>

"ጠቅላዩ ቱግ ያለችውን ሽሮዋን ብአዴንን አማስሏት አብርዷት እንድትበላ አድርጓት ተመልሧል...!!!" (ዘመድኩን በቀለ)

“ጠቅላዩ ቱግ ያለችውን ሽሮዋን ብአዴንን አማስሏት አብርዷት እንድትበላ አድርጓት ተመልሧል…!!!”

ዘመድኩን በቀለ

 

ወግ አይቀር አደል የባህርዳሩ የበድኑ ብአዴን ስብሰባ ከወትሮው ትንሽ በተለየ መልኩ ሞቅ ለማለት የሞከረ ነበር።  
•••
• ቆይ ግን እናንተ በየፌደራል መንግሥቱ ውስጥ እንድትሠሩ የተመደባችሁ የዐማራ አመራሮች ምን ትሠራላችሁ? 
 
• ይሄ ሁላ በደል በህዝባችን ላይ ሲፈጸም ምንድነው ሥራችሁ?   
 
• እስከመቼስ ነው እንደዚህ ሆነን የምንቀጥለው?  
• ክልል (በረት) ላይ ያለነው ክልሉን(በረቱን) በሚገባ እየመራን ነው። እናንተ ግን በፌደራል የተመደባችሁቱ ምንም እየሠራችሁ አይደለም የሚል ጥያቄዎችን ነበር ያነሣው።
•••
አቢቹም ችግኝ ተከላ በሚል ሰበብ በባህርዳር የተነሣበትን የሽሮ ድንፋታ የመሠለ ተቃውሞ ለማብረድ ባደረገው ጉዞ ምን አልባት ሽሮዋ ብአዴን የምሯን ቱግ ብላ ምድጃውን እንዳታቆሽሽበትና በኋላ ደግሞ ምድጃውን ሲያጸዳና ሲያጸዳ እንዳይከርም ብሎ በማሰብ ነበር ሁለት ምርጥ ምርጥ የሽሮ ማማሰያውን ይዞ የገባው። የማማሰያዎቹም ስም ኮንቪንስና ኮንፊዩዝ ይባላሉ።
•••
አቢቹ ቦታውን ያዘ። ቀደም ሲል በድኗ ብአዴን ያነሣችውን ማለትም የክልሉ (የበረቱ) አመራር ያነሳቸውን ጥያቄዎች አጠቃልሎ እነዚህ፣ እነዚህ ነገሮች በስብሰባችን ተነሥተዋል። እናም እባክዎ ንጉሣችን፣ አለቃችን፣ ገዢያችን፣ እኛ ገረዶችህ፣ እኛ ባሮችህ፣ እኛ፣አሽከሮችህ፣ እኛ ሆድአደር ሆዳም አማሮች መፍትሄ ትሰጠን ዘንድ እንማጸንሃል ብለው በሁሌ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ኦቦ ደመአ መኮንን ሀሰን በኩል ለክቡር ዶ/ር ዐብይ አህመድ አሊ ቀርቦላቸዋል።
•••
የሚገርመው ዐቢይ በህወሓት ስብሰባ ላይ አይገኝም። በደቡብ ስብሰባ ላይ አይገኝም። በሌሎቹ ስብሰባ ላይ አይገኝም። በዐማራው ስብሰባ ላይ ግን አፍጥጦ ነው የሚከመረው። ተላላኪም እያለው አያምናቸውም። ንጉሡ ውሸታም ነው ብሎ አያምነውም። ተመስገን እንቅልፋም ነው። ተሻገር ካቲካላና ትሴ ላይ ስለሚጣበቅ አያምነውም። እናም ራሱ ሄዶ ቱግ ያለችውን ሽሮዋን ብአዴን አማስሏት አብርዷት እንድትበላ አድርጓት ተመልሧል።
•••
አብቹ ቀጠለ። እኔ ምን ላድርጋችሁ? በፌደራል እኮ ብዙ ሚንሥትሮች አሏችሁ። ነገር ግን መሥራት አይችሉም። ዞር ብሎ ሁሌ ምክትሏን ደመአን እስቲ ምን ሠራችሁ? በፌደራል መንግሥቱ እንዳትሠሩ እኔ ከለከልኳችሁ? ከአንተ ከደመአ ጀምሮ እንዳትሠሩ የተቃወምኩት የዐማራ ተወካይ ካለ አሁን ፊት ለፊት ይምጣ። (እናም አትበጥረቁብኝ አይነት ምላሽን ነው የሰጣቸው)
•••
እኔም ትዝብቴን ቀጥያለሁ። አሁን አለ የሽመልስን ንግግር ከቁብም አትቁጠሩት። ሽመልስ እንደዚያ የተዝረከረከው ንግግር ስለማይችል ነው። አሁን በኦሮሚያ ክልል (በረት) እምነት የምጥልበትና አቅም ያለው አንድም አመራር የለም። ይልቅ እናንተ ብታግዙኝ ነው የሚሻለው። ለውጥ ማምጣት ከፈለጋችሁ የራሳችሁን ሓላፊነት ተወጡ። ሁል ጊዜ ወደ ሰው አታሳብቡ። እያለ ነው የወረደባቸው።
•••
ደግሞም የሃጫሉን ሞት ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል (በረት) በደረሰው አደጋ። ( የእርድ አደጋውን) ከዐማራ ይልቅ የተጎዳው ራሱ ኦሮሞው ነው። አታካብዱ አይነት ንግግርም አድርጓል። ምንም አይደለም። ኦሮሞም ታርዷል ነው አቢቹ የሚለው። የታረዱት በሙሉ ግን የደመቀ መኮንንና የዐቢይ አሕመድ ሃይማኖት ተከታዮች እንዳልሆኑ ዐቢይ አልተናገረም። የታረዱት በሙሉ የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ልጆች መሆናቸውን መጥቀስ አልፈለገም።
•••
ሌላው ያሳቀኝ ነገር ስለ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በድፍረት የተናገረው ነገር ነው። አቢቹ ታኬን ሊበላት ሳያስብ አልቀረም። ታኬ ሲያቀብጣት ከአቢቹ በላይ ፎቶ አብዝታለች። ልክ መለስ አርከበን እንደበላው አቢቹም ታኬን ሽባ ልታደርገው ያሰበች ይመስላል። “ ትሰሙኛላችሁ በከንቲባውም ቢሆን እኔ በበኩሌ ብዙም እምነት የለኝም። ” በማለት ነበር ሽሮዋን ብአዴንን በማማሰያው አማስሎ አቀዝቅዟት እስከዛሬ ዓመት ድረስ ሳይለንት ሙድ ላይ ገሽሯት ወደ አዲስ አበባ የነካው።
•••
እኔ በስብሰባዉ እስከቆየሁበት ጊዜ የነበረው ድባብ መቼም ገራሚ ነበር። አቢቹ ከመምጣቱ በፊት የነበረው የጦፈ ክርክር አቢቹ ሲመጣ ምድረ ሆዳም የዐማራ ወኪል ነኝ ባይ ሁላ እንደ ለማዳ ድመት ጭራውን ይቆላልፈው ጀመር። እርምጥምጥ፣ ቁልጭልጭ ሲሉ ብታዩ ገራሚ ነበር። ኮስተር ብሎ የተቀመጠ ሰው ያየሁት አቶ ላቀ አያሌውን ብቻ ነበር። ላቀ ግን የሆነ ነገር ገብቶለታል። እንጂ ያለ ነገር እንዲህ አልሆነም።
•••
እኔም ቶሎ ወደ ሀገሬ መመለስ ስለነበረብኝ ልክ ዐብይ ከተሰብሳቢዎቹ በደመአ መኮንን በኩል የቀረቡለትን ጥያቄዎች ምላሽ እንደሰጣቸው ብዙም መቆየት ስላልፈለኩ ሹልክ ብዬ ነክቼዋል።
•••
ቆይቼ እስከአሁን ስሙ ባልተቀየረውና ህወሓት ዐማራን ያዋረደችበትን የባህርዳር ግምቦት 20 አውሮጵላን ማረፊያ ደረስኩ። አውሮጵላኑ ልንገባ  ተሰልፈን እያለ አካባቢው በሪፐብሊካኑ ጋርድ ተጥለቀለቀ። ወዲያው አቢቹ፣ ደመአ፣ እነ ገዱ ተግተልትለው መጥተው በአውሮጵላኗ ገቡ። እያየናቸው በረሩ። ዞር ስል ማንን ባይ ጥሩ ነው። አቶ ላቀ አያሌውን። አጠገቤ ያለውን ወንበር እየነረተ አኩርፎ ቁጭ ብሏል። እነ ንጉሡ ጥላሁን ስላቃጠሩ አቢቹ አኩርፎት ጥሎት ወደ ሸገር ነካው። ከምር ላቀ ተበላ። አሁን ወይ አበረ አዳሙ፣ ወይ ደግሞ ብርሃኑ ጁላ እንዳይበሉት ነው ስጋቴ።
•••
ካፒቴን ቴዎድሮስ የሚዘውራት ጢያራ ስትመጣ እኔም የተበሳጨው ጋሽ ላቀም ተያይዘን ወደ አዱ ገነት አብረን ነካነው። አውሮጵላን ውስጥ ግን የታዘብኩት ነገር ጋሽ ላቀ ኬኳ ስትመጣ አኩርፊአለሁ ብሎ አልተዋትም። ብስኩቷን ጥርቅም አድርጎ ነው የበላት። ቱ!  እኔ ካኮረፍኩ ምግብ ለመቅመስ ትንሽ እቆያለሁ። ብአዴንና ቢዴን መቸም አይጣል እኮ ነው።
•••
ከዚያ ለካቲካላው አፍቃሬ መለስ አቶ ተሻገር በተሰጠው መመሪያ መሠረት አቶ ሽመልስ አብዲሳ አለቃቸው የተናገረው ንግግር “ የኦቦ ሽመልስ ንግግር የግል አቋሙ ነው እንጂ የፓርቲው የብልጽግና አቋም አይደለም” እንዲል ቴፕ ቀርጸው፣ በተሻገር ሶፍትዌር ላይ ጭነው ለቢቢሲ እንዲናገር፣ መግለጫም እንዲሰጥ አደረጉት። ተሼ ፎልፏሌም ባሪያ ነውና፣ ሎሌም ነውና፣ ሲፈጥረው ለህወሓትም ለኦህዴድም አሽከር ተደርጎ የተፈጠረ ድርጅት አባል ነውና አሽከር ጌታው ያዘዘውን ቃል ሳያዛንፍ ተንፒሷል። አረቄያም አለ አጎቴ ሌኒን።
•••
እነ ዐቢይ በቀጣይ በብአዴን በኩል ዐማራውን ከትግሬ ለማባላት ወጥመድ ላይ ናቸው። እነ ተሻገርም እሱን እየሠሩ ነው። ዐማራና ትግሬ ግን ካልነቃ በእነ ዐቢይ መበላታቸው ነው። ተናግሬአለሁ።
•••
ነጋቲ ኦላ ቡላ  !!
Filed in: Amharic