
ወላይቶች በሰላማዊ መንገድ ጥያቄ ማቅረባቸው ሊያስደንቃቸው እንጅ ሊያሳስራቸውም አይገባም!!!

መስከረም አበራ
የወላይታ የክልልነት ጥያቄ የሚያነሱ ፖለቲከኞች፣ምሁራን ትግላቸውን ሲጀምሩ ከመታገያ መርሆቻቸው አንዱ ከየትም ቦታ መጥቶ በወላይታ የሚኖር በማንኛውም የሰው ልጅ ላይ ምንም አይነት የግድያ ቀርቶ ግልምጫ እንዳይደረግ የሚል ነበር።
ወላይቶች ጨዋ ታጋዮች ናቸው።አንድም ሰው ገድለው፣በማንም ንብረት ላይ እጃቸውን አንስተው አያውቁም። የክልል ጥያቄ ያነሱትም ለፍተው ባቀኑት የአዋሳ ከተማ ጨምሮ በየሄዱበት መገደል ቢመራቸው ነው።
የክልል እንሁን ጥያቄያቸው ከሲዳማ ጥያቄ የሚለይበት ነገር የለም። ጥያቄያቸውን ደም ሳያፈሱ ማቅረባቸው ሊያስደንቃቸው እንጅ ሊያሳስራቸውም ሊያስገድላቸው አይገባም።

መንግስት እየመረጠ መግደሉን ያቁም !!
ኦሮሚያ ላይ ይህንን ያክል ሰው ሲያልቅ፣ ሲዘረፍ፣ ሻሸመኔን የሚያክል ከተማ በቁሙ ሲነድ ሰላምን ለማስከበር ወላይታ ላይ ያደረገውን ግማሹን እንኳን ቢያደርግ ቢያንስ ከሞተው ግማሹ ሰው በተረፈ ነበር።