>

በኢትዮጵያ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሟል ! " (የሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን")

 

በኢትዮጵያ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሟል ! “

የሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን”
የምስራች አለሙ

የሰርቢያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እ.ኤ.አ ባሳለፍነው ጁላይ 14 ቀን 2020 ዓ.ም በይፋዊ ድረ ገጿ ላይ ባወጣችው ዘገባ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሟል በማለት ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን እንኳ የካዱትን የኦርቶዶክሳውያንን መገፋት ፣ መጨፍጨፍ እና የማጥፋት ዘመቻ የሩቋ ሰርቢያ ኦርቶዶክሳውያን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ድምፅ ሆነውልን ተስተውለዋል።
ሁሉም የተጀመረው ታዋቂው የኦሮምኛ ሙዚቀኛ ሃጫሉ ሁንዴሳ በአዲስ አበባ ከተማ መገደሉን ተከትሎ መሆኑን የሚያትተው የሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፅሁፍ በአክራሪዎች እና በፅንፈኞች አቀነባባሪነት ፍፁም ሰብዓዊነት በማይሰማቸው ሰዎች አሰቃቂ ወንጀል ተፈፅሟል ይላል።
“እነዚያ ቀናት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ክርስቲያኖች አሰቃቂ ነበሩ ” ሲል ያከለው ፅሁፉ በጥቃቱ ክርስቲያን የኦሮሞ ተወላጆችን ጨምሮ የተለያዩ ብሄረሰቦች ተወላጆች ሰለባ ሆነዋል በማለት በዝርዝር አስቀምጧቸዋል።
ምንም አይነት የመንግስት አካላት ጣልቃ ገብተው ችግሩን ለማረጋጋት ጥረት አለማድረጋቸውን እንዲሁም ከጥቃቱ በኋላ ወታደሮች መሠማራታቸውንም የሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በገጿ አስፍራዋለች። ቤተ ክርስቲያኗ
Borkena.com እና ሌሎች አለምአቀፍ ሚዲያዎች የሰሩትን ሪፖርት በመመልከት የኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ ዞን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ከማኅበረ ቅዱሳን ቴቪ ጋር ባደረጉት ቆይታ ላይ የዘረዘሯቸውን የጥፋት መጠኖች በሙሉ በዝርዝር ያስቀመጠች ሲሆን ባሳለፍነው ጥቅምት ወር በደረሰው ጥቃት በርካታ አቢያተ ክርስቲያናት ላይ የደረሰውን ቃጠሎና ውድመት ብሎም በኦርቶዶክሳውያን ላይ እየተደረገ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በይፋዊ ድረ ገጿ ላይ ዘግባለች።
የሰርቢያ እርቶዶክሳውያን ወንድሞቻችን በዚህ መልኩ የኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን ሰቆቃ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለማሳወቅ ላደረጉት አስተዋፅኦ ምስጋና የሚገባቸው ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥም ጥፋቱን ለመሸፋፈን እና የተለየ የዓመፅ ተግባር ብቻ አስመስሎ እንዲታይ ለማድረግ እየተሄደበት ያለው ርቀት ብዙ የሚያዛልቅ አይደለም እና ይህንን ተግባር በሚዲያ ጭምር በመታገዝ እየሰሩት የሚገኙ የመንግስት አካላት በሙሉ ሊያስቡበት እና ሊያጤኑት ይገባል ! ተወደደም ተጠላም የኦርቶዶክሳውያን ሰማዕታቱ ደም ይፋረዳል !
አሁንም ፣ በቀጣይም በኦርቶዶክሳውያን ላይ እየደረሰ የሚገኘው የዘር ማጥፋት ወንጀል ሊበቃ ይገባል !
ፎቶ :- ከሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ይፋዊ ድረ ገፅ ቅፅበታዊ ገፀ ምስል የተወሰደ
ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኘውን ሊንክ በመጫን የቴሌ ግራም እና የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
Filed in: Amharic