>
5:18 pm - Thursday June 15, 3911

የገዳ ሥርዓት የቋንቋ ፖሊሲ ትናንትና ዛሬ.. !!! (አቻምየለህ ታምሩ)

የገዳ ሥርዓት የቋንቋ ፖሊሲ ትናንትና ዛሬ.. !!!

አቻምየለህ ታምሩ

በዐቢይ አሕመድ  ሳንባ የሚተነፍሰው አባ ገዳ ሺመልስ አብዲሳ እውነተኛ  አባ ገዳ ነው። እሱ ግን እውነተኛ አባ ገዳ  መሆኑን የሚያውቀው አይመስለኝም። ይህን እንድል ያስቻለኝ  ኢትዮጵያን የወረሩት አባ ገዳዎችን የቋንቋ ፖሊሲ እያራመደ የ«ቋንቋ ጭቆና»  ነበረብን፤ ለዚህም ነው ኦሮሞ ትግል የጀመረው ሲል ስለሰማሁት ነው። በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ታሪክ በነገድ  ላይ የተመሰረተ የባሕል ማጥፋትና የቋንቋ ጭቆና በተሳካ ሁኔታ ያካሄዱ ቢኖሩ  የሺመልስ የመንፈስ አባቶች የሆኑት የኦሮሞ አባገዳዎች ብቻ  ናቸው። አባ ገዳ ሽመልስ ሽመልስ አብዲሳ በአማርኛ መቃብር ላይ ኦሮምኛን ለማሳደግ እየሰሩ እንደሆነ የነገረን  የቋንቋ ፖሊሲያቸው ይህን የገዳ የቋንቋ ፖሊሲ ቅጂ ነው።
የኦሮሞ አባገዳዎች በገዳ  ወታደራዊ ሥርዓት እየተመሩ ከቦረና ተነስተው  ለምለሙን  የኢትዮጵያ ክፍል ሲወሩ የሚወሩትን ነባር ሕዝብ እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የሚከተሉት የቋንቋ ፖሊሲ ነበራቸው። ይህ የቋንቋ ፖሊሲያቸው «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”» የሚል ነበር። ይህ የኦሮሞ አባገዳዎች የቋንቋ ፖሊሲ ወደ አማርኛ ሲተረጎም «ኦሮምኛ የሚናገር ወገናችን ነው ይገብር፤ ኦሮምኛ የማይናገር ጠላታችን ነው ይጥፋ”» እንደ ማለት ነው። የዘንድሮው አባ ገዳ ሽመልስ  አብዲሳ በአማርኛ መቃብር ላይ ኦሮምኛን ለማሳደግ እየሰሩ እንደሆነ የነገረን ይህን የጥንቶቹን አባ ገዳዎች የቋንቋ ፖሊሲ ቃል በቃል በመቅዳት ነው።
የኦሮሞ አባገዳዎች «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”» በሚለው የቋንቋ ፖሊሲያቸው እየተመሩ ከሀያ  ስምንት በላይ የኢትዮጵያ ነባር ቋንቋዎችን አጥፍተዋል፤ ባሕላቸውንና ማንነታቸውን በተሳካ ሁኔታ አጥፍተዋል፤ ከርስታቸው አፍልሰው ባለርስቱን በገዛ መሬቱ ላይ ገርባ ወይም ባሪያና ጭሰኛ አድርገው  ለዘመናት ሲጨቁኑትና ሲሸጡት ኖረዋል።  እነ ሺመልስና ዐቢይ በአማርኛ  ላይ ለመድገም እየሰሩ  ያሉት  ይህን የመንፈስ አባቶቻቸው ውርስ ነው።
ባጭሩ በአፍሪካ ታሪክ የተሳካ የቋንቋ  ጭቆና የማድረግ ተሞክሮና ልምድ ያላቸው የኦሮሞ አባገዳዎች ብቻ ናቸው። አፍሪካን በቅኝ ግዛት የያዙት አውሮፓውያን በመላው አፍሪካ ያጠፉት የአፍሪካ ቋንቋ ቁጥር የኦሮሞ አባገዳዎች «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”» በሚለው የቋንቋ ፖሊሲያቸው ካጠፉት የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ቁጥር ጋር የሚወዳደር አይደለም።
ስለ ቋንቋ እኩልነት ሊያስተምሩን የሚፈልጉ ኦነጋውያን «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”» የሚል የቋንቋ ፖሊሲ የነበረውን ገዳን እያሞገሱና በዚህ የቋንቋ ፖሊሲ እየተመሩ በአፍሪካ ውስጥ ባልተደረገ ሁኔታ ከሀያ በላይ ነባር የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን በፖሊሲ ያጠፉ አባገዳዎች ልጆች ነን የሚሉን ጉዶች ናቸው። የአባገዳ ልጅና የገዳ ሥርዓት ናፋቂ ስለ ቋንቋ እኩልነት የመከራከርና የመሟገት የሞራል ልዕልና የለውም።
ቀድመው በማልቀስ ጩኸታችንን እየቀሙ የሚፈልጉትን ማግኘት የለመዱት ኦነጋውያን በእውነቱ ስለ ቋንቋ እኩልነት የሚያስቡና በቋንቋ መጨቆን በደል እንደሆነ የሚያምኑ ቢሆን ኖሮ በሌለ ነገር ላይ ጣታቸውን ወደ ሌላው ከመጠቆማቸው በፊት ወደራሳቸው ማየት ነበረባቸው። ከሁሉ በፊት የሚያሞግሱት የገዳ ሥርዓት የቋንቋ ፖሊሲ የሆነው «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”» በተሳካ ሁኔታ ላጠፋቸው ከሀያ በላይ የሚሆኑ ነባር የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ተንበርክከው ይቅርታ መጠየቅና ለጠፉት ቋንቋዎች መካስ፤ በገዳ ስርዓት ቋንቋቸው እንዲጠፋ ተደርጎ በገዛ በርስታቸው ላይ ኦሮሞ ገርባ አድርጎ በባርነት ሲገዛቸውና ሲሸጣቸው ለኖሩት ከሀያ በላይ የኢትዮጵያ ነገዶች ደግሞ እስካሁን ለተጠቀሙት አፈላማ ከፍለው መሬታቸውን መልቀቅ ነበረባቸው።
ለኦነጋውያን የበጃቸው ነገር ቢኖር የሚነግሩትን ሁሉ የሚያምነው ንፍጥ የሚለቀቅለው ያላዋቂ ሳሚ መብዛቱ ነው። «ደቡብና ኦሮሞን ምኒልክ ወርሮ፣ ቋንቋውን ጭቆ፣ የብሔር ጭቆና አካሂዶብናል» እያሉ ኦነጋውያን የሚያወሩትን ፕሮፓጋዳ ሁሉ ሳይመረምር እንደ እውነት የተቀበሉት ቁጥራቸው ቀላል የሚባል አይደለም። ባለፈው ስሞን አንዱ «ዶክተር» በሲዳማ ሜዲያ ኔትወርክ ላይ ቀርቦ «ደቡብና ኦሮምያ የነበረው የገባር ስርዓት ምኒልክ ኢትዮጵያን አንድ ሲያደርግ የመጣ ነው» እያለ ከዶክተር የሚጠበቀውን ንባብ አለማድረጉን ባደባባይ እያሳወቀ ነበር።
ዳግማዊ ምኒልክ ወደ ደቡብ ባይሄዱ ኖሮ ዛሬ ሲዳማ የሚባል «ብሔር» ሊኖር እንደማይችል ይህ ዶክተር አያውቅም። የኦሮሞ አባገዳዎች «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”» በሚለው የቋንቋ ፖሊሲያቸው ያጠፏቸውና ይውጧቸው እንዲሁም በባርነት እየጠፈነጉ ተሽጠው ይጨርሷቸው እንደነበር ይህ ዶክተር ጭንቅላቱ ለምርመራ ዝግ በማድረጉ ሊያውቅ አልቻለም።
የገባር ስርዓት የኦሮሞ ስርዓት ነው። ዳግማዊ ምኒልክ ኦሮሞ በወረራ  የያዘውን ደቡቡን የቀድሞ የኢትዮጵያ ክፍል መልሰው ከያዙ በኋላ የኦሮሞን የገባር ስርዓት ሙሉ በሙሉ ማስቀረት ባይችሉም፣ አባገዳዎቹንና ባላባቶችን ግን አስገድደው ስርዓቱ እንዲሻሻል አድረገው ነበር። የአባ ገዳዎች ባሪያዎች የነበሩና ባላባቱ በፈቀደው ጊዜ የሚሸጣቸው የነበሩት ገርባዎቹ ሕይዎት የተሻሻለው ዳግማዊ ምኒልክ አባገዳዎችን ካስገበሩ በኋላ አባገዳዎችና ባላባቶች ተስፋፍተው ከያዙት መሬት እንዲያካፈሉ ባደረጉት ማሻሻያ ነው። ለዚህ ዝክር ነገርን ያነቧል።
ከዳግማዊ ምኒልክ በፊት የኦሮሞ አባገዳዎች በወረሩባቸው አካባቢዎች ውስጥ ገርባ አድርገው የሚገዙትን ሕዝብ ሚስቱንና ልጆቹን ሳይቀር ነጥቀው በባርነት ይሸጡት እንደነበር የኦሮሞ ብሔርተኛው ፕሮፈሰር መሐመድ ሐሰን The Oromos of Ethiopia በሚለው መጽሐፉ ገጽ 126 ላይ ነግሮናል። የጉማው ንጉሥ መላ ገባሩን ከነቤተሰቡ ይሸጥ እንደነበር ፕሮፈሰር መሐመድ ነግሮናል። ከኢትዮጵያ በባሪያ ንግድ ኤክስፖርት የተደረጉት ሰዎች በአብዛኛው ኦሮምኛ ተናጋሪ የሆኑበትም ምክንያት አንዱ ይሄ ነው። ሆኖም ግን እነዚህ ሰዎች ኦሮሞዎች አልነበሩም፤ «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”» በሚለው የአባ ገዳ የቋንቋ ፖሊሲ ኦሮምኛ እንዲናገሩ የተገደዱ ገርባዎች እንጂ። ምይ ይኼ ብቻ! ፕሮፈሰር መሐመድ በዚህ መጽሐፉ ገጽ ከ128-129 የጉማው የኦሮሞ ንጉሥ የሰው ስጋ ይበላ እንደነበር ቸሩሊን በመጥቀስ ነግሮናል።
የየም ሕዝብ በአባ ጅፋር ተመናምኖ ለወሬ ነጋሪ የተረፈው ዳግማዊ ምኒልክ ማስጠንቀቂያ ቢሰጡና ደንብ ቢያወጡ የባሪያ ንግድ አላቆምም በማለታቸው መጨረሻ ላይ አዲስ አበባ ተጠርተው እንዲመጡና አፍቀራ እንዲታሰሩ ከተደረገ በኋላ ነው። የእናሪያ ሕዝብ ባሕሉም ቋንቋውም «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”» በሚለው የአባ ገዳ የቋንቋ ፖሊሲ ለወሬ ነጋሪ ሳይቀር ጠፍቷል። የወለጋ፣ የኢሉባቡር ነባር ሕዝብ ገርባ ፍለጋ በሄዱ የኦሮሞ ጦረኞችና አባገዳዎች መዳፍ ውስጥ ወድቆ ቋንቋና ማንነቱ እንዲጠፋ ተደርጎ ኦሮምኛ ተናጋሪ ሆኖ የቀረው «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”» በሚለው የገዳ ስርዓት የቋንቋ ፖሊሲ ነው።
የሚያሳዝነው ነገር ግን «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”» በሚለው የገዳ ስርዓት የቋንቋ ፖሊሲ አባገዳዎች ቋንቋውን ያጠፉበትን ሕዝብ ዛሬም የአገዳ ልጆች ናቸው ነን የሚሉን ኦነጋውያን በድንቁርና ይዘው ማንነቱን እንዳያውቅ ስላደረጉት «ኦሮምያ» የምትባለዋን የተስፋ ኢምፓየር የመመስረቻ ቅዠታቸውን መወጫ እያደረጉት ይገኛሉ።
ባጭሩ  አባ ገዳ ሺመልስ እያራመዱት እንደሆነ የነገረን የቋንቋ ፖሊሲ «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”» የሚለው የአባገዳ የቋንቋ ፖሊሲ ቅጂና  ኦሮምኛ ከሚናገረው ማኅበረሰብ ውጭ ያለውን ሕዝብ ቋንቋ በተሳካ ሁኔታ  የጠፋበትን የወንጀል ፖሊሲ ነው። ይህን  የወንጀል ፖሊሲ  በበላይነት የሚመራው ዐቢይ አሕመድ ነው።  ዛሬ ላይ «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”» የሚል የቋንቋ ፖሊሲ የሚያራምዱ ጉዶች ያልተጫነውን አማርኛን ተጫነ የማለት የሞራልም የኅሊናም ልዕልና የላቸውም።
Filed in: Amharic