>

“ጥቃቱ የሦስተኛውን መቶ ክፍለ ዘመን ሰማዕትነት የደገመ ነው!!!” (ከማኀበረ ቅዱሳን)

“ጥቃቱ የሦስተኛውን መቶ ክፍለ ዘመን ሰማዕትነት የደገመ ነው!!!”

ከማኀበረ ቅዱሳን
ቤተ ክርስቲያን እና ምእመናን ሲጠቁ የኖሩት ሙስሊም በሚበዛባቸው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በሚገኙ  አካባቢዎች ነው፡፡  የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ሽፋን በማድረግ  በምእመናንና በንብረታቸው ላይ አሳዛኝ ጥቃት ተፈጽሟል፡፡ ካለፉት አርባ እና አምሳ ዓመታት ጀምሮ ጥቃቱ  በተደጋጋሚ የሚፈጸመው በባሌ፣ በአርሲ፣ በጅማ፣ በሐረርጌና በከሚሴ ነው፡፡ ጥቃቱን የሚፈጸመውም በአክራሪ ሙስሊሞች ነው፡፡
….
ከድርጊቱ ማረጋገጥ እንደሚቻለው አክራሪው ሙስሊም  ለመግደልና ንብረት ለማውደም ሃይማኖት እንጂ ብሔር አይመርጥም።  የጥቃት ዒላማ ለመሆን የክርስቲያን እምነት ተከታይ መሆን በቂ ነው፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆነው ጥቃት በተፈጸመባቸው አካባቢዎች በርካታ የሸዋ ኦሮሞዎች ኦርቶዶክስ ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ነው። ከመገደላቸው በተጨማሪ ሀብት ንብረታቸው ተዘርፏል፤ ተቃጥሏልም፡፡ ከሌላ አካባቢ ሔደው የሚኖሩ ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች ቢኖሩ እንኳ የክርስቲያኖች ንብረት ወድሞ የሙስሊሞች ሕይወትም፣ ንብረትም አለመነካቱ በአክራሪዎች ታቅዶና ታስቦ መፈጸሙን ያስገነዝባል።
…..
የሚፈጸመንውን ጥቃት  ለማስቆምም ሆነ ለዘለቄታው የቤተ ክርስቲያንን መብትና ክብር ለማስጠበቅ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጀምሮ በየደረጃው የሚገኙ አገልጋዮችም፣ የተቋቋሙ ማኅበራትም ከእስከ አሁኑ የበለጠ እና የተሻለ ሥራ መሥራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በቅንጅት ለዘመኑ የሚመጥን ተግባር መፈጸም ክልቻልን በሚፈጸመው ጥቃት ለመጥፋት ተባባሪ መሆን ነው፡፡ በአጭር ጊዜ ተጨባጭ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ተግባር ለማከናወን መነሣት እንጂ ሁል ጊዜ እንዲህ ተደረግን እያሉ እጅን አጣጥፎ መቀመጥ መፍትሔ አይሆንም።
….
የሚደርሰውን ጉዳት ለባለ ሥልጣናትም፣ ለዓለም ማኅበረሰብም ማስገንዘብ፣ የማያዳግም ውሳኔ እንዴሰጡ መጎትጎት፣ የተበለሸ እና የተመረዘ አመለካከት አስተምሮ አልስተካከል ካሉ የማያዳግም የርምት እርምጃ እንዲወሰድባቸው ተባብሮ መሥራት  ይገባል። በጥፋታችን እንቀጥላለን ያሉትን እና ለጥፋት እንቅልፍ አጥተው ድጋፍ የሚያደርጉላቸውን ባለሥልጣናትም  ደግሞ በሕግ ቍጥጥር ሥር  እንዲውሉ ሳይታክቱ ለሚመለከተው ማሳወቅ ያስፈልጋል።
የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች የአገረ አንድነት የማያሳስባቸው፣ ለሰው ሕይወት ዋጋ የማይሰጡ መናቸው ይታወቃል። የሰውን ሕይወት በከንቱ ከማጥፋት ባለፈ ኦርቶዶክሳውያን በብዙ ውጣ ውረድ ለአርባና ሃምሳ ዓመታት ያፈሩትን ሀብትና ንብረት ጭምር በአንድ ጀንበር ሲያወድሙ የሚያስቡበት አእምሮ አላቸው ብሎ ለመናገር ያዳግታል። የሃይማኖት፣ የሥነ ምግባር እና የመንግሥት ሕግ የማይገዛቸው በማጥፋት ሐሤትን እናገኛለን ብለው የሚደክሙ በመሆናቸው ገዳዮች ቢሆኑም ቤተ ክርስቲያን ትጸልይላቸዋል። ቤተ ክርስቲያን ይህን የምታደርገው ስለተገደሉት ብቻ ሳይሆን ስለገዳዮችም መጸለይና በፍቅር ማሸነፍ እንጂ ሰይፍ ማንሣትን ባሕርይዋ ስለማይፈቅድላት ነው። ክርስቲያኖች ልንኮራ እና ሁል ጊዜ ደስ ሊለን የሚገባንም የዚች ቤተ ክርስቲያን ልጆች በመሆናችን ነው። የኦርቶዶክሳውያን አስተሳሰብ  ከአክራሪ ሙስሊም አስተሳሰብ የሚለየውም ለዚህ  ነው፡፡ የኦርቶዶክሳውያን አስተሳሰብ ለአገር አንድነት የቆመ፣ ለሰው ሕይወት ዋጋ የሚሰጥ፣ በሃይማኖት እና ምግባር የሚመራ እንዲሁም ለመንግሥት ሕግ የሚገዛ ነው፡፡ ይህንን እንደሞኝነት የሚቈጥረው ደግሞ ለጥፋት ይሰለፋል።
…..
ቤተ ክርስቲያን አገርን ከጠላት ተከላክላ እና አንድነትን አስጠብቃ የኖረች በመሆኗ ብቻ  አክራሪው  በሚፈጽምባት ትንኮሳ ካላት ሰማያዊ ዓላማ እና አገራዊ ተልእኮ ፈቀቅ አትልም። ካበደው ጋርም አብራ አታብድም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ለአገር አንድነትና ለሃይማኖት እኩልነት ዋጋ ሰጥታ ባትታገሥ ሊከሠት የሚችለውን መገመት ቀላል ነው።  አክራሪውን እንደ አመጣጡ ለመመለስ  ቀላል ቢሆንም ውጤቱ አገርን የሚያጠፋ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ቤተ ክርስቲያንን የሰው ሞት ይቅርና የእንስሳ ሞት የሚያስጨንቃትና እጽዋትን ተንከባክባ ለትውልድ የምታሻግር ናት። የሞራል ልዕልና ከሌለው ጋር ማበድ ለክብሯ አይመጥንም፡፡ ክርስቲያኖች በሥነ ምግባር ተኮትኩተው ያደጉ በመሆናቸው በሌሎች ቤተ እምነቶች ላይ ጥቃት ፈጽመው አያውቁም፡፡
 ክርስቲያኖችን በጭካኔ መግደልም ሆነ ንብረታቸውን ማውደም የሚነግረን  አክራሪው ሙስሊም “ግርግር ለሌባ ይመቻል” የሚባለውን  ስልት ተግባራዊ በማድረግ ለዓመታት ያቀደውን ጥቃት ለመፈጸም አጋጣሚ ሲጠብቅ መኖሩን ነው፡፡
….
ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች የሌሉባት ኦሮምያን ለመመሥረት ይሠራ እንደነበር በተደጋጋሚ ሲገልጥም ቆይቷል፡፡  እየተፈጸመ የለውን  ጭፍጨፋ ለማስቆም ክርስቲኖች ምን ማድረግ እንደሚጠበቅብን መረዳት ይኖርብናል፡፡ አንዳንድ ወገኖች የኃይል አጸፋ እንድንመልስ ይወተውታሉ፡፡ ክርስቲያኖች እንዲህ ቢያደርጉ አገር እንደ አገር የመቀጠሏ ሁኔታ ጥያቄ ውስጥ ይወድቃል፡፡  የሚበጀው ግን ግራ ቀኝ በማየት ለዘለቄታው የሚሆነንን ማከናወን ነው። ክርስቲያኖች እጃቸውን አጣጥፈው ቆመው በአክራሪዎች  ሰይፍ መገደል የሌለባቸው ቢሆንም በሕጋዊ መንገድ አደብ  ማስገዛት ያስፈልጋል ፡፡ ጥቃቱ የሦስተኛውን መቶ ክፍለ ዘመን ሰማዕትነት የደገመ ” በመሆኑ ከሰማዕታቱ በረከት እንዲከፍለን ፈጣሪያንን መማጸን ይኖርብናል።
Filed in: Amharic