ቴክኖሎጂ የማያውቅ” አድርገው እንደጉድ ዘምተውብኝ ነበር። በነገራችን ላይ ጃዋር በአደባባይ የስልክና የኢንተርኔት ግንኙነቶችን እንደሚጠልፍ በቃለ መጠይቅ የተናገረውን በማስታውስ ባለፈው ሳምንት እዚህ ፌስቡክ  ላይ እስክንጽፍ ድረስ ፖሊስ  ተብዮው ጃዋር ስልክና ኢንተርኔት እንደሚጠልፍ በአደባባይ የተናገረውን መርምሮ  አልደረሰበትም ነበር 🙂
ዛሬ ግን   ጃዋር ከወራት በፊት  በአድባባይ የተናገረውንና  ከቴሌ እውቅና ውጭ የሚሰራ የሳተላይት መቀበያ ፖሊስ ቤቱ አገኘሁ ሲል  ጃዋር በአንደበቱ  የስልክና የኢንተርኔት ግንኙነቶችን እንደሚጠልፍ በቃለ መጠይቅ የተናገረውን  አስታውሰን  ባለፈው ሳምንት የጻፍነውን  ፖሊስ ተብዬው   ለፍርድ ቤት ተብዮው እንዳስታወቀው ጃዋር በመሳሪያው አማካኝነትም የታዋቂ ሰዎችን ስልክ በመጥለፍ ሚስጥራዊ ጉዳዮችን ሲያዳምጡ እንደነበር አስታውቋል 🙂
አጋጃቸው [እረኛቸው ላለማለት ነው] ሰዎች በስልክ የሚያወሩትንና በኢሜል የሚጻጻፉትን በመጥለፍ ሚስጥራዊ መረጃ እንደሚሰበስብ በአደባባይ የተናጋረውን በማስታወስ በመጻፌ በሳተላይት ስልክና ኢንተርኔት እንደማይጠለፍ የማያውቅ እያሉ ሲሰድቡን የሰነበቱት መንጋዎቹ ዛሬ የዐቢይ አሕመድ ፖሊስ ጃዋር  በመሳሪያው አማካኝነትም የታዋቂ ሰዎችን ስልክ በመጥለፍ ሚስጥራዊ ጉዳዮችን ሲያዳምጡ እንደነበር ደርሼበታለሁ ሲል ምን ይሉ ይሆን?።
አቶ ጃዋር መሃመድ በዛሬው እለት በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ችሎት ልደታ አዳራሽ ቀርበዋል፡፡
መርማሪ ፖሊስም ባለፉት ቀናት ያከናወናቸውን ስራዎች በጠቀሰበት ሪፖርቱ በአቶ ጃዋር መኖሪያ ቤት በድጋሚ ባደረገው ፍተሻ መሳሪያዎቹን ማግኘቱን አስታውቋል፡፡
በመሳሪያው አማካኝነትም የታዋቂ ሰዎችን ስልክ በመጥለፍ ሚስጥራዊ ጉዳዮችን ሲያዳምጡ እንደነበር ማስረጃ መሰብሰቡን አስታውቋል፡፡
ከዚህ ባለፈም በርካታ ተጨማሪ አዳዲስ ግኝቶችን በምርመራ ማግኘቱን ለችሎቱ ይፋ አድርጓል።
አቶ ጃዋር በበኩላቸው የፖሊስ ምርመራ እኔን አይመለከትም ይህ የፖለቲካ ጉዳይ ነው ሲሉ ተቃውሞ አሰምተዋል።
ፍርድ ቤቱም አቶ ጃዋር ባነሷቸው አቤቱታዎች ዙሪያ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
የችሎቱን ሙሉ ዝርዝር ይዘን እንመለሳለን”
ከችሎቱ ውሎ በተያያዘ – ይናገራል ፎቶ! 
 
ትናንት ጃዋር መሐመድ አደባባይ ላይ ከህግ በላይ ሆኖ እንደ ልቡ ፍለጠው ቁረጠው እያለ ሲፈነጭ  እንዳልነበር ዛሬ ጃዌ ፍርድ ቤት ውስጥ ጨዋነት በተሞላበት መንገድ በትህትና አቤቱታውን ሲያቀብ አይተነዋል። ሁለት የተለያዩ ሰዎች እንጂ አንድ ሰው አይመስልም። ዛሬ ያለን አንድ መንግስት ብቻ ነው።
Filed in: Amharic