>

የዘር ጭፍጨፋ የሚጀምረው ከጥላቻ ንግግር ነው ...!!! (ታምሩ ብርሀኑ)

የዘር ጭፍጨፋ የሚጀምረው ከጥላቻ ንግግር ነው …!!!

ታምሩ ብርሀኑ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጥላቻ ንግግር በዓለም ላይ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ንጹሃን ሞት ምክንያት ሆኗል። የሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ ከመከሰቱ በፊት የጥላቻ ንግግር ነበር ። የአይሁዳውያን በመርዝ ጋዝ ከማለቃቸው በፊት ምክንያቱ የጥላቻ ቅስቀሳና ያንን አምኖ ለማስፈጸም የሚችል ስልጣን ያለው በጥላቻ የነደደ ኃይል ስለነበር ነው።
ትላንት እነ በቀለ ገርባ ሚዲያ ላይ ቀርበው ዜጎችን በገዛ አጋራቸው አስወጡ አሳዱ ሲሉ አርሲ ላይ ወዲያው ምልክት ታይቶ ነበር።በማህበራዊ ሚዲያ ተጮኸ መንግስትም ሰምቶ እንዳልሰማ አለፈው። የአርቲስት ሃጫሉን ግድያ ተከትሎ የዘር ማጥፋት ቅስቀሳው በዚህ ውጭ አገር ተቀምጠው ማንም አይነካንም ባሉ ብሶዋል።ሁሉም ፉከራዎች በአግባቡ ተሰናድተው ቢያንስ ዋና ዋናዎቹን ተጠያቂዎች በህግ ለመጠየቅ እንደሚቻል አቶ ጥበበ ሳሙኤል ፈረንጅ ትልቅ ምሳሌ ናቸው። በግላቸው በሁለት ግለሰቦች ላይ ክስ መስርተዋል። ዝርዝሩን ወደፊት ይገለጽ ስላሉ እንመለስበታለን። ዛሬም የጥላቻ ቅስቀሳ አድራጊዎች ናቸው የትላንቱ የሻሸመኔ እንል ባኣስር የአርሲ ወረዳዎች፣በድሬዳዋ፣በሐርረር እና በአዲስ አበባ ለብዙዎች ብሄር እና ሃይማኖት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ማንገድ ያመቻቸው።የዛሬው የጥላቻ ቅስቀሳ እንደ ቀልድ ካለፍናው ነገ የሌሎች ንጹሃንን ሕይወት ይቀጥፋል። ስማቸውን የዳበቁም ሆነ ባግልጽ ያሉ የጥላቻ ንግግር አድራጊዎች፣ግደለው አውድመው ባዮችን በጋራ ልንፋረድ ይገባል ለማለት እንዋዳላን።
ስል ጥላቻ ንግግር እና መዘዙ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአንድ ወቅት ያወጣውን ቪዲዮ ደግመን ወዲህ አምጥተነዋል።
Filed in: Amharic