>

ቀለብተኞቹ ብአዴኖች ባህርዳርን ለፌዴራል  መቀመጫነት አሳልፈው ለመስጠት ቋምጠዋል!!! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

ቀለብተኞቹ ብአዴኖች ባህርዳርን ለፌዴራል  መቀመጫነት አሳልፈው ለመስጠት ቋምጠዋል!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

ብአዴኖች ባሕርዳርን እንደ ድሬዳዋ ልዩ የፌዴራል ከተማ አሥተዳደር ከሆነች የሰነበተች አስመስለው ሲያወሩ መሰንበታቸውን ከቀናት በፊት ነግሬያቹህ ነበረ፡፡ የዚህን የጠላቶቻችን የብአዴኖች ወሬ ዓላማ ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ “አዲስ አበባን irrelevant ለማድረግ አምስት ከተሞችን መርጠናል!” ከማለቱ የተረዳቹህት ነገር እንዳለ እገምታለሁ፡፡ ከተመረጡት አምስት ከተሞች አንዷ ባሕር ዳር የመጀመሪያዋ ናት!!!
ይሄ ሁሉ ማጭበርበር ለበጎ እንዳይመስልህ ወገኔ፡፡ የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ጥናት የጣናን ዙሪያ የከተማዋ አካል ከማድረግ እቅዳቸው እንደተረዳቹህት ውብ የጣናን ዳርቻ ከገበሬው እጅ ነጥቀውና ገበሬውን አፈናቅለው አሰፍስፎ ላለው የውጭና የውስጥ ባለሀብት ለሪዞርትነት፣ ለውድ የመኖሪያ ቤቶችና ለመሳሰሉት አገልግሎት በመቸብቸብ የአማራን ሀብት ለመዝረፍ ነው ይሄ ሁሉ የማጨናበሪያ ምክንያት ሌላ እንዳይመስልህ!!!
የአማራን ዘር ከዚህች ሀገር የማጥፋት እርምጃቸው የመጨረሻ ግብ እኮ አማራን አጥፍተው የአማራ የሆነውን ሁሉ ለመውረስ ነው ሌላ አይደለም፡፡ መሬቱ እስኪተፋ ድረስ ከርሰምድሩ በነዳጅ ዘይት የተሞላ እንደሆነ የጎንደርና የቤተ አማራ (ወሎ) መሬት አፍ አውጥቶ እየተናገረ “እናውጣው!” ያላሉት ለምን ይመስልሃል ወገኔ???
“በቅድሚያ አማራን ከዚያ ምድር ማጥፋትና መሬቱን በእጃችን ማድረግ አለብን!” ብለው ስላሰቡ ነው ሌላ እንዳይመስልህ ወገኔ፡፡ ሠራዊታቸው አልበቃ ብሏቸው አንተን በቀንደኛ ጠላትህ በብአዴን አስረውና እንዳትታጠቅ፣ እንዳትሠለጥንና እንዳትደራጅ ከልክለው ትግሬና ኦሮሞ ይሄ ሁሉ በልዩ ኃይል ስም እያሠለጠኑት ያለው እንደ አሸን የፈላ ሠራዊት እየተዘጋጀልህ ያለው ለዚህ ዓላማ ነው ለሌላ እንዳይመስልህ!!!
መላው ዓለም እንደሆነ የአማራ ጠላት ነው፡፡ በአንተ ላይ ሲዘምቱና ሲጨፈጭፉህ አንድም የሚናገራቸው የሚኖር እንዳይመስልህ፡፡ እስከዛሬ ድረስ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ሲፈጽምብን ማንም የተናገራቸው እንደሌለና ዓይተው እንዳላዩ በመሆን እንዳለፏቸው ሁሉ ወደፊትም በጅምላ ሲፈጅህ ማንም የሚናገራቸው አይኖርም!!! እንዲያውም አማራን የማጥፋት የቤት ሥራው የተሰጣቸው ከእነሱ ማለትም ከባዕዳኑ ነው!!!
ብትነቃ ንቃ ባትነቃ የራስህ ጉዳይ!!!
ሌላው ቢቀር ጠላትን ይዞ መሞትና አንተ ሞተህ የአንተን ሀገርና ሀብት ወርሶ ሲምነሸነሽ እንዲኖር ዕድል አለመስጠትም ጀግንነት ነው!!!
ይህ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ነው ለአማራ!!!
Filed in: Amharic