>
5:18 pm - Thursday June 16, 2191

ይሄን ባልፅፈው ባታይዩትና እንደእኔ ባትታመሙ ደስ ይለኝ ነበር  - ግን ደሞ ቃሌ ነው! (ጋዜጠኛ መአዛ መሀመድ)

ይሄን ባልፅፈው ባታይዩትና እንደእኔ ባትታመሙ ደስ ይለኝ ነበር  

– ግን ደሞ ቃሌ ነው!

ጋዜጠኛ መአዛ መሀመድ

• ብርሃኑ ዝቅአርጋቸው ተወልዶ ያደገው አርሲ ነው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ሲሆን
• ኦዳ ቡልቱም ዩንቨርስቲ መምህር ነው
• የአራት ሴትና አንድ ወንድ ልጅ አባት ነው
• በጭሮ ከተማ ከ30አመት በላይ ቤተሰብ መስርቶ ንብረት አፍርቶ ይኖር የነበረ ነው።
*   *   *
ብርሃኑ ዝቅአርጋቸው በምእራብ ሃረርጌ በአራጆች በግፍ አገዳደል በድንጋይ፣ በሜጫ፣ በአጠና ተደብድቦ የተገደለ ነው። ሰኔ 23/2012 ከሃጫሉ ሞት ማግስት ከቀኑ 4:00 ሰአት አካባቢ እቤቱን ለማቃጠልና ንብረት ዘርፈው እርሱንም ገድለው ለመሄድ የመጡት ጽንፈኞቹ በቅድሚያ ይህንን ተግባር እንደሚፈጽሙ እቤት ለነበረችው ባለቤቱ ነግረው እርሷ ልጆችዋን ይዛ እንድትወጣ ካደረጉ በኋላ በእለቱ የነበረን የመስሪያ ቤት ባልደረባ ልጅ ሞት. በመሞቱ ቀብር ቆይቶ በቤቱ እየተከናወነ ያለውን ድርጊት የሰማውና የመጣው የቤቱ ባለቤት አቶ ብርሃኑ ዝቅአርጋቸው በድርጊታቸው አሳዝኖ ችች እርሱም ጥያቄአቸውን ተቀብሎ  የሶስት አመት ህጻን ወንድ ልጁን ይዞ ከቤት እየወጣላቸው እያለ በመጀመርያ ልጁ ፊት ግንባሩን በድንጋይ በመምታት ዋናውን የመጡበትን የመግደል ስራ ሲጀምሩ እርሱም ለማምለጥ ልጁን ለእናቱ ትቶ ደሙን እያፈሰሰ ሮጦ በመሸሽ ጎረቤት ግቢ ውስጥ በአጥር ዘሎ በመግባት የቤቱ ባላቤት ዳቦ መጋገርያ ነበረውና ዳቦ ማቡኪያ ገንዳ ውስጥ ደብቆት በላዩ ላይ የዱቄት ማዳበርያ በማልበስ ቢሸሽገውም ጽንፈኞቹ ከሌላ የጎረቤት ሰው በደረሳቸው ጥቆማ ግቢውን አስገድደው በማስከፈትና በመግባት የቤቱን ባለቤት በመደብደብና በማስገደድ ከተደበቀበት ቦታ አውጥተው በዚህ መልክ በግፍ ገድለውታል። ሬሳውን እስከ ቀኑ 10:00ሰአት ድረስ እንዳይነሳ በመከልከል አስከሬኑ ስር ቁጭ ብለው ጫት ሲቅሙ ከዋሉ በኋላ መከላከያ ሰራዊት ከተማዋን ከተቆጣጠረ በኋላ ሄዶ አስከሬኑን በማምጣት መኖርያ ቤቱ ስለወደመ ከተማው ውስጥ በሚገኝ በታላቅ እህቱ ቤት እንዲያርፍ አድርጎአል።
በማግስቱም ከከተማው ውጭ በሚገኘው በአጥቢያው በእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስትያን ሬሳው እንዳይቀበር ጽንፈኞቹ በመከልከላቸው በከተማ ውስጥ ባለችው በደብረ ጽዮን ቅድስት ልደታ ማርያም ቤተክርስቲያን እንዲቀበር ሁኗል።
ይሄን የሚነግሯችሁ ልጆቹ ናቸው እና ሀገር እንዳይፈርስ ዝም በሉ ልበላቸው?
Filed in: Amharic