>

ነሐሴ ፩- አደባባይ የወጡ የአማራ እንቦቀቅላወች በግፍ የወደቁበት የእውነተኛ ሰማዕታት ቀን ነው! (አቻምየለህ ታምሩ)

ነሐሴ ፩- አደባባይ የወጡ የአማራ እንቦቀቅላወች በግፍ የወደቁበት የእውነተኛ ሰማዕታት ቀን ነው!

አቻምየለህ ታምሩ

ነሐሴ ፩- አደባባይ የወጡ የአማራ እንቦቀቅላወች የወደቁበት የእውነተኛ ሰማዕታት ቀን ነው!
ስናይፐር በጦር ሜዳ እንኳ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በጦር አዛዦች ብቻ የሚያዝ ትጥቅ ነበር። በፋሽስት ወያኔ የአፓርታይድ አገዛዝ ግን ስናይፐር ተራ የፋሽስት ወያኔ ነፍሰ በላ ወታደሮች በአማራ ሰላማዊ እምቦቀቅላዎች መካከል እየገቡ ሕጻናትን ለመረሸን የሚታጠቁት ተራ የጦር መሳሪያ ለመሆን በቅቷል።
ነሐሴ አንድ 2008 ዓ.ም. የባሕር ዳር ቦዩች ሁሉ ስናይፐር በታጠቁ የፋሽስት ወያኔ ወታደሮች በታረዱ የአማራ ሕጻናት ደም ተሞልተውና የከተማው መንገዶች በጠቅላላ ነፍሰ በላ ወታደሮች በግፍ በረሸኗቸው የአማራ ልጆች አስከሬን ተሸፍነው ውለው የአደሩበት ቀን ነበር። ዕለቱ የፋሽስት ወያኔ ነፍሰ በላይ ወታደሮች አርደው ያጋደሟቸው የአማራ እንቦቀቀቅላዎች ሬሳ በሬሳ ላይ የተከመረበት፣ ባሕር ዳርም የደም ጎርፍ የወረደባት ምድር የሆነችበት ጥቁር ቀን ነበር። ይህንን ለትግራይ ሪፑብሊክ ሲባል ስናይፐር የታጠቁ የፋሽስት ወያኔ ነፍሰ በላ ወታደሮች በአማራ ሕጻናት ሬሳ ላይ የተረማመዱበት ቀን ምላሳችን ከትናጋችን እስኪጣበቅ ድረስ የማንረሳው ሰማዕቶቻችንን የማንረሳበት የመከራ ቀናችን ነው።
ነሐሴ አንድ በመጣ ቁጥር በፋሽስት ወያኔ ወታደሮች የተካሄደው የአማራ ጭፍጨፋ ይታወሳል። ነሐሴ አንድ ለትውልድ የምናወርሰው ታሪክም ትቶልናል። በየአመቱ ነሐሴ አንድ በመጣ ቁጥር የፋሽስት ወያኔ ነፍሰ በላ ፋሽስት ወታደሮችን ክብረ ወሰን የተቀዳጀ የአረመኔነት ጥግ [ለዛሬውና ለመጭው ትውልድ] በአማራ ልጆች የሬሳ ክምር ዶሴ የምናስተምርበት እለት ነው።
ነሐሴ አንድ ቀን የተካሄደው የአማራ ጭፍጨፋ ይሳካ ዘንድ የያኔው የፋሽስት ወያኔ ነውረኛ ድርጅት የሆነው ብአዴንም የጽሕፈት ቤቱን ሕንጻ አማራን ለማጥቃት የሰለጠኑ የፋሽስት ወያኔ አልሞ ተኳሽ ወታደሮች በምሽግነት እንዲጠቀሙበት አድርጓል። ሙሉ ለሙሉ ባይባልም ባመዛኙ በእለቱ ለት የፋሽስት ወያኔ ወታደሮች ያካሄዱት የአማራ እምቦቀቅላዎች ጭፍጨፋ የተካሄደው ብአዴን ጽሕፈት ቤት አናት ላይ ስናይፐር ታጥቀው በመሸጉ የፋሽስት ወያኔ ወታደሮች ነበር። ይህም ከታች በተያያዘው ታሪካዊ ምስል ላይ ይታያል።
በዐቢይ  አሕመድ የተቀባው አማራ ክልል የሚባለው አካባቢ  እንደራሴ የበዓለ ሲመቱ ግብዣ ላይ ሲቀኝ፤
ምሳርማ ምን ያርግ የብረቶች ልጅ፣
ያ የእኛ ወልጋዳ አስጨረሰን እንጅ፤
በማለት ያቀረበው ግጥም የሚገልጸው ማንንም ሳይሆን ራሱን ብአዴንን ነው። የአማራ ልጆች እንዲጨፈጨፉ ምሽግ የሆነው የብአዴን ጽሕፈት ቤት ከአማራው መሀል ወጥተው አማራውን ያስጨረሱ ወልጋዳ አማሮች ተምሳሌት ነው።
በመሆኑም ባመዛኙ ከአማራ መካከል የበቀሉ ወልጋዶች የተኮለኮሉበት ድርጅት የሆነው ብአዴን ተለውጫለሁ የሚል ከሆነ የአማራ እንቦቀቅላዎች እንዲጨፈጨፉ ምሽግ ሆኖ ያገለገለውን ጽሕፈት ቤቱን ዘግቶ ወደ ሙዚዬምነት በመቀየር የነሐሴ 1 የአማራ ልጆች ሰማዕታት መታሰቢያ እንዲሆን ሊያደርገው ይገባል።
ለአማራ ኅልውና ስትሉ በትውልድ ቅያችሁ ሆናችሁ መብታችሁን በመጠየቃችሁ በፋሽስት ወያኔ አማራ ጠል የትሕነግ ቅልብ ነፍሰ በሎች በግፍ ለወደቃችሁ የነሐሴ አንድ ሰማዕቶቻችን ከፍ ያለ ክብርና ሞገስ ይድረሳችሁ። ቀሪው ወገናችሁ በደማችሁ የለኮሳችሁትን የተጋድሎ ችቦ ይዞ የሞታችሁበትን ክቡር አላማ ከዳር ለማድረስ ስለተነሳ መስዕዋትነታችሁ በደማችሁ ከጻፋችሁት ታሪክ ጋር ለዘላለም አብሮ ይኖራል! ፈጣሪ አምላክ ነፍሳችሁን መንግሥተ ሰማያት ያዋርስልን!
ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ ለጀግኖቻችንና የነሐሴ ፩- ሰማዕታት!
Filed in: Amharic