>

" እኔ በተጠረጠርኩበት  ወንጀል እስክንድር እና የልደቱን ማሰር  ግልፅ የፖለቲካ ፍርድ ነው!" (ጃዋር መሀመድ ለፍርድ ቤት የሰጠው ቃል)

” እኔ በተጠረጠርኩበት  ወንጀል እስክንድር እና የልደቱን ማሰር  ግልፅ የፖለቲካ ፍርድ ነው!” 

ጃዋር መሀመድ ለፍርድ ቤት የሰጠው ቃል
 
“የወንጀል ምርመራ አይደለም የፖለቲካ ፍርድ እንጂ”
“ከአቶ እስክንድርና ከአቶ ልደቱ አያሌውጋር ያለኝ የፖለቲካ አመለካከት የተለያየ ሆኖ ሳለ ፤ እኔ በተጠረጠርኩበት እነሱንም ማሰር ሆን ተብሎ ተቃዋሚዎችን ከፖለቲካ ጎራ የማስወጣት እንጂ የወንጀል ምርመራ አይደለም ፤ ግልፅ የፖለቲካ ፍርድ ነው”
ጃዋር በፍርድ ቤት ይህንን ቃል መናገሩን የጃዋር ጠበቃ አቶ ቱሉ ባይሳ ለBBC Amharic ተናግረዋል ።
 
*     *    *
“ለሆነው ነገር እና እየሆነ ነገር ላለው ሁሉ ተጠያቂው መንግስት ነው!!!”
 ኢ/ር ይልቃል ጌትነት 
“የእኔ ጉዳይ ከእዚህ ችሎት አቅም በላይ ነው። ያ ባይሆን አንድ ቀን ማደር አልነበረብኝም። ዝም የምለው ቃለ መሃላ ፈፅመው ለተቀመጡት ዳኛ ክብር ስላለኝ ነው እንጅ ለሆነው ነገር እና እየሆነ ነገር ላለው ሁሉ ተጠያቂው መንግስት ነው።
24 ሰዓት ስለ ፍትሕ ስርዓቱ መሻሻል በሚወራበት ሃገር ፖሊስ የፖለቲካ ውሳኔ እያስፈፀመ ነው። እኔ ብሔርና ብሔር እንዳይጋጩ ስጮህ ነበር።
በብሔር ግጭት መክሰስ ለእኔ ፌዝ ነው።” ኢ/ር ይልቃል ዛሬ በችሎት የተናገረው ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ
ጊዜ 10 ቀን ተፈቅዶ ለነሃሴ 4 ቀን 2012 ዓ.ም በድጋሜ ተቀጥረዋል።
አክቲቪስት እና የሕግ ባለሙያው አዲሱ ጌታነህ ከስፍራው እንደዘገበው..
Filed in: Amharic